ኢዮብ 35:1-16

  • ኤሊሁ፣ ኢዮብ ያቀረበው ሐሳብ የተሳሳተ መሆኑን ጠቆመ (1-16)

    • ኢዮብ ከአምላክ ይበልጥ ጻድቅ እንደሆነ ተናግሯል (2)

    • አምላክ እጅግ ከፍ ያለ በመሆኑ ሰው የሚሠራው ኃጢአት ሊጎዳው አይችልም (5, 6)

    • ኢዮብ አምላክን መጠባበቅ አለበት (14)

35  ኤሊሁ እንዲህ ሲል መልስ መስጠቱን ቀጠለ፦   “ትክክል እንደሆንክ በጣም እርግጠኛ ከመሆንህ የተነሳ‘እኔ ከአምላክ ይበልጥ ጻድቅ ነኝ’ ትላለህ?+   ደግሞም ‘ይህ ለአንተ* ምን ለውጥ ያመጣል? ኃጢአት ብሠራ ኖሮ ከዚህ የከፋ ነገር ይደርስብኝ ነበር?’ ብለሃልና።+   ለአንተና አብረውህ ላሉት ወዳጆችህ፣+መልስ እሰጣለሁ።   ቀና ብለህ ወደ ሰማይ እይ፤ከአንተ ከፍ ያሉትን ደመናት በጥሞና ተመልከት።+   ኃጢአት ብትሠራ እሱን ምን ትጎዳዋለህ?+ በደልህ ቢበዛ እሱን ምን ታደርገዋለህ?+   ጻድቅ ብትሆን ለእሱ ምን ትጨምርለታለህ?ከአንተ እጅ ምን ይቀበላል?+   ክፋት ብትሠራ የምትጎዳው እንደ አንተ ያለውን ሰው ብቻ ነው፤ጽድቅህም የሚጠቅመው የሰውን ልጅ ነው።   ሰዎች ከባድ ጭቆና ሲደርስባቸው ይጮኻሉ፤ከኃያል ሰው የሥልጣን ቀንበር* ለመገላገል ይጮኻሉ።+ 10  ይሁንና ‘በሌሊት መዝሙር እንዲዘመር የሚያደርገው፣+ታላቅ ፈጣሪዬ የሆነው አምላክ የት አለ?’ የሚል የለም።+ 11  ከምድር እንስሳት+ ይበልጥ እኛን ያስተምረናል፤+በሰማይ ከሚበርሩ ወፎችም በላይ ጥበበኞች አድርጎናል። 12  በክፉዎች ኩራት የተነሳ ሰዎች ይጮኻሉ፤ሆኖም እሱ አይመልስላቸውም።+ 13  በእርግጥ አምላክ ከንቱ ጩኸት* አይሰማም፤+ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ ትኩረት አይሰጠውም። 14  አላየሁትም ብለህ ቅሬታ እያሰማህ፣ አንተንማ እንዴት ይስማህ!+ ጉዳይህ በእሱ ፊት ነው፤ ስለዚህ እሱን በትዕግሥት ተጠባበቅ።+ 15  ተቆጥቶ ተጠያቂ አላደረገህምና፤በችኮላ ያደረግከውንም አልያዘብህም።+ 16  ኢዮብ አፉን የሚከፍተው በከንቱ ነው፤እውቀት ሳይኖረው ብዙ ይናገራል።”+

የግርጌ ማስታወሻ

አምላክን የሚያመለክት ሳይሆን አይቀርም።
ቃል በቃል “ክንድ።”
ወይም “ውሸት።”