ዘኁልቁ 34:1-29
34 በተጨማሪም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦
2 “ለእስራኤላውያን ይህን መመሪያ ስጣቸው፦ ‘ወደ ከነአን ምድር ስትገቡ+ ርስት አድርጋችሁ የምትወርሷት ምድር ይኸውም የከነአን ምድር ከነወሰኖቿ ይህች ናት።+
3 “‘በስተ ደቡብ ያለው ወሰናችሁ ከጺን ምድረ በዳ ተነስቶ እስከ ኤዶም ጠረፍ ድረስ ይዘልቃል፤ በስተ ምሥራቅ ያለው ደቡባዊ ወሰናችሁ ደግሞ ከጨው ባሕር* ዳርቻ ጀምሮ ያለው ይሆናል።+
4 ወሰናችሁ አቅጣጫውን በመቀየር ከአቅራቢም አቀበት+ በስተ ደቡብ አድርጎ እስከ ጺን ድረስ ይዘልቃል፤ መጨረሻውም ከቃዴስበርኔ+ በስተ ደቡብ ይሆናል። ከዚያም ወደ ሃጻርአዳር+ ይሄድና ወደ አጽሞን ይዘልቃል።
5 ወሰኑ አጽሞን ላይ ሲደርስ አቅጣጫውን ቀይሮ ወደ ግብፅ ደረቅ ወንዝ* ይሄዳል፤ መጨረሻውም ባሕሩ* ይሆናል።+
6 “‘ምዕራባዊ ወሰናችሁ ደግሞ ታላቁ ባሕርና* የባሕሩ ዳርቻ ይሆናል። ይህ ምዕራባዊ ወሰናችሁ ይሆናል።+
7 “‘ሰሜናዊ ወሰናችሁ የሚከተለው ይሆናል፦ ከታላቁ ባሕር አንስቶ እስከ ሆር ተራራ ድረስ ምልክት በማድረግ ወሰናችሁን ከልሉ።
8 ከሆር ተራራም አንስቶ እስከ ሌቦሃማት*+ ድረስ ወሰኑን ምልክት አድርጉ፤ የወሰኑም መጨረሻ ጼዳድ+ ይሆናል።
9 ወሰኑም እስከ ዚፍሮን ድረስ ይዘልቃል፤ መጨረሻውም ሃጻርኤናን+ ይሆናል። ይህ ሰሜናዊ ወሰናችሁ ይሆናል።
10 “‘ከዚያም በስተ ምሥራቅ በኩል ወሰናችሁን ከሃጻርኤናን አንስቶ እስከ ሸፋም ድረስ ምልክት አድርጉ።
11 ወሰኑም ከሸፋም አንስቶ ከአይን በስተ ምሥራቅ እስከሚገኘው እስከ ሪብላ ድረስ ይዘልቃል፤ ከዚያም ቁልቁል ወርዶ የኪኔሬትን ባሕር* ምሥራቃዊ ዳርቻ አቋርጦ ያልፋል።+
12 ወሰኑ ወደ ዮርዳኖስ ይወርድና መጨረሻው ጨው ባሕር ይሆናል።+ እንግዲህ ምድራችሁ+ በዙሪያዋ ካሉት ወሰኖቿ ጋር ይህች ናት።’”
13 በመሆኑም ሙሴ እስራኤላውያንን እንዲህ ሲል አዘዛቸው፦ “ይሖዋ ለዘጠኙ ነገዶችና ለግማሹ ነገድ እንዲሰጥ ባዘዘው መሠረት ርስት አድርጋችሁ በዕጣ የምትከፋፈሏት+ ምድር ይህች ናት።
14 የሮቤላውያን ነገድ በየአባቶቻቸው ቤት፣ የጋዳውያን ነገድ በየአባቶቻቸው ቤት እንዲሁም የምናሴ ነገድ እኩሌታ አስቀድመው ርስታቸውን ወስደዋልና።+
15 ሁለቱ ነገድና ግማሹ ነገድ በኢያሪኮ አቅራቢያ ከዮርዳኖስ ክልል በስተ ምሥራቅ በፀሐይ መውጫ አቅጣጫ ርስታቸውን አግኝተዋል።”+
16 በተጨማሪም ይሖዋ ሙሴን እንዲህ አለው፦
17 “ምድሪቱን ለእናንተ ርስት አድርገው የሚያከፋፍሏችሁ ካህኑ አልዓዛርና+ የነዌ ልጅ ኢያሱ+ ናቸው።
18 ምድሪቱን ርስት አድርጋችሁ ለማከፋፈል ከእያንዳንዱ ነገድ አንድ አንድ አለቃ ትወስዳላችሁ።+
19 የሰዎቹም ስም የሚከተለው ነው፦ ከይሁዳ ነገድ+ የየፎኒ ልጅ ካሌብ፣+
20 ከስምዖን ልጆች ነገድ+ የአሚሁድ ልጅ ሸሙኤል፣
21 ከቢንያም ነገድ+ የኪስሎን ልጅ ኤሊዳድ፣
22 ከዳን ልጆች ነገድ+ አንድ አለቃ ይኸውም የዮግሊ ልጅ ቡቂ፣
23 ከዮሴፍ ልጆች+ መካከል ከምናሴ ልጆች ነገድ+ አንድ አለቃ ይኸውም የኤፎድ ልጅ ሃኒኤል፣
24 ከኤፍሬም ልጆች ነገድ+ አንድ አለቃ ይኸውም የሺፍጣን ልጅ ቀሙኤል፣
25 ከዛብሎን ልጆች ነገድ+ አንድ አለቃ ይኸውም የፓርናክ ልጅ ኤሊጻፋን፣
26 ከይሳኮር ልጆች ነገድ+ አንድ አለቃ ይኸውም የአዛን ልጅ ፓልጢኤል፣
27 ከአሴር ልጆች ነገድ+ አንድ አለቃ ይኸውም የሸሎሚ ልጅ አሂሑድ፣
28 ከንፍታሌም ልጆች ነገድ+ አንድ አለቃ ይኸውም የአሚሁድ ልጅ ፐዳሄል።”
29 ይሖዋ በከነአን ምድር ለእስራኤላውያን መሬቱን እንዲያከፋፍሉ ያዘዛቸው እነዚህ ናቸው።+