ኤርምያስ 6:1-30

  • ኢየሩሳሌም የምትከበብበት ጊዜ ተቃረበ (1-9)

  • የይሖዋ ቁጣ በኢየሩሳሌም ላይ ነደደ (10-21)

    • ‘ሰላም ሳይኖር “ሰላም ነው!” ይላሉ’ (14)

  • ከሰሜን ምድር ጨካኝ ወራሪዎች ይመጣሉ (22-26)

  • ኤርምያስ ብረትን እንደሚፈትን ሰው ሆኖ ያገለግላል (27-30)

6  እናንተ የቢንያም ልጆች፣ ተሸሸጉ፤ ከኢየሩሳሌም ወጥታችሁ ሽሹ። በተቆአ+ ቀንደ መለከት ንፉ፤+በቤትሃኬሬም እሳት በማንደድ ምልክት አሳዩ! ከሰሜን ጥፋት፣ ይኸውም ታላቅ መዓት እያንዣበበ ነውና።+   የጽዮን ሴት ልጅ ያማረችና ቅምጥል ሴት ትመስላለች።+   እረኞችና መንጎቻቸው ይመጣሉ። በዙሪያዋም ድንኳኖቻቸውን ይተክሉባታል፤+እያንዳንዳቸውም የሚጠብቋቸውን መንጎች ያሰማራሉ።+   “በእሷ ላይ ጦርነት ለማወጅ ተዘጋጁ!* ተነሱ፣ እኩለ ቀን ላይ ጥቃት እንሰንዝርባት!” “ወዮልን፣ ቀኑ እየመሸ፣የምሽቱም ጥላ እየረዘመ ነውና!”   “ተነሱ፣ በሌሊት ጥቃት እንሰንዝርባት፤የማይደፈሩትንም ማማዎቿን እንደምስስ።”+   የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦ “እንጨት ቁረጡ፤ በኢየሩሳሌም ዙሪያም የአፈር ቁልል ደልድሉ።+ ይህች ከተማ ተጠያቂ ልትሆን ይገባል፤በውስጧ ከግፍ በቀር ምንም አይገኝም።+   የውኃ ጉድጓድ ውኃውን እንደቀዘቀዘ እንደሚያቆይ፣እሷም ክፋቷን እንዳለ ጠብቃ አቆይታለች። ዓመፅና ጥፋት በውስጧ ይሰማል፤+ሕመምና ደዌ ምንጊዜም በፊቴ ናቸው።   ኢየሩሳሌም ሆይ፣ ተጸይፌሽ ከአንቺ እንዳልርቅ* ተጠንቀቂ፤+ባድማና ሰው የማይኖርበት ምድር አደርግሻለሁ።”+   የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “የእስራኤልን ቀሪዎች በወይን ተክል ላይ እንደቀሩ የመጨረሻ የወይን ፍሬዎች ምንም ሳያስቀሩ ይቃርሟቸዋል። ከወይን ተክሎች ላይ የወይን ፍሬዎች እንደሚለቅም ሰው በድጋሚ እጅህን ዘርጋ።” 10  “ለማን ልናገር? ማንን ላስጠንቅቅ? ማንስ ይሰማል? እነሆ፣ ጆሮዎቻቸው ስለተዘጉ* ማዳመጥ አይችሉም።+ እነሆ፣ የይሖዋን ቃል መሳለቂያ አድርገውታል፤+ቃሉም ደስ አያሰኛቸውም። 11  በመሆኑም በይሖዋ ቁጣ ተሞልቻለሁ፤በውስጤ አፍኜ ስለያዝኩት ዝያለሁ።”+ “በጎዳና ባለ ልጅ፣ተሰብስበው ባሉ ወጣቶች ላይ አፍስሰው።+ ባልም ሆነ ሚስቱ፣አረጋውያኑም ሆኑ ያረጁት* ይያዛሉ።+ 12  ቤቶቻቸው፣ እርሻዎቻቸውና ሚስቶቻቸውለሌሎች ይሰጣሉ።+ እጄን በምድሪቱ ነዋሪዎች ላይ እዘረጋለሁና” ይላል ይሖዋ። 13  “ከትንሹ አንስቶ እስከ ትልቁ ድረስ እያንዳንዱ አግባብ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት ይሯሯጣል፤+ከነቢዩ አንስቶ እስከ ካህኑ ድረስ ሁሉም ያጭበረብራል።+ 14  ሰላም ሳይኖር፣‘ሰላም ነው! ሰላም ነው!’ እያሉ የሕዝቤን ስብራት* ላይ ላዩን* ለመጠገን ይሞክራሉ።+ 15  በፈጸሙት አስጸያፊ ተግባር ኀፍረት ተሰምቷቸዋል? እነሱ እንደሆነ ጨርሶ ኀፍረት አይሰማቸውም! ውርደት ምን ማለት እንደሆነ እንኳ አያውቁም!+ ስለዚህ ከወደቁት ጋር ይወድቃሉ። እነሱን በምቀጣበት ጊዜ ይሰናከላሉ” ይላል ይሖዋ። 16  ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “መስቀለኛ መንገዶቹ ላይ ቁሙና ተመልከቱ። ስለ ጥንቶቹ ጎዳናዎች፣መልካም የሆነው መንገድ የትኛው እንደሆነ ጠይቁ፤ በዚያም ሂዱ፤+እረፍትም አግኙ።”* እነሱ ግን “በዚያ አንሄድም” ይላሉ።+ 17  “እኔም በእናንተ ላይ ጠባቂዎችን ሾምኩ፤+ጠባቂዎቹም ‘የቀንደ መለከቱን ድምፅ በትኩረት አዳምጡ!’ አሉ”፤+ እነሱ ግን “አናዳምጥም” አሉ።+ 18  “ስለዚህ እናንተ ብሔራት፣ ስሙ! እናንተ ሰዎች ሆይ፣ምን እንደሚደርስባቸው እወቁ። 19  ምድር ሆይ፣ ስሚ! በእነዚህ ሰዎች ላይ የገዛ ውጥናቸውን ፍሬ፣ጥፋትን አመጣባቸዋለሁ፤+እነሱ ለቃሌ ምንም ትኩረት አልሰጡምና፤ሕጌንም* አልተቀበሉም።” 20  “ነጭ ዕጣን ከሳባ፣ጠጅ ሣር* ከሩቅ አገር ብታመጡልኝ ምን ይጠቅመኛል? ሙሉ በሙሉ የሚቃጠል መባችሁን አልቀበልም፤መሥዋዕቶቻችሁም ደስ አያሰኙኝም።”+ 21  ስለዚህ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “በዚህ ሕዝብ ፊት መሰናክል አስቀምጣለሁ፤አባቶችም ሆኑ ልጆች፣ጎረቤትም ሆነ ባልንጀራውበአንድነት ይሰናከላሉ፤ሁሉም ይጠፋሉ።”+ 22  ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፣ ከሰሜን ምድር አንድ ሕዝብ እየመጣ ነው፤ከምድር ዳርቻም ታላቅ ብሔር ይነሳል።+ 23  ቀስትና ጦር ይይዛሉ። ጨካኝና ምሕረት የለሽ ናቸው። ድምፃቸው እንደ ባሕር ያስተጋባል፤ፈረሶችንም ይጋልባሉ።+ የጽዮን ሴት ልጅ ሆይ፣ ልክ እንደ ተዋጊ በአንቺ ላይ ይሰለፋሉ።” 24  ወሬውን ሰምተናል። እጆቻችንም ዝለዋል፤+በጭንቀት ተውጠናል፤ልትወልድ እንደተቃረበች ሴት ሥቃይ ቀስፎናል።*+ 25  ወደ ውጭ አትውጡ፤በመንገዱም ላይ አትዘዋወሩ፤ጠላት ሰይፍ ታጥቋልና፤በየቦታውም ሽብር ነግሦአል። 26  የሕዝቤ ሴት ልጅ ሆይ፣ማቅ ልበሺ፤+ በአመድም ላይ ተንከባለዪ። አንድ ልጁን እንዳጣ ሰው መራራ ለቅሶ አልቅሺ፤+አጥፊው በእኛ ላይ በድንገት ይመጣልና።+ 27  “አንተን* በሕዝቤ መካከል ብረትን እንደሚፈትን፣በጥንቃቄም እንደሚመረምር ሰው አድርጌሃለሁ፤አንተም ልብ በል፤ መንገዳቸውንም መርምር። 28  ሁሉም በጣም ግትር ናቸው፤+እየዞሩ ስም ያጠፋሉ።+ እንደ መዳብና ብረት ናቸው፤ሁሉም ምግባረ ብልሹዎች ናቸው። 29  ወናፎቹ በእሳት ተቃጠሉ። ከእሳቱም የሚወጣው እርሳስ ነው። አንጥረኛ በደንብ የሚያጣራው እንዲያው በከንቱ ነው፤+መጥፎዎቹም ተለይተው አልወጡም።+ 30  ሰዎች ‘የተጣለ ብር’ ብለው ይጠሯቸዋል፤ይሖዋ ጥሏቸዋልና።”+

የግርጌ ማስታወሻ

ቃል በቃል “ጦርነት ቀድሱ።”
ወይም “ነፍሴ ተጸይፋሽ ከአንቺ እንዳትርቅ።”
ቃል በቃል “ጆሯቸው ስላልተገረዘ።”
ቃል በቃል “ቀናት የጠገቡት።”
ወይም “እንደነገሩ።”
ወይም “ስንጥቅ።”
ወይም “ነፍሳችሁም እረፍት ታግኝ።”
ወይም “መመሪያዬንም፤ ትምህርቴንም።”
ኢሳ 43:24 ላይ የሚገኘውን የግርጌ ማስታወሻ ተመልከት።
ቃል በቃል “ምጥ ይዞናል።”
ነቢዩ ኤርምያስን ያመለክታል።