ዘካርያስ 11:1-17

  • የአምላክን እረኛ መናቅ የሚያስከትለው መዘዝ (1-17)

    • “ለእርድ የተዘጋጀውን መንጋ ጠብቅ” (4)

    • ሁለት በትሮች፦ ደስታና ኅብረት (7)

    • የእረኛው ደሞዝ፦ 30 የብር ሰቅል (12)

    • ገንዘቡ ግምጃ ቤት ውስጥ ተጣለ (13)

11  “ሊባኖስ ሆይ፣ እሳት አርዘ ሊባኖሶችህን እንድትበላበሮችህን ክፈት።   የጥድ ዛፍ ሆይ፣ አርዘ ሊባኖሱ ስለወደቀ ዋይ ዋይ በል፤ታላላቆቹ ዛፎች ወድመዋል! እናንተ የባሳን የባሉጥ ዛፎች፣ጥቅጥቅ ያለው ጫካ ስለጠፋ ዋይ ዋይ በሉ!   ስሙ! እረኞች ግርማ ሞገሳቸው ስለተገፈፈዋይ ዋይ ይላሉ። አዳምጡ! በዮርዳኖስ አጠገብ ያሉት ጥቅጥቅ ያሉ ጥሻዎች ስለወደሙደቦል አንበሶች ያገሳሉ።  “አምላኬ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ለእርድ የተዘጋጀውን መንጋ ጠብቅ፤+  የገዟቸው ያርዷቸዋል፤+ ሆኖም ተጠያቂ አይሆኑም። የሚሸጧቸውም+ “ይሖዋ የተመሰገነ ይሁን፤ ባለጸጋ እሆናለሁና” ይላሉ። እረኞቻቸውም ምንም ዓይነት ርኅራኄ አያሳዩአቸውም።’+  “‘ከእንግዲህ ለምድሪቱ ነዋሪዎች አልራራላቸውም’ ይላል ይሖዋ። ‘በመሆኑም እያንዳንዱ ሰው በባልንጀራው እጅና በንጉሡ እጅ እንዲወድቅ አደርጋለሁ፤ እነሱም ምድሪቱን ያደቋታል፤ እኔም እነሱን ከእጃቸው አልታደግም።’”  እናንተ ጉስቁልና የደረሰባችሁ የመንጋው አባላት፣ ለመታረድ የተዘጋጀውን መንጋ መጠበቅ ጀምሬአለሁ፤+ ይህን ያደረግኩትም ለእናንተ ስል ነው። ስለዚህ ሁለት በትሮችን ወስጄ አንደኛውን በትር “ደስታ፣” ሌላኛውን ደግሞ “ኅብረት” ብዬ ጠራሁት፤+ እኔም መንጋውን መጠበቅ ጀመርኩ።  ደግሞም በአንድ ወር ውስጥ ሦስት እረኞችን አባረርኩ፤ ይህን ያደረግኩት እነሱን መታገሥ ስላልቻልኩና* እነሱም እኔን ስለተጸየፉኝ* ነው።  እንዲህም አልኩ፦ “ከእንግዲህ እረኛችሁ አልሆንም። የምትሞተው ትሙት፤ የምትጠፋውም ትጥፋ። የቀሩት ደግሞ አንዳቸው የሌላውን ሥጋ ይብሉ።” 10  ስለዚህ ከሕዝቡ ሁሉ ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳኔን በማፍረስ “ደስታ” የተባለውን በትሬን+ ወስጄ ሰበርኩት። 11  በመሆኑም በዚያን ቀን ቃል ኪዳኑ ፈረሰ፤ ይመለከቱኝ የነበሩት የተጎሳቆሉት የመንጋው አባላትም ይህ የይሖዋ ቃል መሆኑን አወቁ። 12  ከዚያም “መልካም መስሎ ከታያችሁ ደሞዜን ስጡኝ፤ ካልሆነ ግን ተዉት” አልኳቸው። እነሱም ደሞዜን፣ 30 የብር ሰቅል ከፈሉኝ።*+ 13  ከዚያም ይሖዋ “እኔን የገመቱበትን የከበረ ዋጋ+ ይኸውም ብሩን ግምጃ ቤት ውስጥ ጣለው” አለኝ። እኔም 30ውን የብር ሰቅል ወስጄ በይሖዋ ቤት ግምጃ ቤት ውስጥ ጣልኩት።+ 14  ከዚያም በይሁዳና በእስራኤል መካከል ያለውን ወንድማማችነት በማፍረስ “ኅብረት” የተባለውን ሁለተኛውን በትሬን+ ሰበርኩት።+ 15  ይሖዋም እንዲህ አለኝ፦ “እንግዲህ የሰነፍ እረኛ መሣሪያዎችን ውሰድ።+ 16  በምድሪቱ ላይ እረኛ አስነሳለሁና። እያለቁ ያሉትን በጎች አይንከባከብም፤+ ግልገሎቹን አይፈልግም ወይም የተጎዳውን አይፈውስም+ አሊያም መቆም የሚችሉትን አይቀልብም። ከዚህ ይልቅ የሰባውን በግ ሥጋ ይበላል፤+ የበጎቹንም ሰኮና ቆርጦ ይጥላል።+ 17  መንጋውን ለሚተው+ የማይረባ እረኛዬ ወዮለት!+ ሰይፍ ክንዱንና ቀኝ ዓይኑን ይመታዋል። ክንዱ ሙሉ በሙሉ ይሰልላል፤ቀኝ ዓይኑም ሙሉ በሙሉ ይታወራል።”*

የግርጌ ማስታወሻ

ወይም “ነፍሴ እነሱን መታገሥ ስላልቻለችና።”
ወይም “የእነሱም ነፍስ እኔን ስለተጸየፈችኝ።”
ቃል በቃል “መዘኑልኝ።”
ቃል በቃል “ይጨልማል።”