ለኤፌሶን ሰዎች የተጻፈ ደብዳቤ 3:1-21

  • ቅዱሱ ሚስጥር (1-13)

    • አሕዛብ ከክርስቶስ ጋር አብረው ወራሾች ይሆናሉ (6)

    • ‘የአምላክ ዘላለማዊ ዓላማ’ (11)

  • የኤፌሶን ክርስቲያኖች ማስተዋል እንዲያገኙ የቀረበ ጸሎት (14-21)

3  በዚህ ምክንያት እኔ ጳውሎስ ከአሕዛብ ወገን ለሆናችሁት ለእናንተ ስል የክርስቶስ ኢየሱስ እስረኛ ሆኛለሁ።+  ለእናንተ ጥቅም ሲባል ስለተሰጠኝ የአምላክ ጸጋ መጋቢነት+ በእርግጥ ሰምታችኋል፤  ቀደም ሲል በአጭሩ እንደጻፍኩት ቅዱሱ ሚስጥር ተገልጦልኛል።  በመሆኑም ይህን ስታነቡ ስለ ክርስቶስ ቅዱስ ሚስጥር+ ያለኝን ግንዛቤ መረዳት ትችላላችሁ።  ይህ ሚስጥር አሁን ለቅዱሳን ሐዋርያትና ነቢያት በመንፈስ እንደተገለጠው ባለፉት ትውልዶች ለነበሩ የሰው ልጆች አልተገለጠም ነበር።+  ሚስጥሩ ይህ ነው፦ ከአሕዛብ ወገን የሆኑ ሰዎች ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር አንድ በመሆን በምሥራቹ አማካኝነት አብረው ወራሾች፣ የአንድ አካል ክፍሎችና+ ከእኛ ጋር የተስፋው ተካፋዮች ይሆናሉ።  አምላክ የኃይሉ መግለጫ አድርጎ በሰጠኝ ነፃ ስጦታ ይኸውም በጸጋው አማካኝነት የዚህ ሚስጥር አገልጋይ ሆኛለሁ።+  ከቅዱሳን ሁሉ ለማንስ+ ለእኔ ይህ ጸጋ ተሰጠኝ፤+ ይህም ሊደረስበት ስለማይችለው የክርስቶስ ብልጽግና የሚገልጸውን ምሥራች ለአሕዛብ እንዳውጅ  እንዲሁም ሁሉን ነገር የፈጠረው አምላክ ለብዙ ዘመናት ሰውሮት የቆየው ቅዱሱ ሚስጥር ሥራ ላይ የዋለበትን መንገድ ሰዎች ሁሉ እንዲያስተውሉ እረዳቸው ዘንድ ነው።+ 10  ይህ የሆነው በርካታ ገጽታዎች ያሉት የአምላክ ጥበብ በሰማያዊ ስፍራ ላሉት መስተዳድሮችና ባለሥልጣናት አሁን በጉባኤው አማካኝነት ግልጽ ይሆን ዘንድ ነው።+ 11  ይህም አምላክ ከጌታችን ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር በተያያዘ ባዘጋጀው ዘላለማዊ ዓላማ መሠረት ነው፤+ 12  በእሱም አማካኝነት ይህ የመናገር ነፃነት አለን፤ በክርስቶስ ላይ ባለን እምነት አማካኝነትም በልበ ሙሉነት ወደ አምላክ በነፃነት መቅረብ እንችላለን።+ 13  ስለዚህ ለእናንተ ስል እየደረሰብኝ ባለው መከራ የተነሳ ተስፋ እንዳትቆርጡ አደራ እላችኋለሁ፤ ይህ ለእናንተ ክብር ነውና።+ 14  በዚህም ምክንያት በአብ ፊት ለመጸለይ እንበረከካለሁ፤ 15  በሰማይና በምድር ያለ እያንዳንዱ ቤተሰብ ስያሜውን ያገኘው ከእሱ ነው። 16  እሱ ታላቅ ክብር ያለው እንደመሆኑ መጠን ውስጣዊውን ሰውነታችሁን የሚያጠነክር ኃይል+ በመንፈሱ አማካኝነት እንዲሰጣችሁ እጸልያለሁ፤ 17  ደግሞም በእምነታችሁ አማካኝነት ክርስቶስ ከፍቅር+ ጋር በልባችሁ ውስጥ እንዲያድር እጸልያለሁ። ሥር እንድትሰዱና+ በመሠረቱ ላይ እንድትታነጹ+ ያስችላችሁ ዘንድ እለምናለሁ፤ 18  ይህም ስፋቱ፣ ርዝመቱ፣ ከፍታውና ጥልቀቱ ምን ያህል እንደሆነ ከቅዱሳን ሁሉ ጋር በሚገባ መረዳት እንድትችሉ 19  እንዲሁም አምላክ በሚሰጠው ሙላት ሁሉ ትሞሉ ዘንድ ከእውቀት በላይ የሆነውን የክርስቶስ ፍቅር እንድታውቁ ነው።+ 20  እንግዲህ በእኛ ውስጥ ከሚሠራው ኃይሉ ጋር በሚስማማ ሁኔታ፣+ ከምንጠይቀው ወይም ከምናስበው ሁሉ በላይ እጅግ አብልጦ ማድረግ ለሚችለው+ 21  ለእሱ በጉባኤው አማካኝነትና በክርስቶስ ኢየሱስ አማካኝነት በትውልዶች ሁሉ ለዘላለም ክብር ይሁን። አሜን።

የግርጌ ማስታወሻ