ዘዳግም 2:1-37

  • ለ38 ዓመት በምድረ በዳ ተንከራተቱ (1-23)

  • የሃሽቦንን ንጉሥ ሲሖንን ድል አደረጉ (24-37)

2  ከዚያም ልክ ይሖዋ በነገረኝ መሠረት ተመልሰን ወደ ቀይ ባሕር የሚወስደውን መንገድ በመከተል ወደ ምድረ በዳው ተጓዝን፤+ በሴይር ተራራ አካባቢም ለብዙ ቀናት ተንከራተትን።  በመጨረሻም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦  ‘እንግዲህ በዚህ ተራራ አካባቢ ብዙ ተንከራታችኋል። አሁን ወደ ሰሜን አቅኑ።  ሕዝቡንም እንዲህ ብለህ እዘዝ፦ “እንግዲህ በሴይር በሚኖሩት+ በወንድሞቻችሁ በኤሳው ዘሮች+ ድንበር አልፋችሁ ልትሄዱ ነው፤ እነሱም ይፈሯችኋል፤+ ቢሆንም ከፍተኛ ጥንቃቄ አድርጉ።  ከምድራቸው ላይ የእግር መርገጫ የምታክል መሬት እንኳ ስለማልሰጣችሁ ከእነሱ ጋር እንዳትጣሉ፤* ምክንያቱም የሴይርን ተራራ ለኤሳው ርስት አድርጌ ሰጥቼዋለሁ።+  ለምትበሉት ምግብም ሆነ ለምትጠጡት ውኃ ገንዘብ ክፈሏቸው።+  አምላክህ ይሖዋ የእጅህን ሥራ ሁሉ ባርኮልሃልና። በዚህ ጭልጥ ያለ ምድረ በዳ እንደተጓዝክ በሚገባ ያውቃል። በእነዚህ 40 ዓመታት አምላክህ ይሖዋ ከአንተ ጋር ስለነበር ምንም የጎደለብህ ነገር የለም።”’+  ስለዚህ በሴይር በሚኖሩት ወንድሞቻችን በኤሳው ዘሮች በኩል አልፈን ሄድን፤+ ወደ አረባ ከሚወስደው መንገድ፣ ከኤላት እና ከዔጽዮንጋብር ርቀን ተጓዝን።+ “በመቀጠልም ተነስተን ወደ ሞዓብ ምድረ በዳ በሚወስደው መንገድ ተጓዝን።+  ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ ‘ከሞዓብ ምድር የትኛውንም መሬት ርስት አድርጌ ስለማልሰጥህ ከእሱ ጋር አትጣላ ወይም ጦርነት አትግጠም፤ ምክንያቱም ኤርን ለሎጥ ዘሮች ርስት አድርጌ ሰጥቻቸዋለሁ።+ 10  (ታላቅና ብዙ እንዲሁም ልክ እንደ ኤናቃውያን ቁመተ ረጃጅም የሆኑት ኤሚማውያን+ ቀደም ሲል በዚያ ይኖሩ ነበር። 11  ረፋይማውያንም+ ልክ እንደ ኤናቃውያን+ ይቆጠሩ ነበር፤ ሞዓባውያንም ኤሚማውያን ብለው ይጠሯቸው ነበር። 12  ሆራውያን+ ቀደም ሲል በሴይር ይኖሩ ነበር፤ እስራኤላውያን ይሖዋ ርስት አድርጎ በሚሰጣቸው ምድር ላይ እንደሚያደርጉት ሁሉ የኤሳውም ዘሮች ሆራውያንን በማስለቀቅና በማጥፋት በምድራቸው ላይ መኖር ጀመሩ።)+ 13  በሉ አሁን ተነሱና የዘረድን ሸለቆ* አቋርጣችሁ ሂዱ።’ ስለዚህ የዘረድን ሸለቆ*+ አቋርጠን ሄድን። 14  ከቃዴስበርኔ ተነስተን የዘረድን ሸለቆ* እስክናቋርጥ ድረስ 38 ዓመት ፈጅቶብናል፤ በዚህ ጊዜም ይሖዋ ለእነሱ በማለላቸው መሠረት ለጦርነት ብቁ የሆነው ትውልድ በሙሉ ከሕዝቡ መካከል አለቀ።+ 15  ሙሉ በሙሉ እስኪጠፉም ድረስ የይሖዋ እጅ ከሕዝቡ መካከል ሊያጠፋቸው በእነሱ ላይ ነበር።+ 16  “ለጦርነት ብቁ የሆኑት ወንዶች ሁሉ ከሕዝቡ መካከል ሞተው እንዳለቁ+ 17  ይሖዋ በድጋሚ እንዲህ አለኝ፦ 18  ‘ዛሬ በሞዓብ ክልል ይኸውም በኤር በኩል ታልፋለህ። 19  ወደ አሞናውያን በቀረብክ ጊዜ እነሱን አታስቆጣቸው ወይም አትተናኮላቸው፤ ምክንያቱም ምድሪቱን ለሎጥ ዘሮች ርስት አድርጌ ስለሰጠኋቸው ከአሞን ልጆች ምድር የትኛውንም መሬት ርስት አድርጌ አልሰጥህም።+ 20  ይህችም ምድር የረፋይማውያን+ ምድር ተደርጋ ትቆጠር ነበር። (ቀደም ሲል ረፋይማውያን በዚያ ይኖሩ ነበር፤ አሞናውያንም ዛምዙሚማውያን ብለው ይጠሯቸው ነበር። 21  እነሱም ታላቅና ቁጥራቸው የበዛ እንዲሁም ልክ እንደ ኤናቃውያን+ ቁመተ ረጃጅሞች ነበሩ፤ ይሖዋ ግን ከአሞናውያን ፊት አጠፋቸው፤ እነሱም ምድራቸውን አስለቅቀው በዚያ ሰፈሩ። 22  አሁን በሴይር ለሚኖሩት+ የኤሳው ዘሮች ሆራውያንን+ ከፊታቸው ባጠፋላቸው ጊዜ ያደረገላቸው ይህንኑ ነበር፤ በዚህም የተነሳ የኤሳው ዘሮች እነሱን አስለቅቀው እስከ ዛሬ ድረስ በምድራቸው ላይ እየኖሩ ነው። 23  አዊማውያን ደግሞ ከካፍቶር* የተገኙት ካፍቶሪማውያን+ እነሱን አጥፍተው በምድራቸው ላይ መኖር እስከጀመሩበት ጊዜ ድረስ እስከ ጋዛ+ በሚገኙት መንደሮች ይኖሩ ነበር።) 24  “‘ተነሱና የአርኖንን ሸለቆ*+ አቋርጣችሁ ሂዱ። ይኸው የሃሽቦንን ንጉሥ አሞራዊውን ሲሖንን+ በእጃችሁ ሰጥቻችኋለሁ። በመሆኑም ምድሩን መውረስ ጀምሩ፤ ከእሱም ጋር ጦርነት ግጠሙ። 25  በዚህች ዕለት፣ ስለ እናንተ የሰሙ ከሰማይ በታች ያሉ ሕዝቦች ሁሉ እንዲሸበሩና በፍርሃት እንዲርዱ አደርጋለሁ። በእናንተም የተነሳ ይታወካሉ፤ ምጥም ይይዛቸዋል።’+ 26  “ከዚያም እኔ ከቀደሞት+ ምድረ በዳ ለሃሽቦን ንጉሥ ለሲሖን እንዲህ የሚል የሰላም መልእክት እንዲነግሩት መልእክተኞችን ላክሁበት፦+ 27  ‘ምድርህን አቋርጬ እንዳልፍ ፍቀድልኝ። ከመንገዱ አልወጣም፤ ወደ ቀኝም ሆነ ወደ ግራ ዞር አልልም።+ 28  በገንዘብ የምትሸጥልኝን ምግብ ብቻ እበላለሁ፤ በገንዘብ የምትሰጠኝንም ውኃ ብቻ እጠጣለሁ። ምድሩን ረግጬ እንዳልፍ ብቻ ፍቀድልኝ፤ 29  አምላካችን ይሖዋ ወደሚሰጠን ምድር ለመግባት ዮርዳኖስን እስክሻገር ድረስ በሴይር የሚኖሩት የኤሳው ዘሮችና በኤር የሚኖሩት ሞዓባውያን እንዲሁ አድርገውልኛል።’ 30  የሃሽቦን ንጉሥ ሲሖን ግን በእሱ በኩል አቋርጠን እንድናልፍ አልፈቀደልንም፤ ምክንያቱም አምላክህ ይሖዋ ሐሳበ ግትር እንዲሆንና ልቡ እንዲደነድን ፈቅዶ ነበር፤+ ይህን ያደረገው ይኸው ዛሬ እንደምታዩት እጃችሁ ላይ እንዲወድቅ ነው።+ 31  “ከዚያም ይሖዋ እንዲህ አለኝ፦ ‘እነሆ ሲሖንን እና ምድሩን በእጅህ አሳልፌ ሰጥቼሃለሁ። እንግዲህ ምድሩን ለመውረስ ተነስ።’+ 32  ሲሖንም ከመላው ሕዝቡ ጋር በመሆን ያሃጽ+ ላይ እኛን ለመውጋት በወጣ ጊዜ 33  አምላካችን ይሖዋ በእጃችን አሳልፎ ሰጠው፤ ስለዚህ እሱንም ሆነ ልጆቹን እንዲሁም ሕዝቡን በሙሉ ድል አደረግናቸው። 34  በዚያን ጊዜም ከተሞቹን ሁሉ ያዝን፤ ወንዶችን፣ ሴቶችንና ልጆችን ጨምሮ እያንዳንዱን ከተማ ሙሉ በሙሉ አጠፋን። ማንንም በሕይወት አላስተረፍንም።+ 35  ለራሳችን ማርከን የወሰድነው እንስሶችንና በያዝናቸው ከተሞች ውስጥ ያገኘነውን ንብረት ብቻ ነው። 36  በአርኖን ሸለቆ* ዳርቻ ካለችው ከአሮዔር+ (በሸለቆው ውስጥ የምትገኘውን ከተማ ጨምሮ) እስከ ጊልያድ ድረስ ከእጃችን ያመለጠ አንድም ከተማ አልነበረም። አምላካችን ይሖዋ ሁሉንም በእጃችን አሳልፎ ሰጥቶን ነበር።+ 37  ሆኖም ወደ አሞናውያን ምድር፣+ ወደ ያቦቅ ሸለቆ*+ ዳርቻ ሁሉና በተራራማው አካባቢ ወደሚገኙት ከተሞች ወይም አምላካችን ይሖዋ ወደከለከለን ወደ ሌላ ማንኛውም ቦታ አልቀረባችሁም።

የግርጌ ማስታወሻ

ወይም “እነሱን አትተንኩሷቸው።”
ወይም “ደረቅ ወንዝ።”
ወይም “ደረቅ ወንዝ።”
ወይም “ደረቅ ወንዝ።”
ቀርጤስን ያመለክታል።
ወይም “ደረቅ ወንዝ።”
ወይም “ደረቅ ወንዝ።”
ወይም “ደረቅ ወንዝ።”