ኤርምያስ 45:1-5

  • ይሖዋ ለባሮክ ያስተላለፈው መልእክት (1-5)

45  የኢዮስያስ ልጅ፣ የይሁዳ ንጉሥ ኢዮዓቄም በነገሠ በአራተኛው ዓመት፣+ የነሪያህ ልጅ ባሮክ+ ይህን ቃል ከኤርምያስ አፍ እየሰማ በመጽሐፍ በጻፈበት ጊዜ፣+ ነቢዩ ኤርምያስ ለባሮክ የተናገረው ቃል ይህ ነው፦  “ባሮክ፣ የእስራኤል አምላክ ይሖዋ አንተን በተመለከተ እንዲህ ይላል፦  ‘አንተ “ወዮልኝ፣ ይሖዋ በሥቃዬ ላይ ሐዘን ጨምሮብኛልና! ከማሰማው ሲቃ የተነሳ ዝያለሁ፤ ማረፊያ ቦታም አላገኘሁም” ብለሃል።’  “እሱን እንዲህ በለው፦ ‘ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ የገነባሁትን አፈርሳለሁ፤ የተከልኩትንም እነቅላለሁ፤ ምድሪቱን በሙሉ አወድማለሁ።+  አንተ ግን ለራስህ ታላላቅ ነገሮችን ትፈልጋለህ።* እንዲህ ያሉ ነገሮችን ፈጽሞ አትፈልግ።”’* “‘በሥጋ ለባሽ* ሁሉ ላይ ጥፋት ላመጣ ነውና’+ ይላል ይሖዋ፤ ‘በምትሄድበትም ቦታ ሁሉ ሕይወትህን* እንደ ምርኮ አድርጌ እሰጥሃለሁ።’”*+

የግርጌ ማስታወሻ

ወይም “ታላላቅ ነገሮች አገኛለሁ ብለህ ትጠብቃለህ።”
ወይም “መፈለግህን ተው።”
ወይም “በሰዎች።”
ወይም “ነፍስህን።”
ወይም “ሕይወትህ እንዲተርፍ አደርጋለሁ።”