ዘኁልቁ 2:1-34

  • ሦስት ነገዶችን ባቀፈ ምድብ ተከፋፍለው ይሰፍራሉ (1-34)

    • የይሁዳ ምድብ በስተ ምሥራቅ ይሰፍራል (3-9)

    • የሮቤል ምድብ በስተ ደቡብ ይሰፍራል (10-16)

    • ሌዊ መሃል ላይ ይሰፍራል (17)

    • የኤፍሬም ምድብ በስተ ምዕራብ ይሰፍራል (18-24)

    • የዳን ምድብ በስተ ሰሜን ይሰፍራል (25-31)

    • የተመዘገቡት ወንዶች ጠቅላላ ቁጥር (32-34)

2  ይሖዋ ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፦  “እስራኤላውያን ሦስት ነገዶችን ላቀፈው ምድባቸው+ በተሰጠው ቦታ ይስፈሩ፤ እያንዳንዱም ሰው ለአባቶቹ ቤት በቆመው ዓርማ* አጠገብ ይስፈር። ፊታቸውን ወደ መገናኛ ድንኳኑ አድርገው ዙሪያውን ይስፈሩ።  “በስተ ምሥራቅ ፀሐይ በምትወጣበት አቅጣጫ በየምድቡ* የሚሰፍረው ሦስት ነገዶችን ያቀፈው የይሁዳ ምድብ ይሆናል፤ የይሁዳ ልጆች አለቃ የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን+ ነው።  በሠራዊቱ ውስጥ የተመዘገቡትም 74,600 ናቸው።+  ከእሱም ቀጥሎ የሚሰፍረው የይሳኮር ነገድ ይሆናል፤ የይሳኮር ልጆች አለቃ የጹአር ልጅ ናትናኤል+ ነው።  በሠራዊቱ ውስጥ የተመዘገቡትም 54,400 ናቸው።+  ከዚያ ቀጥሎ የዛብሎን ነገድ ይስፈር፤ የዛብሎን ልጆች አለቃ የሄሎን ልጅ ኤልያብ+ ነው።  በሠራዊቱ ውስጥ የተመዘገቡትም 57,400 ናቸው።+  “በይሁዳ ምድብ በሠራዊቱ ውስጥ የተመዘገቡት በአጠቃላይ 186,400 ናቸው። መጀመሪያ ድንኳናቸውን ነቅለው የሚነሱት እነሱ ይሆናሉ።+ 10  “ሦስት ነገዶችን ያቀፈው የሮቤል+ ምድብ በየምድቡ* በመሆን በስተ ደቡብ አቅጣጫ ይስፈር፤ የሮቤል ልጆች አለቃ የሸደኡር ልጅ ኤሊጹር+ ነው። 11  በሠራዊቱ ውስጥ የተመዘገቡትም 46,500 ናቸው።+ 12  ከእሱ ቀጥሎ የሚሰፍረው የስምዖን ነገድ ይሆናል፤ የስምዖን ልጆች አለቃ የጹሪሻዳይ ልጅ ሸሉሚኤል+ ነው። 13  በሠራዊቱ ውስጥ የተመዘገቡትም 59,300 ናቸው።+ 14  ከዚያ ቀጥሎ የጋድ ነገድ ይስፈር፤ የጋድ ልጆች አለቃ የረኡዔል ልጅ ኤሊያሳፍ+ ነው። 15  በሠራዊቱ ውስጥ የተመዘገቡትም 45,650 ናቸው።+ 16  “በሮቤል ምድብ በሠራዊቱ ውስጥ የተመዘገቡት በአጠቃላይ 151,450 ናቸው፤ በሁለተኛ ደረጃ ድንኳናቸውን ነቅለው የሚነሱት እነሱ ናቸው።+ 17  “የመገናኛ ድንኳኑ ከቦታ ወደ ቦታ በሚንቀሳቀስበት ጊዜ+ የሌዋውያኑ ሰፈር በሌሎቹ ሰፈሮች መሃል መሆን ይኖርበታል። “እነሱም ልክ በሰፈሩበት ሁኔታ እያንዳንዳቸው ቦታቸውን ጠብቀው+ ሦስት ነገድ ባቀፈው ምድባቸው መሠረት መጓዝ ይኖርባቸዋል። 18  “ሦስት ነገዶችን ያቀፈው የኤፍሬም ምድብ በየምድቡ* በመሆን በስተ ምዕራብ አቅጣጫ ይስፈር፤ የኤፍሬም ልጆች አለቃ የአሚሁድ ልጅ ኤሊሻማ+ ነው። 19  በሠራዊቱ ውስጥ የተመዘገቡትም 40,500 ናቸው።+ 20  ከእሱም ቀጥሎ የምናሴ+ ነገድ ይስፈር፤ የምናሴ ልጆች አለቃ የፐዳጹር ልጅ ገማልያል+ ነው። 21  በሠራዊቱ ውስጥ የተመዘገቡትም 32,200 ናቸው።+ 22  ከዚያ ቀጥሎ የቢንያም ነገድ ይስፈር፤ የቢንያም ልጆች አለቃ የጊድኦኒ ልጅ አቢዳን+ ነው። 23  በሠራዊቱ ውስጥ የተመዘገቡትም 35,400 ናቸው።+ 24  “በኤፍሬም ምድብ በሠራዊቱ ውስጥ የተመዘገቡት በአጠቃላይ 108,100 ናቸው፤ በሦስተኛ ደረጃ ድንኳናቸውን ነቅለው የሚነሱት እነሱ ናቸው።+ 25  “ሦስት ነገዶችን ያቀፈው የዳን ምድብ በየምድቡ* በመሆን በስተ ሰሜን አቅጣጫ ይስፈር፤ የዳን ልጆች አለቃ የአሚሻዳይ ልጅ አሂዔዜር+ ነው። 26  በሠራዊቱ ውስጥ የተመዘገቡትም 62,700 ናቸው።+ 27  ከእሱም ቀጥሎ የሚሰፍረው የአሴር ነገድ ይሆናል፤ የአሴር ልጆች አለቃ የኦክራን ልጅ ፓጊኤል+ ነው። 28  በሠራዊቱ ውስጥ የተመዘገቡትም 41,500 ናቸው።+ 29  ከዚያ ቀጥሎ የንፍታሌም ነገድ ይስፈር፤ የንፍታሌም ልጆች አለቃ የኤናን ልጅ አሂራ+ ነው። 30  በሠራዊቱ ውስጥ የተመዘገቡትም 53,400 ናቸው።+ 31  “በዳን ምድብ የተመዘገቡት በአጠቃላይ 157,600 ናቸው። ሦስት ነገዶችን ባቀፈው ምድባቸው መሠረት መጨረሻ ላይ ድንኳናቸውን ነቅለው የሚነሱት እነሱ ናቸው።”+ 32  በአባቶቻቸው ቤት መሠረት የተመዘገቡት እስራኤላውያን እነዚህ ነበሩ፤ ወደ ሠራዊቱ ለመቀላቀል በሰፈሩ ውስጥ የተመዘገቡት በአጠቃላይ 603,550 ነበሩ።+ 33  ሌዋውያኑ ግን ልክ ይሖዋ ሙሴን ባዘዘው መሠረት ከሌሎቹ እስራኤላውያን ጋር+ አልተመዘገቡም።+ 34  እስራኤላውያንም ይሖዋ ሙሴን ያዘዘውን ሁሉ አደረጉ። እያንዳንዳቸው በየቤተሰባቸውና በየአባቶቻቸው ቤት በመሆን ሦስት ነገዶችን ባቀፈው ምድባቸው+ መሠረት የሰፈሩትም ሆነ ድንኳናቸውን ነቅለው የተነሱት በዚህ መንገድ ነው።+

የግርጌ ማስታወሻ

ወይም “ምልክት።”
ቃል በቃል “በየሠራዊቱ።”
ቃል በቃል “በየሠራዊቱ።”
ቃል በቃል “በየሠራዊቱ።”
ቃል በቃል “በየሠራዊቱ።”