ኢዮብ 7:1-21

  • ኢዮብ መልስ መስጠቱን ቀጠለ (1-21)

    • ሕይወት እንደ ግዳጅ አገልግሎት ነው (1, 2)

    • “ዒላማህ ያደረግከኝ ለምንድን ነው?” (20)

7  “በምድር ላይ ያለ ሟች የሆነ ሰው ሕይወት፣ እንደ ግዳጅ አገልግሎት አይደለም?የሕይወት ዘመኑስ እንደ ቅጥር ሠራተኛ ዘመን አይደለም?+   እንደ ባሪያ፣ ጥላ ለማግኘት ይመኛል፤እንደ ቅጥር ሠራተኛም ደሞዙን ለመቀበል በጉጉት ይጠባበቃል።+   እኔም ከንቱ የሆኑ ወራት ተመድበውልኛል፤በሥቃይ የተሞሉ ሌሊቶችም ተወስነውልኛል።+   በተኛሁ ጊዜ ‘የምነሳው መቼ ነው?’ እላለሁ።+ ሌሊቱም ሲረዝም ጎህ እስኪቀድ* ድረስ ያለእረፍት እገላበጣለሁ።   ሥጋዬ ትልና የአፈር ጓል ለብሷል፤+ቆዳዬ በሙሉ አፈክፍኳል፤ ደግሞም መግል ይዟል።+   ዘመኔ ከሸማኔ መወርወሪያ ይበልጥ በፍጥነት ያልፋል፤+ያላንዳች ተስፋም ወደ ፍጻሜ ይደርሳል።+   ሕይወቴ ነፋስ እንደሆነ፣+ዓይኔም ዳግመኛ ደስታ* እንደማያይ አስታውስ።   አሁን የሚያየኝ ዓይን ከእንግዲህ አያየኝም፤ዓይኖችህ እኔን ይፈልጋሉ፤ እኔ ግን አልኖርም።+   እንደሚበተንና እንደሚጠፋ ደመና፣ወደ መቃብር* የሚወርድም ተመልሶ አይወጣም።+ 10  ዳግመኛ ወደ ቤቱ አይመለስም፤ስፍራውም ከእንግዲህ ወዲህ አያውቀውም።+ 11  ስለዚህ እኔ ከመናገር ወደኋላ አልልም። ከመንፈሴ ጭንቀት የተነሳ እናገራለሁ፤በከባድ ምሬት* እሮሮ አሰማለሁ!+ 12  በእኔ ላይ ጠባቂ የምታቆመው፣እኔ ባሕር ነኝ ወይስ ግዙፍ የባሕር ፍጥረት? 13  ‘መኝታዬ ያጽናናኛል፣አልጋዬ ሥቃዬን ያቀልልኛል’ ባልኩ ጊዜ፣ 14  አንተ በሕልም ታሸብረኛለህ፤በራእይም ታስፈራራኛለህ፤ 15  ስለዚህ እኔ* መታፈንን፣አዎ፣ ከሰውነቴም* ይልቅ ሞትን መረጥኩ።+ 16  ሕይወቴን ተጸየፍኳት፤+ በሕይወት መቀጠል አልፈልግም። ዘመኔ እንደ እስትንፋስ+ ስለሆነ ተወት አድርገኝ። 17  ታስበው ዘንድ፣ትኩረት ትሰጠውም* ዘንድ ሟች የሆነ ሰው ምንድን ነው?+ 18  በየማለዳው የምትመረምረው፣በየጊዜውም የምትፈትነው ለምንድን ነው?+ 19  ዓይንህን ከእኔ ላይ አታነሳም?ምራቄን እስክውጥስ ድረስ ፋታ አትሰጠኝም?*+ 20  የሰውን ልጅ የምትከታተል ሆይ፣+ ኃጢአት ብሠራ እንኳ አንተን እንዴት ልጎዳህ እችላለሁ? ዒላማህ ያደረግከኝ ለምንድን ነው? ሸክም ሆኜብሃለሁ? 21  መተላለፌን ይቅር የማትለው፣በደሌንም በምሕረት የማታልፈው ለምንድን ነው? ከጥቂት ጊዜ በኋላ አፈር ውስጥ እጋደማለሁና፤+አንተም ትፈልገኛለህ፤ እኔ ግን አልገኝም።”

የግርጌ ማስታወሻ

ወይም “እስከ ማለዳ ወጋገን።”
ቃል በቃል “መልካም ነገር።”
ወይም “ሲኦል።” የሰው ልጆችን ሁሉ መቃብር ያመለክታል። የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
ወይም “በነፍሴ ምሬት።”
ወይም “ነፍሴ . . . መረጠች።”
ቃል በቃል “ከአጥንቶቼም።”
ቃል በቃል “ልብህን ታኖርበትም።”
ለአጭር ጊዜ እንኳ የማትተወኝ ለምንድን ነው? ማለት ነው።