ኤርምያስ 47:1-7
-
በፍልስጤማውያን ላይ የተነገረ ትንቢት (1-7)
47 ፈርዖን ጋዛን ከመውጋቱ በፊት ፍልስጤማውያንን+ በተመለከተ ወደ ነቢዩ ኤርምያስ የመጣው የይሖዋ ቃል ይህ ነው።
2 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦
“እነሆ፣ ከሰሜን ውኃ እየመጣ ነው።
የሚያጥለቀልቅም ወንዝ ይሆናል።
ምድሪቱንና በውስጧ ያሉትን ሁሉ፣ከተማዋንና ነዋሪዎቿን ያጥለቀልቃል።
ሰዎቹ ይጮኻሉ፤በምድሪቱም የሚኖሩ ሁሉ ዋይ ዋይ ይላሉ።
3 ከድንጉላ ፈረሶቹ ኃይለኛ የኮቴ ድምፅ፣ከሚንገጫገጩት የጦር ሠረገሎቹ ድምፅናከመንኮራኩሮቹ* የማያባራ ድምፅ የተነሳአባቶች እጃቸው ስለሚዝልልጆቻቸውን ለመርዳት እንኳ ወደ ኋላ አይዞሩም፤
4 ምክንያቱም የሚመጣው ቀን ፍልስጤማውያንን+ ሁሉ ያጠፋል፤በሕይወት ተርፈው ጢሮስንና+ ሲዶናን+ የሚረዱትን ሁሉ ያስወግዳል።
ይሖዋ ፍልስጤማውያንንይኸውም ከካፍቶር*+ ደሴት የመጡ ቀሪዎችን ያጠፋልና።
5 ጋዛ ትመለጣለች።*
አስቀሎን ጸጥ ትላለች።+
ሸለቋሟ በሆነው ሜዳቸው* የምትኖሩ ቀሪዎች ሆይ፣ሰውነታችሁን የምትቆርጡት እስከ መቼ ነው?+
6 አንተ የይሖዋ ሰይፍ!+
የማታርፈው እስከ መቼ ነው?
ወደ ሰገባህ ግባ።
እረፍ፤ ጸጥ ብለህም ተቀመጥ።
7 ይሖዋ ትእዛዝ ሰጥቶት እያለእንዴት አርፎ ሊቀመጥ ይችላል?
ትእዛዝ የተሰጠው በአስቀሎንና በባሕሩ ዳርቻ ላይ ነው፤+በዚያ መድቦታል።”