ኢዮብ 37:1-24
37 “ከዚህም የተነሳ ልቤ ይመታል፤ከስፍራውም ይዘላል።
2 የድምፁን ጉምጉምታ፣ከአፉም የሚወጣውን ነጎድጓድ በጥሞና ስሙ።
3 ከሰማያት በታች ይልከዋል፤መብረቁንም እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ይሰደዋል።+
4 ከዚያም በኋላ ድምፅ ያስተጋባል፤ግርማ በተላበሰ ድምፅ ያንጎደጉዳል፤+ድምፁም በሚሰማበት ጊዜ አይከለክለውም።
5 አምላክ በሚያስደንቅ ሁኔታ በድምፁ ያንጎደጉዳል፤+እኛ መረዳት የማንችላቸውን ታላላቅ ነገሮች ያደርጋል።+
6 በረዶውን ‘ወደ መሬት ውረድ፣’+
ዶፉን ዝናብም ‘በኃይል ውረድ’ ይለዋልና።+
7 ሟች የሆነ ሰው ሁሉ ሥራውን እንዲያውቅ፣አምላክ የእያንዳንዱን ሰው ሥራ ያስቆማል።*
8 የዱር አራዊት ወደ ጎሬአቸው ይገባሉ፤በዋሻዎቻቸውም ውስጥ ይቀመጣሉ።
9 አውሎ ነፋስ ከማደሪያው ይነፍሳል፤+ቅዝቃዜም ከሰሜን ነፋሳት ይመጣል።+
10 በአምላክ እስትንፋስ በረዶ ይገኛል፤+የተንጣለሉትም ውኃዎች ግግር በረዶ ይሆናሉ።+
11 አዎ፣ ደመናትን እርጥበት ያሸክማቸዋል፤በደመናት መካከል መብረቁን ይበትናል፤+
12 እሱ በመራቸው አቅጣጫ ይሽከረከራሉ፤ሰዎች በሚኖሩበት* የምድር ገጽ ላይ እሱ ያዘዘውን ሁሉ ይፈጽማሉ።+
13 ለቅጣትም+ ሆነ* ለምድሩ ሲልአሊያም ታማኝ ፍቅር ለማሳየት ይህ እንዲሆን ያደርጋል።+
14 ኢዮብ ሆይ፣ ይህን ስማ፤ቆም ብለህ የአምላክን ድንቅ ሥራዎች በጥሞና አስብ።+
15 አምላክ ደመናትን እንዴት እንደሚቆጣጠር፣*ከደመናውም እንዴት መብረቅ እንደሚያበርቅ ታውቃለህ?
16 ደመናት እንዴት እንደሚንሳፈፉ ታውቃለህ?+
እነዚህ፣ እውቀቱ ፍጹም የሆነው አምላክ ድንቅ ሥራዎች ናቸው።+
17 ምድር በደቡብ ነፋስ ጸጥ ስትል፣ልብስህ የሚሞቀው ለምንድን ነው?+
18 እንደ ብረት መስተዋት ጠንካራ የሆኑትን ሰማያት፣ከእሱ ጋር ልትዘረጋ* ትችላለህ?+
19 ለእሱ የምንለውን ንገረን፤ጨለማ ውስጥ ስለሆን መልስ መስጠት አንችልም።
20 እኔ መናገር እንደምፈልግ ለእሱ ማሳወቅ ያስፈልጋል?
ወይስ እሱ ሊያውቀው የሚገባ ነገር የተናገረ ሰው አለ?+
21 በሰማይ ላይ ብርሃን ቢኖርም፣ነፋስ ነፍሶ ደመናቱን ካልበተነ፣ሰዎች ብርሃኑን* ማየት አይችሉም።
22 ከሰሜን ወርቃማ ጨረር ይወጣል፤የአምላክ ግርማ+ አስፈሪ ነው።
23 ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ ከመረዳት ችሎታችን በላይ ነው፤+ኃይሉ ታላቅ ነው፤+ደግሞም ፍትሑንና ታላቅ ጽድቁን አይጥስም።+
24 ስለዚህ ሰዎች ሊፈሩት ይገባል።+
ጠቢብ ነን ብለው ለሚያስቡ* ሁሉ ሞገስ አያሳይምና።”+