ኢዮብ 17:1-16
17 “መንፈሴ ተሰብሯል፤ ዘመኔ አብቅቷል፤መቃብር ይጠብቀኛል።+
2 ፌዘኞች ከበውኛል፤+ዓይኔም የዓመፅ ተግባራቸውን በትኩረት ትመለከታለች።*
3 እባክህ፣ መያዣዬን ተቀብለህ አንተ ዘንድ አስቀምጥልኝ።
እጄን የሚመታና ተያዥ የሚሆነኝ ሌላ ማን ይኖራል?+
4 ማስተዋልን ከልባቸው ሰውረሃልና፤+ከዚህም የተነሳ ከፍ ከፍ አታደርጋቸውም።
5 የልጆቹ ዓይን ደክሞ እያለ፣ያለውን ለወዳጆቹ ሊያካፍል ይችላል።
6 አምላክ የሰዎች መቀለጃ* አደረገኝ፤+በመሆኑም ፊቱ ላይ እንደሚተፉበት ሰው ሆንኩ።+
7 ከሐዘን የተነሳ ዓይኔ ፈዘዘ፤+እጆቼና እግሮቼም እንደ ጥላ ሆኑ።
8 ቅን የሆኑ ሰዎች በዚህ ነገር በመገረም ትኩር ብለው ይመለከታሉ፤ንጹሕ የሆነውም፣ አምላክ የለሽ* በሆነው ሰው ይረበሻል።
9 ጻድቅ መንገዱን በጥብቅ ይከተላል፤+እጁ ንጹሕ የሆነ ሰውም እየበረታ ይሄዳል።+
10 ይሁን እንጂ ሁላችሁም ተመልሳችሁ መከራከራችሁን መቀጠል ትችላላችሁ፤ከእናንተ መካከል አንድም ጥበበኛ አላገኘሁምና።+
11 የሕይወት ዘመኔ አበቃ፤+ዕቅዴና የልቤ ምኞት ተንኮታኮተ።+
12 ሌሊቱን ወደ ቀን ይለውጣሉ፤‘ጨለማ ስለሆነ ብርሃን የሚፈነጥቅበት ጊዜ ቀርቧል’ ይላሉ።
13 ዝም ብዬ ብጠብቅ ያን ጊዜ መቃብር፣* ቤቴ ይሆናል፤+በጨለማ መኝታዬን እዘረጋለሁ።+
14 ጉድጓዱን*+ ‘አንተ አባቴ ነህ!’ እለዋለሁ፤
ትሏን ‘አንቺ እናቴና እህቴ ነሽ!’ እላታለሁ።
15 እንግዲህ የእኔ ተስፋ የት አለ?+
ተስፋ እንዳለኝ አድርጎ የሚያስብስ ማን ነው?
16 ሁላችንም ተያይዘን ወደ አፈር ስንገባ፣ተስፋዬ ወደተቀረቀሩ የመቃብር* በሮች ይወርዳል።”+
የግርጌ ማስታወሻ
^ ወይም “በዓመፅ ተግባራቸው ላይ ተተከለች።”
^ ቃል በቃል “መተረቻ፤ ምሳሌ።”
^ ወይም “ከሃዲ።”
^ ወይም “ሲኦል።” የሰው ልጆችን ሁሉ መቃብር ያመለክታል። የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
^ ወይም “መቃብሩን።”
^ ወይም “የሲኦል።” የሰው ልጆችን ሁሉ መቃብር ያመለክታል። የቃላት መፍቻውን ተመልከት።