ዘኁልቁ 33:1-56
33 የእስራኤል ሕዝብ በሙሴና በአሮን መሪነት+ በየምድቡ*+ በመሆን ከግብፅ ምድር በወጣ ጊዜ+ የተጓዘው በዚህ መልክ ነበር።
2 ሙሴም በጉዟቸው ላይ ሳሉ ያረፉባቸውን ቦታዎች ይሖዋ በሰጠው ትእዛዝ መሠረት ይመዘግብ ነበር፤ ከአንዱ ስፍራ ተነስተው ወደ ሌላው የተጓዙት በሚከተለው ሁኔታ ነበር፦+
3 በመጀመሪያው ወር ከወሩም በ15ኛው ቀን+ ከራምሴስ ተነሱ።+ ልክ በፋሲካ በዓል+ ማግስት እስራኤላውያን ግብፃውያን ሁሉ እያዩአቸው በልበ ሙሉነት* ወጡ።
4 በዚህ ጊዜ ግብፃውያን ይሖዋ በመቅሰፍት የመታቸውን በኩሮቻቸውን ሁሉ እየቀበሩ ነበር፤+ ምክንያቱም ይሖዋ በአማልክታቸው ላይ የቅጣት እርምጃ ወስዶ ነበር።+
5 በመሆኑም እስራኤላውያን ከራምሴስ ተነስተው በሱኮት+ ሰፈሩ።
6 ከዚያም ከሱኮት ተነስተው በምድረ በዳው ዳርቻ ላይ በምትገኘው በኤታም ሰፈሩ።+
7 በመቀጠልም ከኤታም ተነስተው በበዓልጸፎን+ ትይዩ ወደምትገኘው ወደ ፊሃሂሮት ተመለሱ፤ በሚግዶልም+ ፊት ለፊት ሰፈሩ።
8 ከዚያም ከፊሃሂሮት ተነስተው ባሕሩን በማቋረጥ+ ወደ ምድረ በዳው+ ሄዱ፤ በኤታም ምድረ በዳ+ የሦስት ቀን መንገድ ከተጓዙ በኋላ በማራ+ ሰፈሩ።
9 ከዚያም ከማራ ተነስተው ወደ ኤሊም መጡ። በኤሊም 12 የውኃ ምንጮችና 70 የዘንባባ ዛፎች ነበሩ፤ በመሆኑም በዚያ ሰፈሩ።+
10 በመቀጠል ደግሞ ከኤሊም ተነስተው በቀይ ባሕር አጠገብ ሰፈሩ።
11 ከዚያ በኋላ ከቀይ ባሕር ተነስተው በሲን ምድረ በዳ ሰፈሩ።+
12 ከሲን ምድረ በዳ ተነስተው ደግሞ በዶፍቃ ሰፈሩ።
13 በኋላም ከዶፍቃ ተነስተው በአሉሽ ሰፈሩ።
14 በመቀጠልም ከአሉሽ ተነስተው በረፊዲም+ ሰፈሩ፤ በዚያም ሕዝቡ የሚጠጣው ውኃ አልነበረም።
15 ከዚያ በኋላ ከረፊዲም ተነስተው በሲና ምድረ በዳ ሰፈሩ።+
16 ከሲና ምድረ በዳም ተነስተው በቂብሮትሃታባ+ ሰፈሩ።
17 ከዚያም ከቂብሮትሃታባ ተነስተው በሃጼሮት+ ሰፈሩ።
18 በኋላም ከሃጼሮት ተነስተው በሪትማ ሰፈሩ።
19 በመቀጠል ደግሞ ከሪትማ ተነስተው በሪሞንጰሬጽ ሰፈሩ።
20 ከዚያም ከሪሞንጰሬጽ ተነስተው በሊብና ሰፈሩ።
21 ከሊብናም ተነስተው በሪሳ ሰፈሩ።
22 በመቀጠልም ከሪሳ ተነስተው በቀሄላታ ሰፈሩ።
23 ከዚያም ከቀሄላታ ተነስተው በሸፈር ተራራ ሰፈሩ።
24 በኋላም ከሸፈር ተራራ ተነስተው በሃራዳ ሰፈሩ።
25 ከዚያም ከሃራዳ ተነስተው በማቅሄሎት ሰፈሩ።
26 ቀጥሎም ከማቅሄሎት ተነስተው+ በታሃት ሰፈሩ።
27 ከዚያ በኋላም ከታሃት ተነስተው በታራ ሰፈሩ።
28 ከዚያም ከታራ ተነስተው በሚትቃ ሰፈሩ።
29 በኋላም ከሚትቃ ተነስተው በሃሽሞና ሰፈሩ።
30 ከሃሽሞናም ተነስተው በሞሴሮት ሰፈሩ።
31 ከዚያም ከሞሴሮት ተነስተው በብኔያዕቃን+ ሰፈሩ።
32 በኋላም ከብኔያዕቃን ተነስተው በሆርሃጊድጋድ ሰፈሩ።
33 ከዚያም ከሆርሃጊድጋድ ተነስተው በዮጥባታ+ ሰፈሩ።
34 ከዮጥባታም ተነስተው በአብሮና ሰፈሩ።
35 ከዚያም ከአብሮና ተነስተው በዔጽዮንጋብር+ ሰፈሩ።
36 በኋላም ከዔጽዮንጋብር ተነስተው በጺን ምድረ በዳ+ በምትገኘው በቃዴስ ሰፈሩ።
37 ከቃዴስም ተነስተው በኤዶም ምድር ወሰን ላይ በሚገኘው በሆር ተራራ+ ሰፈሩ።
38 እስራኤላውያን ከግብፅ ምድር በወጡ በ40ኛው ዓመት በአምስተኛው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ካህኑ አሮን ይሖዋ በሰጠው ትእዛዝ መሠረት ወደ ሆር ተራራ ወጣ፤ በዚያም ሞተ።+
39 አሮን በሆር ተራራ ላይ በሞተበት ጊዜ ዕድሜው 123 ዓመት ነበር።
40 በከነአን ምድር በኔጌብ ይኖር የነበረው ከነአናዊው የአራድ ንጉሥ+ የእስራኤላውያንን መምጣት ሰማ።
41 ከጊዜ በኋላም ከሆር ተራራ+ ተነስተው በጻልሞና ሰፈሩ።
42 ከዚያም ከጻልሞና ተነስተው በጱኖን ሰፈሩ።
43 በመቀጠልም ከጱኖን ተነስተው በኦቦት+ ሰፈሩ።
44 ከኦቦትም ተነስተው በሞዓብ ድንበር+ ላይ በምትገኘው በኢዬዓባሪም ሰፈሩ።
45 በኋላም ከኢይም ተነስተው በዲቦንጋድ+ ሰፈሩ።
46 በመቀጠልም ከዲቦንጋድ ተነስተው በአልሞንዲብላታይም ሰፈሩ።
47 ከአልሞንዲብላታይም ተነስተው ደግሞ በነቦ+ ፊት ለፊት በአባሪም+ ተራሮች ሰፈሩ።
48 በመጨረሻም ከአባሪም ተራሮች ተነስተው በኢያሪኮ በሚገኘው በዮርዳኖስ አጠገብ ባለው የሞዓብ በረሃማ ሜዳ ሰፈሩ።+
49 በሞዓብ በረሃማ ሜዳ ከቤትየሺሞት እስከ አቤልሺቲም+ በሚገኘው ስፍራ በዮርዳኖስ ወንዝ ዳርቻ ሰፈሩ።
50 ይሖዋ በኢያሪኮ በሚገኘው በዮርዳኖስ አጠገብ ባለው የሞዓብ በረሃማ ሜዳ ላይ ሙሴን እንዲህ አለው፦
51 “እስራኤላውያንን ተናገራቸው፤ እንዲህም በላቸው፦ ‘እንግዲህ ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ ወደ ከነአን ምድር ልትገቡ ነው።+
52 የምድሪቱን ነዋሪዎች በሙሉ ከፊታችሁ አባሯቸው፤ የተቀረጹ የድንጋይ ምስሎቻቸውንም+ ሁሉ አጥፉ፤ ከብረት የተሠሩ ሐውልቶቻቸውንም*+ በሙሉ አስወግዱ፤ በከፍታ ቦታዎች ላይ ያሉ ቅዱስ ስፍራዎቻቸውን+ ሁሉ አፍርሱ።
53 ምድሪቱን ርስት አድርጌ ስለምሰጣችሁ ምድሪቱን ወርሳችሁ በዚያ ትኖራላችሁ።+
54 ምድሪቱንም በየቤተሰባችሁ ውርስ አድርጋችሁ በዕጣ+ ተከፋፈሉ። ተለቅ ላለው ቡድን በዛ ያለውን፣ አነስ ላለው ቡድን ደግሞ አነስ ያለውን ውርስ አድርጋችሁ ስጡት።+ ሁሉም በወጣለት ዕጣ መሠረት የተሰጠውን ቦታ ይወርሳል። በየአባቶቻችሁ ነገዶች ርስታችሁን ውርስ አድርጋችሁ ትቀበላላችሁ።+
55 “‘የምድሪቱን ነዋሪዎች ከፊታችሁ ሳታባርሩ እዚያው ከተዋችኋቸው+ ግን ዓይናችሁ ውስጥ እንደገባ ጉድፍ እንዲሁም ጎናችሁ ላይ እንደተሰካ እሾህ ይሆኑባችኋል፤ ደግሞም በምትኖሩበት ምድር ያንገላቷችኋል።+
56 እኔም በእነሱ ላይ ለማድረግ ያሰብኩትን በእናንተ ላይ አደርግባችኋለሁ።’”+