ዘካርያስ 2:1-13

  • ራእይ 3፦ የመለኪያ ገመድ የያዘ ሰው (1-13)

    • ኢየሩሳሌም ትለካለች (2)

    • ይሖዋ “በዙሪያዋ የእሳት ቅጥር” ይሆናል (5)

    • “እናንተን የሚነካ ሁሉ የዓይኔን ብሌን ይነካል” (8)

    • “ብዙ ብሔራት ከይሖዋ ጋር ይተባበራሉ” (11)

2  እኔም ቀና ብዬ ስመለከት በእጁ የመለኪያ ገመድ+ የያዘ ሰው አየሁ።  ከዚያም “ወዴት እየሄድክ ነው?” ብዬ ጠየቅኩት። እሱም “ወርዷና ርዝመቷ ምን ያህል እንደሆነ አውቅ ዘንድ ኢየሩሳሌምን ለመለካት እየሄድኩ ነው”+ ሲል መለሰልኝ።  እነሆም፣ ከእኔ ጋር ሲነጋገር የነበረው መልአክ ሄደ፤ ሌላም መልአክ ሊገናኘው መጣ።  ከዚያም እንዲህ አለው፦ “ወደዚያ ሮጠህ ሂድና ያንን ወጣት እንዲህ በለው፦ ‘“በመካከሏ ካሉት ሰዎችና መንጎች ሁሉ የተነሳ+ ኢየሩሳሌም ቅጥር እንደሌላቸው መንደሮች በነዋሪዎች ትሞላለች።+  እኔም በዙሪያዋ የእሳት ቅጥር እሆንላታለሁ”+ ይላል ይሖዋ፤ “ክብሬም በመካከሏ ይሆናል።”’”+  “ኑ! ኑ! ከሰሜን ምድር ሽሹ”+ ይላል ይሖዋ። “ወደ አራቱ የሰማይ ነፋሳት በትኛችኋለሁና”+ ይላል ይሖዋ።  “ጽዮን ሆይ፣ ነይ! ከባቢሎን ሴት ልጅ ጋር የምትኖሪ ሆይ፣ አምልጪ።+  ክብር ከተጎናጸፈ በኋላ፣* እናንተን ወደዘረፏችሁ ብሔራት የላከኝ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላልና፦+ ‘እናንተን የሚነካ ሁሉ የዓይኔን ብሌን* ይነካል።+  አሁን በእነሱ ላይ እጄን በዛቻ አወዛውዛለሁ፤ የገዛ ባሪያዎቻቸውም ይዘርፏቸዋል።’+ እናንተም እኔን የላከኝ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንደሆነ ታውቃላችሁ። 10  “የጽዮን ሴት ልጅ ሆይ፣ እልል በይ፤+ እኔ እመጣለሁና፤+ በመካከልሽም እኖራለሁ”+ ይላል ይሖዋ። 11  “በዚያን ቀን ብዙ ብሔራት ከይሖዋ ጋር ይተባበራሉ፤+ እነሱም ሕዝቤ ይሆናሉ፤ እኔም በመካከልሽ እኖራለሁ።” ደግሞም እኔን ወደ አንቺ የላከኝ የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንደሆነ ታውቂያለሽ። 12  ይሖዋ ይሁዳን በተቀደሰው ምድር ላይ ድርሻው አድርጎ ይወርሰዋል፤ ኢየሩሳሌምንም እንደገና ይመርጣል።+ 13  የሰው ልጆች ሁሉ፣* በይሖዋ ፊት ጸጥ በሉ፤ በቅዱስ መኖሪያው ሆኖ እርምጃ እየወሰደ ነውና።

የግርጌ ማስታወሻ

የመጀመሪያው ጽሑፍ “የዓይኔን ብሌን” የሚል ነበር። ሆኖም ሶፌሪም በመባል የሚታወቁት ጸሐፍት “የዓይኑን ብሌን” ብለው ቀየሩት።
ቃል በቃል “ከክብር በኋላ።”
ቃል በቃል “ሥጋ ሁሉ።”