ኤርምያስ 24:1-10
-
ጥሩ በለሶችና መጥፎ በለሶች (1-10)
24 ከዚያም ይሖዋ በለስ የያዙ ሁለት ቅርጫቶችን በይሖዋ ቤተ መቅደስ ፊት ለፊት ተቀምጠው አሳየኝ፤ ይህም የሆነው የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር* የይሁዳን ንጉሥ የኢዮዓቄምን ልጅ+ ኢኮንያንን፣*+ ከይሁዳ መኳንንት፣ ከእጅ ጥበብ ባለሙያዎቹና ከአንጥረኞቹ* ጋር ከኢየሩሳሌም ወደ ባቢሎን በግዞት ከወሰዳቸው በኋላ ነው።+
2 በአንደኛው ቅርጫት ውስጥ ያሉት በለሶች በመጀመሪያው ወቅት ላይ እንደሚደርሱ በለሶች ጥሩ ዓይነት ነበሩ፤ በሌላኛው ቅርጫት ውስጥ ያሉት በለሶች ደግሞ መጥፎ ዓይነት ነበሩ፤ በጣም መጥፎ ከመሆናቸው የተነሳም ሊበሉ የሚችሉ አልነበሩም።
3 ከዚያም ይሖዋ “ኤርምያስ፣ የምታየው ምንድን ነው?” ሲል ጠየቀኝ። እኔም እንዲህ አልኩ፦ “የበለስ ፍሬዎችን አያለሁ፤ ጥሩዎቹ በለሶች በጣም ጥሩ ዓይነት ናቸው፤ መጥፎዎቹ ደግሞ በጣም መጥፎ ዓይነት ናቸው፤ ከመጥፎነታቸውም የተነሳ ሊበሉ አይችሉም።”+
4 ከዚያም የይሖዋ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፦
5 “የእስራኤል አምላክ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ከዚህ ስፍራ ወደ ከለዳውያን ምድር የሰደድኳቸውን የይሁዳ ግዞተኞች እንደነዚህ ጥሩ ዓይነት በለሶች በጥሩ ዓይን እመለከታቸዋለሁ።
6 መልካም ነገር አደርግላቸው ዘንድ ዓይኔን በእነሱ ላይ አኖራለሁ፤ ወደዚህችም ምድር እንዲመለሱ አደርጋለሁ።+ እገነባቸዋለሁ እንጂ አላፈርሳቸውም፤ እተክላቸዋለሁ እንጂ አልነቅላቸውም።+
7 እኔ ይሖዋ መሆኔን እንዲያውቁም ልብ እሰጣቸዋለሁ።+ በሙሉ ልባቸው ወደ እኔ ስለሚመለሱ+ ሕዝቤ ይሆናሉ፤ እኔም አምላካቸው እሆናለሁ።+
8 “‘ይሁንና ከመጥፎነታቸው የተነሳ ሊበሉ የማይችሉትን መጥፎ በለሶች+ በተመለከተ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስን፣+ መኳንንቱን፣ በዚህች ምድር ላይ የሚቀሩትን የኢየሩሳሌም ቀሪዎችና በግብፅ ምድር የሚኖሩትን በዚሁ ዓይን እመለከታቸዋለሁ።+
9 ለምድር መንግሥታት ሁሉ መቀጣጫ እንዲሆኑ ጥፋት አመጣባቸዋለሁ፤+ በምበትናቸው ቦታም ሁሉ+ ነቀፋ እንዲደርስባቸው፣ መተረቻ እንዲሆኑ፣ እንዲፌዝባቸውና እንዲረገሙ አደርጋለሁ።+
10 ለእነሱና ለአባቶቻቸው ከሰጠኋት ምድር ላይ እስኪጠፉ ድረስ በእነሱ ላይ ሰይፍ፣+ ረሃብና ቸነፈር* እሰዳለሁ።”’”+