ዕዝራ 2:1-70

  • ወደ አገራቸው የተመለሱት ግዞተኞች ዝርዝር (1-67)

    • የቤተ መቅደሱ አገልጋዮች (43-54)

    • የሰለሞን አገልጋዮች ወንዶች ልጆች (55-57)

  • ለቤተ መቅደሱ የቀረቡ የፈቃደኝነት መባዎች (68-70)

2  የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነጾር ወደ ባቢሎን በግዞት ወስዷቸው+ የነበሩትና ተማርከው በግዞት ከተወሰዱት+ መካከል ወጥተው በኋላ ላይ ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ ይኸውም ወደየከተሞቻቸው የተመለሱት የአውራጃው ነዋሪዎች እነዚህ ናቸው፤+  ከዘሩባቤል፣+ ከየሆሹዋ፣+ ከነህምያ፣ ከሰራያህ፣ ከረኤላያህ፣ ከመርዶክዮስ፣ ከቢልሻን፣ ከሚስጳር፣ ከቢግዋይ፣ ከረሁምና ከባአናህ ጋር የመጡት እነዚህ ናቸው። የእስራኤላውያን ወንዶች ቁጥር የሚከተሉትንም ይጨምራል፦+  የፓሮሽ ወንዶች ልጆች 2,172፣  የሰፋጥያህ ወንዶች ልጆች 372፣  የኤራ+ ወንዶች ልጆች 775፣  የየሹዋና የኢዮዓብ ወንዶች ልጆች የሆኑት የፓሃትሞአብ+ ወንዶች ልጆች 2,812፣  የኤላም ወንዶች ልጆች+ 1,254፣  የዛቱ ወንዶች ልጆች+ 945፣  የዛካይ ወንዶች ልጆች 760፣ 10  የባኒ ወንዶች ልጆች 642፣ 11  የቤባይ ወንዶች ልጆች 623፣ 12  የአዝጋድ ወንዶች ልጆች 1,222፣ 13  የአዶኒቃም ወንዶች ልጆች 666፣ 14  የቢግዋይ ወንዶች ልጆች 2,056፣ 15  የአዲን ወንዶች ልጆች 454፣ 16  የሕዝቅያስ ልጅ የአጤር ወንዶች ልጆች 98፣ 17  የቤጻይ ወንዶች ልጆች 323፣ 18  የዮራ ወንዶች ልጆች 112፣ 19  የሃሹም ወንዶች ልጆች+ 223፣ 20  የጊባር ወንዶች ልጆች 95፣ 21  የቤተልሔም ወንዶች ልጆች 123፣ 22  የነጦፋ ወንዶች ልጆች 56፣ 23  የአናቶት+ ሰዎች 128፣ 24  የአዝማዌት ወንዶች ልጆች 42፣ 25  የቂርያትየአሪም፣ የከፊራና የበኤሮት ወንዶች ልጆች 743፣ 26  የራማና+ የጌባ+ ወንዶች ልጆች 621፣ 27  የሚክማስ ሰዎች 122፣ 28  የቤቴልና የጋይ+ ሰዎች 223፣ 29  የነቦ ወንዶች ልጆች+ 52፣ 30  የማግቢሽ ወንዶች ልጆች 156፣ 31  የሌላኛው ኤላም ወንዶች ልጆች 1,254፣ 32  የሃሪም ወንዶች ልጆች 320፣ 33  የሎድ፣ የሃዲድና የኦኖ ወንዶች ልጆች 725፣ 34  የኢያሪኮ ወንዶች ልጆች 345፣ 35  የሰናአ ወንዶች ልጆች 3,630። 36  ካህናቱ+ የሚከተሉት ናቸው፦ ከየሹዋ+ ቤተሰብ የሆነው የየዳያህ+ ወንዶች ልጆች 973፣ 37  የኢሜር+ ወንዶች ልጆች 1,052፣ 38  የጳስኮር+ ወንዶች ልጆች 1,247፣ 39  የሃሪም+ ወንዶች ልጆች 1,017። 40  ሌዋውያኑ+ የሚከተሉት ናቸው፦ የሆዳውያህ ወንዶች ልጆች የሆኑት የየሹዋና የቃድሚኤል+ ወንዶች ልጆች 74። 41  ዘማሪዎቹ+ የአሳፍ+ ወንዶች ልጆች 128። 42  የበር ጠባቂዎቹ+ ወንዶች ልጆች የሆኑት የሻሉም ወንዶች ልጆች፣ የአጤር ወንዶች ልጆች፣ የታልሞን+ ወንዶች ልጆች፣ የአቁብ+ ወንዶች ልጆች፣ የሃጢጣ ወንዶች ልጆችና የሾባይ ወንዶች ልጆች በአጠቃላይ 139። 43  የቤተ መቅደሱ አገልጋዮች*+ የሚከተሉት ናቸው፦ የጺሃ ወንዶች ልጆች፣ የሃሱፋ ወንዶች ልጆች፣ የታባኦት ወንዶች ልጆች፣ 44  የቀሮስ ወንዶች ልጆች፣ የሲአ ወንዶች ልጆች፣ የፓዶን ወንዶች ልጆች፣ 45  የለባና ወንዶች ልጆች፣ የሃጋባ ወንዶች ልጆች፣ የአቁብ ወንዶች ልጆች፣ 46  የሃጋብ ወንዶች ልጆች፣ የሳልማይ ወንዶች ልጆች፣ የሃናን ወንዶች ልጆች፣ 47  የጊዴል ወንዶች ልጆች፣ የጋሃር ወንዶች ልጆች፣ የረአያህ ወንዶች ልጆች፣ 48  የረጺን ወንዶች ልጆች፣ የነቆዳ ወንዶች ልጆች፣ የጋዛም ወንዶች ልጆች፣ 49  የዑዛ ወንዶች ልጆች፣ የፓሰአህ ወንዶች ልጆች፣ የቤሳይ ወንዶች ልጆች፣ 50  የአስና ወንዶች ልጆች፣ የመኡኒም ወንዶች ልጆች፣ የነፉሲም ወንዶች ልጆች፣ 51  የባቅቡቅ ወንዶች ልጆች፣ የሃቁፋ ወንዶች ልጆች፣ የሃርሑር ወንዶች ልጆች፣ 52  የባጽሉት ወንዶች ልጆች፣ የመሂዳ ወንዶች ልጆች፣ የሃርሻ ወንዶች ልጆች፣ 53   የባርቆስ ወንዶች ልጆች፣ የሲሳራ ወንዶች ልጆች፣ የተማ ወንዶች ልጆች፣ 54  የነጺሃ ወንዶች ልጆችና የሃጢፋ ወንዶች ልጆች። 55  የሰለሞን አገልጋዮች ወንዶች ልጆች የሚከተሉት ናቸው፦ የሶጣይ ወንዶች ልጆች፣ የሶፈረት ወንዶች ልጆች፣ የፐሩዳ+ ወንዶች ልጆች፣ 56  የያላ ወንዶች ልጆች፣ የዳርቆን ወንዶች ልጆች፣ የጊዴል ወንዶች ልጆች፣ 57   የሰፋጥያህ ወንዶች ልጆች፣ የሃጢል ወንዶች ልጆች፣ የፖክሄሬትሃጸባይም ወንዶች ልጆችና የአሚ ወንዶች ልጆች። 58  የቤተ መቅደሱ አገልጋዮችና* የሰለሞን አገልጋዮች ወንዶች ልጆች በአጠቃላይ 392 ነበሩ። 59  ከቴልመላ፣ ከቴልሃርሻ፣ ከከሩብ፣ ከአዳንና ከኢሜር የወጡት ሆኖም ከየትኛው የአባቶች ቤትና የዘር ሐረግ እንደመጡ በውል መለየትም ሆነ እስራኤላዊ መሆን አለመሆናቸውን በትክክል ማረጋገጥ ያልቻሉት የሚከተሉት ናቸው፦+ 60  የደላያህ ወንዶች ልጆች፣ የጦብያ ወንዶች ልጆችና የነቆዳ ወንዶች ልጆች 652። 61  ከካህናቱ ወንዶች ልጆች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፦ የሃባያ ወንዶች ልጆች፣ የሃቆጽ+ ወንዶች ልጆች እንዲሁም ከጊልያዳዊው ከቤርዜሊ ሴቶች ልጆች መካከል አንዷን ያገባውና በስማቸው የተጠራው የቤርዜሊ+ ወንዶች ልጆች። 62  እነዚህ የዘር ሐረጋቸውን ለማረጋገጥ በመዝገቡ ላይ የቤተሰባቸውን ስም ለማግኘት ቢጥሩም ሊያገኙት አልቻሉም፤ በመሆኑም ከክህነት አገልግሎቱ ታገዱ።*+ 63  ገዢውም* በኡሪምና ቱሚም+ አማካኝነት ምክር የሚጠይቅ ካህን እስኪገኝ ድረስ እጅግ ቅዱስ ከሆኑት ነገሮች መብላት እንደማይችሉ ነገራቸው።+ 64  መላው ጉባኤ በአጠቃላይ 42,360 ነበር፤+ 65  ይህ 7,337 ወንድና ሴት ባሪያዎቻቸውን አይጨምርም፤ በተጨማሪም 200 ወንድና ሴት ዘማሪዎች ነበሯቸው። 66  ከዚህም ሌላ 736 ፈረሶች፣ 245 በቅሎዎች 67  እንዲሁም 435 ግመሎችና 6,720 አህዮች ነበሯቸው። 68  ከአባቶች ቤት መሪዎች መካከል አንዳንዶቹ ኢየሩሳሌም ወደነበረው ወደ ይሖዋ ቤት ሲደርሱ ቤቱን በቀድሞ ቦታው ላይ መልሶ ለመገንባት+ ለእውነተኛው አምላክ ቤት የፈቃደኝነት መባዎችን አቀረቡ።+ 69  እነሱም ለሥራው ማስኬጃ እንዲሆን እንደየአቅማቸው 61,000 የወርቅ ድራክማ፣* 5,000 የብር ምናን*+ እና 100 የካህናት ቀሚስ ለግምጃ ቤቱ ሰጡ። 70  ካህናቱ፣ ሌዋውያኑ፣ ከሕዝቡ መካከል አንዳንዶቹ፣ ዘማሪዎቹ፣ በር ጠባቂዎቹና የቤተ መቅደስ አገልጋዮቹ* በየከተሞቻቸው ሰፈሩ፤ የቀሩትም እስራኤላውያን በሙሉ በየከተሞቻቸው መኖር ጀመሩ።+

የግርጌ ማስታወሻ

ወይም “ናታኒሞቹ።” ቃል በቃል “የተሰጡ ሰዎች።”
ወይም “ናታኒሞቹ።” ቃል በቃል “የተሰጡ ሰዎች።”
ወይም “እንደረከሱ ተቆጥረው ከክህነት አገልግሎቱ ተገለሉ።”
ወይም “ቲርሻታው።” ለአንድ የአውራጃ ገዢ የሚሰጥ የፋርሳውያን የማዕረግ ስም ነው።
አብዛኛውን ጊዜ 8.4 ግራም ከሚመዝነው የፋርሳውያን የወርቅ ዳሪክ ጋር እኩል መጠን አለው። በግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት ላይ ከተጠቀሰው ድራክማ የተለየ ነው። ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።
በዕብራይስጥ ቅዱሳን መጻሕፍት ውስጥ አንድ ምናን 570 ግራም ነው። ከተጨማሪው መረጃ ላይ ለ14ን ተመልከት።
ወይም “ናታኒሞቹ።” ቃል በቃል “የተሰጡ ሰዎች።”