ዘካርያስ 13:1-9
13 “በዚያ ቀን፣ ኃጢአታቸውንና ርኩሰታቸውን ለማንጻት ለዳዊት ቤትና ለኢየሩሳሌም ነዋሪዎች የውኃ ጉድጓድ ይቆፈራል።+
2 “በዚያ ቀን” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ፣ “የጣዖቶቹን ስም ከምድሪቱ ላይ እደመስሳለሁ፤+ እነሱም ዳግመኛ አይታወሱም፤ ደግሞም ነቢያቱንና የርኩሰት መንፈሱን ከምድሪቱ ላይ አስወግዳለሁ።+
3 አንድ ሰው ዳግመኛ ትንቢት ቢናገር የወለዱት አባትና እናቱ ‘በይሖዋ ስም ሐሰት ስለተናገርክ በሕይወት አትኖርም’ ይሉታል። ደግሞም የወለዱት አባትና እናቱ ትንቢት በመናገሩ ይወጉታል።+
4 “በዚያ ቀን እያንዳንዱ ነቢይ ትንቢት በሚናገርበት ጊዜ ሁሉ በገዛ ራእዩ ያፍራል፤ ሰዎችንም ለማታለል የነቢያት ዓይነት ፀጉራም ልብስ+ አይለብስም።
5 ደግሞም እንዲህ ይላል፦ ‘እኔ ነቢይ አይደለሁም። ይልቁንም አራሽ ነኝ፤ ምክንያቱም አንድ ሰው ልጅ ሳለሁ ባሪያ አድርጎ ገዝቶኛል።’
6 አንድ ሰውም ‘በትከሻዎችህ መካከል* ያሉት ቁስሎች ምንድን ናቸው?’ ብሎ ቢጠይቀው ‘በወዳጆቼ ቤት ሳለሁ የቆሰልኩት ነው’ ይላል።”
7 “ሰይፍ ሆይ፣ በእረኛዬ+ ይኸውምበወዳጄ ላይ ንቃ” ይላል የሠራዊት ጌታ ይሖዋ።
“እረኛውን ምታ፤+ መንጋውም ይበተን፤*+እኔም እጄን ታናናሽ በሆኑት ላይ አዞራለሁ።”
8 “በምድሪቱም ሁሉ” ይላል ይሖዋ፣“በእሷ ላይ ካለው ሁለት ሦስተኛው ተመትቶ ይጠፋል፤*አንድ ሦስተኛው ግን በውስጧ ይቀራል።
9 ደግሞም አንድ ሦስተኛው በእሳት ውስጥ እንዲያልፍ አደርጋለሁ፤ብር እንደሚነጥር አነጥራቸዋለሁ፤ወርቅም እንደሚፈተን እፈትናቸዋለሁ።+
እነሱ ስሜን ይጠራሉ፤እኔም እመልስላቸዋለሁ።
‘እነሱ ሕዝቤ ናቸው’ እላለሁ፤+
እነሱ ደግሞ ‘ይሖዋ አምላካችን ነው’ ይላሉ።”