ዘሌዋውያን 16:1-34
-
የስርየት ቀን (1-34)
16 ሁለቱ የአሮን ወንዶች ልጆች ይሖዋ ፊት በመቅረባቸው የተነሳ ከሞቱ+ በኋላ ይሖዋ ሙሴን አነጋገረው።
2 ይሖዋም እንዲህ አለው፦ “እኔ ከመክደኛው በላይ+ በደመና ውስጥ+ ስለምገለጥ በመጋረጃው ውስጥ+ ወዳለው ቅዱስ ስፍራ+ ይኸውም በታቦቱ ላይ ወዳለው መክደኛ ፊት በፈለገው ጊዜ እንዳይገባና በዚህም የተነሳ እንዳይሞት+ ለወንድምህ ለአሮን ንገረው።
3 “አሮን ወደተቀደሰው ስፍራ በሚገባበት ጊዜ ለኃጢአት መባ የሚሆን አንድ ወይፈንና+ ለሚቃጠል መባ የሚሆን አንድ አውራ በግ+ ይዞ ይምጣ።
4 ቅዱሱን የበፍታ ቀሚስ+ ይልበስ፤ በበፍታ ቁምጣዎቹም+ ሰውነቱን ይሸፍን፤ የበፍታ መቀነቱንም+ ይታጠቅ፤ ራሱም ላይ የበፍታ ጥምጥሙን+ ይጠምጥም። እነዚህ ቅዱስ ልብሶች+ ናቸው። እሱም ገላውን በውኃ ታጥቦ+ ይለብሳቸዋል።
5 “ከእስራኤል ማኅበረሰብም ሁለት ተባዕት የፍየል ጠቦቶችን ለኃጢአት መባ፣ አንድ አውራ በግ ደግሞ ለሚቃጠል መባ ይውሰድ።+
6 “ከዚያም አሮን ለራሱ የኃጢአት መባ የሚሆነውን ወይፈን ያቅርብ፤ ለራሱም+ ሆነ ለቤቱ ያስተሰርያል።
7 “ሁለቱን ፍየሎች ወስዶ በመገናኛ ድንኳኑ መግቢያ በይሖዋ ፊት እንዲቆሙ ያደርጋል።
8 አሮንም በሁለቱ ፍየሎች ላይ ዕጣ ይጥላል፤ አንደኛው ዕጣ ለይሖዋ ሌላኛው ዕጣ ደግሞ ለአዛዜል* ይሆናል።
9 አሮንም ለይሖዋ እንዲሆን ዕጣ+ የወጣበትን ፍየል ያቀርባል፤ የኃጢአትም መባ ያደርገዋል።
10 ለአዛዜል እንዲሆን ዕጣ የወጣበት ፍየል ግን በእሱ አማካኝነት ስርየት እንዲፈጸምበት ከነሕይወቱ መጥቶ በይሖዋ ፊት እንዲቆም ይደረግ፤ ከዚያም ለአዛዜል እንዲሆን ወደ ምድረ በዳ ይለቀቃል።+
11 “አሮንም ለራሱ የኃጢአት መባ የሚሆነውን ወይፈን ያቀርባል፤ ለራሱም ሆነ ለቤቱ ያስተሰርያል፤ ከዚያም ለራሱ የኃጢአት መባ የሚሆነውን ወይፈን ያርዳል።+
12 “በይሖዋ ፊት ካለው መሠዊያ ላይ የተወሰደ ፍም+ የሞላበትን ዕጣን ማጨሻና+ ሁለት እፍኝ ሙሉ ጥሩ መዓዛ ያለው ዕጣን+ ይወስዳል፤ እነዚህንም ይዞ ወደ መጋረጃው ውስጥ ይገባል።+
13 እንዳይሞትም ዕጣኑን በይሖዋ ፊት+ ባለው እሳት ላይ ይጨምረዋል፤ የዕጣኑም ጭስ ከምሥክሩ+ በላይ ያለውን የታቦቱን መክደኛ+ ይሸፍነዋል።
14 “ከወይፈኑም ደም+ የተወሰነውን ወስዶ ከመክደኛው ፊት ለፊት በስተ ምሥራቅ በኩል በጣቱ ይረጨዋል፤ የተወሰነውን ደም ደግሞ ከመክደኛው ፊት በጣቱ ሰባት ጊዜ ይረጨዋል።+
15 “ከዚያም ለሕዝቡ የኃጢአት መባ+ የሚሆነውን ፍየል ያርደዋል፤ ደሙንም ወደ መጋረጃው ውስጥ ይዞ በመግባት+ ልክ በወይፈኑ ደም+ እንዳደረገው በዚህኛውም ደም ያደርጋል፤ ደሙንም ወደ መክደኛውና በመክደኛው ፊት ይረጨዋል።
16 “እስራኤላውያን ስለፈጸሙት ርኩሰት፣ ስለ መተላለፋቸውና ስለ ኃጢአታቸው+ ለቅዱሱ ስፍራ ያስተሰርይ፤ በእነሱ ዘንድ በርኩሰታቸው መካከል ለሚገኘው ለመገናኛ ድንኳኑም ይህንኑ ያድርግ።
17 “ለማስተሰረይ ወደ ቅዱሱ ስፍራ ገብቶ እስኪወጣ ድረስ ሌላ ማንም ሰው በመገናኛ ድንኳኑ ውስጥ መገኘት የለበትም። እሱም ለራሱ፣ ለቤቱና+ ለመላው የእስራኤል ጉባኤ+ ያስተሰርያል።
18 “ከዚያም በይሖዋ ፊት ወዳለው መሠዊያ ይወጣል፤+ ለመሠዊያውም ያስተሰርይለታል፤ ከወይፈኑ ደም የተወሰነውን እንዲሁም ከፍየሉ ደም የተወሰነውን ወስዶ በመሠዊያው ጎኖች ሁሉ ላይ ያሉትን ቀንዶች ይቀባል።
19 በተጨማሪም ከደሙ የተወሰነውን ወስዶ በመሠዊያው ላይ በጣቱ ሰባት ጊዜ በመርጨት እስራኤላውያን ከፈጸሙት ርኩሰት ያነጻዋል እንዲሁም ይቀድሰዋል።
20 “ለቅዱሱ ስፍራ፣ ለመገናኛ ድንኳኑና ለመሠዊያው+ ካስተሰረየ+ በኋላ በሕይወት ያለውንም ፍየል ያቀርባል።+
21 ከዚያም አሮን ሁለቱንም እጆቹን በሕይወት ባለው ፍየል ራስ ላይ በመጫን እስራኤላውያን የሠሩትን ስህተት ሁሉ፣ መተላለፋቸውን ሁሉና ኃጢአታቸውን ሁሉ ይናዘዝበታል፤ እነዚህንም በፍየሉ ራስ ላይ ያደርጋል፤+ ፍየሉንም ለዚህ በተመደበው* ሰው እጅ ወደ ምድረ በዳ ይሰደዋል።
22 ፍየሉም ስህተቶቻቸውን በሙሉ ተሸክሞ+ ወደ በረሃ ይሄዳል፤+ እሱም ፍየሉን ወደ ምድረ በዳ ይሰደዋል።+
23 “ከዚያም አሮን ወደ መገናኛ ድንኳኑ ይገባል፤ ወደ ቅዱሱ ስፍራ ሲገባ ለብሷቸው የነበሩትንም የበፍታ ልብሶች ያወልቃል፤ ልብሶቹንም እዚያው ይተዋቸዋል።
24 ገላውንም በቅዱስ ስፍራ በውኃ ይታጠብ፤+ ልብሶቹንም ይልበስ፤+ ከዚያም ወጥቶ የራሱን የሚቃጠል መባ+ እንዲሁም የሕዝቡን የሚቃጠል መባ+ ያቀርባል፤ ለራሱና ለሕዝቡም ያስተሰርያል።+
25 የኃጢአት መባው ስብም በመሠዊያው ላይ እንዲጨስ ያደርጋል።
26 “ለአዛዜል+ ሲል ፍየሉን የለቀቀውም ሰው ልብሶቹን ይጠብ፤ ገላውንም በውኃ ይታጠብ፤ ከዚያም ወደ ሰፈሩ መግባት ይችላል።
27 “ደማቸው ለማስተሰረያ እንዲሆን ወደ ቅዱሱ ስፍራ የገባው የኃጢአት መባው ወይፈንና የኃጢአት መባው ፍየል ከሰፈሩ ውጭ ይወሰዳሉ፤ ቆዳቸው፣ ሥጋቸውና ፈርሳቸውም በእሳት ይቃጠላል።+
28 እነዚህን ያቃጠለው ሰው ልብሶቹን ይጠብ፤ ገላውንም በውኃ ይታጠብ፤ ከዚያም ወደ ሰፈሩ መግባት ይችላል።
29 “ይህም ለእናንተ ዘላቂ ደንብ ሆኖ ያገለግላል፦ በሰባተኛው ወር ከወሩም በአሥረኛው ቀን ራሳችሁን አጎሳቁሉ፤* ምንም ዓይነት ሥራም አትሥሩ፤+ የአገራችሁ ሰውም ሆነ በመካከላችሁ የሚኖር የባዕድ አገር ሰው ምንም ዓይነት ሥራ አይሥራ።
30 በዚህ ቀን፣ ንጹሕ መሆናችሁን ለማሳወቅ ለእናንተ ማስተሰረያ+ ይቀርባል። በይሖዋም ፊት ከኃጢአታችሁ ሁሉ ንጹሕ ትሆናላችሁ።+
31 ይህ ሙሉ በሙሉ የምታርፉበት ሰንበት ነው፤ እናንተም ራሳችሁን* አጎሳቁሉ።+ ይህም ዘላቂ ደንብ ነው።
32 “አባቱን ተክቶ+ በክህነት እንዲያገለግል የሚቀባውና የሚሾመው*+ ካህን ያስተሰርያል፤ እንዲሁም ቅዱስ የሆኑትን የበፍታ ልብሶች+ ይለብሳል።
33 ለቅዱሱ መቅደስ፣+ ለመገናኛ ድንኳኑና+ ለመሠዊያው+ ያስተሰርያል፤ እንዲሁም ለካህናቱና ለጉባኤው ሕዝብ በሙሉ ያስተሰርያል።+
34 ይህም የእስራኤላውያንን ኃጢአት በሙሉ በዓመት አንድ ጊዜ+ ለማስተሰረይ የሚያገለግል ዘላቂ ደንብ ይሆናል።”+
እሱም ልክ ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረት አደረገ።