ኢዮብ 28:1-28

  • ኢዮብ የምድርን ውድ ሀብት ከጥበብ ጋር አነጻጸረ (1-28)

    • ሰው ማዕድን ለማግኘት የሚያደርገው ጥረት (1-11)

    • ጥበብ ከዕንቁ ትበልጣለች (18)

    • ይሖዋን መፍራት እውነተኛ ጥበብ ነው (28)

28  “ብር የሚወጣበት ቦታ፣ወርቅም የሚነጠርበት ስፍራ አለ፤+   ብረት ከመሬት ውስጥ ይገኛል፤መዳብም ከዓለት ቀልጦ ይወጣል።*+   ሰው ጨለማን ያሸንፋል፤ማዕድን* ለማግኘትበጨለማና በድቅድቅ ጨለማ ውስጥ እስከ ወሰኑ ድረስ ፍለጋ ያካሂዳል።   ሰዎች ከሚኖሩበት ክልል ርቆ በሚገኝ ስፍራ፣ሰዎች ከሚመላለሱበት አካባቢ ርቀው በሚገኙ የተረሱ ቦታዎች ጥልቅ ጉድጓድ ይቆፍራል፤አንዳንድ ሰዎች በገመድ ወደዚያ ይወርዳሉ፤ ተንጠልጥለውም ይሠራሉ።   በምድር ላይ እህል ይበቅላል፤ከታች ግን ምድር በእሳት የሆነ ያህል ትታመሳለች።*   በዚያ በድንጋዮቹ ውስጥ ሰንፔር ይገኛል፤በአፈሩም ውስጥ ወርቅ አለ።   ወደዚያ የሚወስደውን መንገድ የትኛውም አዳኝ አሞራ አያውቀውም፤የጥቁር ጭልፊትም ዓይን አላየውም።   ግርማ የተላበሱ አራዊት አልረገጡትም፤ብርቱ አንበሳም በዚያ አላደባም።   ሰው የባልጩት ድንጋይ በእጁ ይመታል፤ተራሮችንም ከሥር መሠረታቸው ይገለብጣል። 10  በዓለት ውስጥ የውኃ ቦዮች ይሠራል፤+ዓይኑም ውድ የሆኑ ነገሮችን ሁሉ ያያል። 11  ወንዞች የሚፈልቁባቸውን ቦታዎች ይገድባል፤የተሰወረውንም ነገር ወደ ብርሃን ያወጣል። 12  ይሁንና ጥበብ የት ልትገኝ ትችላለች?+ማስተዋል የሚገኘውስ ከየት ነው?+ 13  ማንም ሰው ዋጋዋን አይገነዘብም፤+በሕያዋንም ምድር ልትገኝ አትችልም። 14  ጥልቁ ውኃ ‘እኔ ውስጥ የለችም!’ ይላል፤ ባሕሩም ‘በእኔ ዘንድ አይደለችም!’ ይላል።+ 15  እሷን በንጹሕ ወርቅ መግዛት አይቻልም፤በብርም ልትለወጥ አትችልም።+ 16  በኦፊር ወርቅም+ ሆነብርቅ በሆነው ኦኒክስና በሰንፔር ልትገዛ አትችልም። 17  ወርቅና መስተዋት* ከእሷ ጋር ሊወዳደሩ አይችሉም፤ምርጥ ከሆነ* ወርቅ በተሠራ ዕቃም እሷን መለወጥ አይቻልም።+ 18  ዛጎልና ክሪስታል ጨርሶ አይወዳደሯትም፤+ጥበብ በከረጢት ሙሉ ካለ ዕንቁ ትበልጣለችና። 19  የኢትዮጵያ* ቶጳዝዮን+ ከእሷ ጋር ሊወዳደር አይችልም፤በንጹሕ ወርቅ እንኳ እሷን መግዛት አይቻልም። 20  ታዲያ ጥበብ ከየት ትመጣለች?ማስተዋል የሚገኘውስ ከየት ነው?+ 21  ከሕያዋን ፍጥረታት ሁሉ ዓይን ተሰውራለች፤+በሰማያት ከሚበርሩ ወፎችም ተሸሽጋለች። 22  ጥፋትና ሞት፣‘ወሬዋን ብቻ በጆሯችን ሰምተናል’ ይላሉ። 23  ወደ እሷ የሚወስደውን መንገድ የሚረዳው አምላክ ነው፤መኖሪያዋን የሚያውቀው እሱ ብቻ ነው፤+ 24  እሱ እስከ ምድር ዳርቻ ይመለከታልና፤ከሰማያትም በታች ያለውን ሁሉ ያያል።+ 25  የነፋስን ኃይል* በወሰነ ጊዜ፣+ውኃዎችንም በለካ ጊዜ፣+ 26  ለዝናብ ሥርዓትን ባወጣ ጊዜ፣+ነጎድጓድ ለቀላቀለ ጥቁር ደመና መንገድን ባዘጋጀ ጊዜ፣+ 27  ያኔ ጥበብን አያት፤ ደግሞም ገለጻት፤መሠረታት፤ እንዲሁም መረመራት። 28  ሰውንም እንዲህ አለው፦ ‘እነሆ፣ ይሖዋን መፍራት ጥበብ ነው፤+ከክፉም መራቅ ማስተዋል ነው።’”+

የግርጌ ማስታወሻ

ቃል በቃል “(ከዓለት) ይፈስሳል።”
ቃል በቃል “ድንጋይ።”
ማዕድን የማውጣት ሥራን የሚያመለክት ይመስላል።
ወይም “ከጠራ።”
ይህ ቃል የገባው ማዕድኑን ለማመልከት ነው።
ወይም “የኩሽ።”
ቃል በቃል “ክብደት።”