በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የዘፀአት መጽሐፍ

ምዕራፎች

የመጽሐፉ ይዘት

  • 1

    • እስራኤላውያን በግብፅ እየበዙ ሄዱ (1-7)

    • ፈርዖን እስራኤላውያንን ጨቆናቸው (8-14)

    • ፈሪሃ አምላክ ያላቸው አዋላጆች ወንዶቹን ልጆች ሳይገድሏቸው ቀሩ (15-22)

  • 2

    • ሙሴ ተወለደ (1-4)

    • የፈርዖን ሴት ልጅ ሙሴን አሳደገችው (5-10)

    • ሙሴ ወደ ምድያም ሸሸ፤ ሲፓራን አገባ (11-22)

    • አምላክ የእስራኤላውያንን ጩኸት ሰማ (23-25)

  • 3

    • ሙሴና የሚነደው ቁጥቋጦ (1-12)

    • ይሖዋ የስሙን ትርጉም ገለጠ (13-15)

    • ይሖዋ ለሙሴ የሰጠው ትእዛዝ (16-22)

  • 4

    • ሙሴ ሦስት ተአምራት እንዲፈጽም ተነገረው (1-9)

    • ሙሴ ብቁ እንዳልሆነ ተሰማው (10-17)

    • ሙሴ ወደ ግብፅ ተመለሰ (18-26)

    • ሙሴ በድጋሚ ከአሮን ጋር ተገናኘ (27-31)

  • 5

    • ሙሴና አሮን ፈርዖን ፊት ቀረቡ (1-5)

    • እስራኤላውያን የሚደርስባቸው ጭቆና እየባሰ ሄደ (6-18)

    • እስራኤላውያን ሙሴንና አሮንን አማረሩ (19-23)

  • 6

    • ነፃ እንደሚወጡ ዳግመኛ ተስፋ ተሰጣቸው (1-13)

      • ይሖዋ ስሙን ሙሉ በሙሉ አልገለጠላቸውም ነበር (2, 3)

    • የሙሴና የአሮን የዘር ሐረግ (14-27)

    • ሙሴ በድጋሚ ፈርዖን ፊት ቀረበ (28-30)

  • 7

    • ይሖዋ ሙሴን አበረታታው (1-7)

    • የአሮን በትር ትልቅ እባብ ሆነ (8-13)

    • የመጀመሪያው መቅሰፍት፦ ውኃው ወደ ደም ተለወጠ (14-25)

  • 8

    • ሁለተኛው መቅሰፍት፦ እንቁራሪቶች (1-15)

    • ሦስተኛው መቅሰፍት፦ ትንኝ (16-19)

    • አራተኛው መቅሰፍት፦ ተናካሽ ዝንብ (20-32)

      • መቅሰፍቱ ጎሸንን አልነካም (22, 23)

  • 9

    • አምስተኛው መቅሰፍት፦ ከብቶቻቸው ሞቱ (1-7)

    • ስድስተኛው መቅሰፍት፦ በሰዎችና በእንስሳት ላይ እባጭ ወጣ (8-12)

    • ሰባተኛው መቅሰፍት፦ የበረዶ ውርጅብኝ (13-35)

      • ፈርዖን የአምላክን ኃይል ያያል (16)

      • የይሖዋ ስም ይታወጃል (16)

  • 10

    • ስምንተኛው መቅሰፍት፦ አንበጦች (1-20)

    • ዘጠነኛው መቅሰፍት፦ ድቅድቅ ጨለማ (21-29)

  • 11

    • አሥረኛው መቅሰፍት እንደሚመጣ ተነገረ (1-10)

      • እስራኤላውያን ከግብፃውያን ላይ ስጦታ እንዲጠይቁ ተነገራቸው (2)

  • 12

    • የፋሲካ በዓል ተቋቋመ (1-28)

      • ደሙን በበሩ መቃንና ጉበን ላይ እንዲረጩ ተነገራቸው (7)

    • አሥረኛው መቅሰፍት፦ በኩር የሆኑት ተገደሉ (29-32)

    • እስራኤላውያን ከግብፅ ወጡ (33-42)

      • አራት መቶ ሠላሳው ዓመት ተፈጸመ (40, 41)

    • ስለ ፋሲካ በዓል አከባበር የተሰጠ መመሪያ (43-51)

  • 13

    • በኩር የሆነ ወንድ ሁሉ የይሖዋ ነው (1, 2)

    • እርሾ ያልገባበት ቂጣ በዓል (3-10)

    • በኩር የሆነ ወንድ ሁሉ ለአምላክ የተሰጠ ነው (11-16)

    • እስራኤላውያን ወደ ቀይ ባሕር እንዲያመሩ ታዘዙ (17-20)

    • የደመናና የእሳት ዓምድ (21, 22)

  • 14

    • እስራኤላውያን ቀይ ባሕር ደረሱ (1-4)

    • ፈርዖን እስራኤላውያንን አሳደዳቸው (5-14)

    • እስራኤላውያን ቀይ ባሕርን ተሻገሩ (15-25)

    • ግብፃውያን ባሕሩ ውስጥ ሰመጡ (26-28)

    • እስራኤላውያን በይሖዋ አመኑ (29-31)

  • 15

    • የሙሴና የእስራኤላውያን የድል መዝሙር (1-19)

    • ሚርያም ከወንዶቹ ጋር እየተቀባበለች ዘመረች (20, 21)

    • መራራው ውኃ ጣፋጭ ሆነ (22-27)

  • 16

    • ሕዝቡ በምግብ የተነሳ አጉረመረመ (1-3)

    • ይሖዋ ማጉረምረማቸውን ሰማ (4-12)

    • ድርጭትና መና ተሰጣቸው (13-21)

    • በሰንበት ቀን መና አልነበረም (22-30)

    • መና ለመታሰቢያነት ተቀመጠ (31-36)

  • 17

    • በኮሬብ ውኃ ባለማግኘታቸው አማረሩ (1-4)

    • ከዓለት ውኃ ፈለቀ (5-7)

    • ከአማሌቃውያን ጋር ተዋግተው አሸነፉ (8-16)

  • 18

    • ዮቶርና ሲፓራ ወደ ሙሴ መጡ (1-12)

    • ሙሴ ፈራጆችን እንዲሾም ዮቶር መከረው (13-27)

  • 19

    • ሙሴ ወደ ሲና ተራራ ወጣ (1-25)

      • እስራኤላውያን የካህናት መንግሥት ይሆናሉ (5, 6)

      • ሕዝቡ አምላክ ፊት ለመቅረብ ተቀደሰ (14, 15)

  • 20

    • አሥሩ ትእዛዛት (1-17)

    • እስራኤላውያን በተራራው ላይ ባዩት ትዕይንት የተነሳ ፈሩ (18-21)

    • አምልኮን በተመለከተ የተሰጠ መመሪያ (22-26)

  • 21

    • ለእስራኤላውያን የተሰጡ ድንጋጌዎች (1-36)

      • ከዕብራውያን ባሮች ጋር በተያያዘ (2-11)

      • በባልንጀራ ላይ ከሚወሰድ የኃይል እርምጃ ጋር በተያያዘ (12-27)

      • ከእንስሳት ጋር በተያያዘ (28-36)

  • 22

    • ለእስራኤላውያን የተሰጡ ድንጋጌዎች (1-31)

      • ከስርቆት ጋር በተያያዘ (1-4)

      • በእህል ላይ ከሚደርስ ጉዳት ጋር በተያያዘ (5, 6)

      • ካሳ ከመክፈልና ከንብረት ባለቤትነት ጋር በተያያዘ (7-15)

      • ያልታጨችን ድንግል አባብሎ የፆታ ግንኙነት ከመፈጸም ጋር በተያያዘ (16, 17)

      • ከአምልኮና ከማኅበራዊ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ (18-31)

  • 23

    • ለእስራኤላውያን የተሰጡ ድንጋጌዎች (1-19)

      • ከሐቀኝነትና ፍትሐዊ ከመሆን ጋር በተያያዘ (1-9)

      • ከሰንበትና ከበዓላት ጋር በተያያዘ (10-19)

    • እስራኤላውያንን የሚመራቸው መልአክ (20-26)

    • ምድሩን መውረስና ወሰን መከለል (27-33)

  • 24

    • ሕዝቡ ቃል ኪዳኑን ለማክበር ተስማማ (1-11)

    • ሙሴ በሲና ተራራ ላይ (12-18)

  • 25

    • ለማደሪያ ድንኳኑ የሚሰጥ መዋጮ (1-9)

    • ታቦቱ (10-22)

    • ጠረጴዛው (23-30)

    • መቅረዙ (31-40)

  • 26

    • የማደሪያ ድንኳኑ (1-37)

      • የድንኳኑ ጨርቆች (1-14)

      • አራት ማዕዘን ቋሚዎችና መሰኪያዎቻቸው (15-30)

      • መጋረጃውና መከለያው (31-37)

  • 27

    • የሚቃጠል መባ የሚቀርብበት መሠዊያ (1-8)

    • የማደሪያ ድንኳኑ ግቢ (9-19)

    • ለመብራት የሚሆን ዘይት (20, 21)

  • 28

    • የካህናቱ አልባሳት (1-5)

    • ኤፉዱ (6-14)

    • የደረት ኪሱ (15-30)

      • ኡሪሙና ቱሚሙ (30)

    • እጅጌ የሌለው ቀሚስ (31-35)

    • ጥምጥሙና በጥምጥሙ ላይ የሚደረገው ጠፍጣፋ ወርቅ (36-39)

    • ሌሎች የካህናት አልባሳት (40-43)

  • 29

    • የካህናቱ ሹመት (1-37)

    • በየቀኑ የሚቀርብ መባ (38-46)

  • 30

    • የዕጣን መሠዊያ (1-10)

    • የሕዝብ ቆጠራና ለማስተሰረያ የሚሆን ገንዘብ (11-16)

    • ለመታጠቢያ የሚያገለግለው የመዳብ ገንዳ (17-21)

    • በብልሃት የተቀመመ የቅብዓት ዘይት (22-33)

    • የቅዱሱ ዕጣን አቀማመም (34-38)

  • 31

    • በአምላክ መንፈስ የተሞሉ የእጅ ጥበብ ባለሙያዎች (1-11)

    • በአምላክና በእስራኤላውያን መካከል ምልክት የሆነው ሰንበት (12-17)

    • ሁለቱ የድንጋይ ጽላቶች (18)

  • 32

    • ለአምልኮ የተሠራው የወርቅ ጥጃ (1-35)

      • ሙሴ ለየት ያለ መዝሙር ሰማ (17, 18)

      • ሙሴ ሕጉ የተጻፈባቸውን ጽላቶች ሰባበራቸው (19)

      • ሌዋውያን በታማኝነት ከይሖዋ ጎን ቆሙ (26-29)

  • 33

    • አምላክ ሕዝቡን ገሠጸ (1-6)

    • የመገናኛ ድንኳኑ ከሰፈሩ ውጭ ተተከለ (7-11)

    • ሙሴ የይሖዋን ክብር ለማየት ጠየቀ (12-23)

  • 34

    • አዲስ የድንጋይ ጽላቶች ተዘጋጁ (1-4)

    • ሙሴ የይሖዋን ክብር አየ (5-9)

    • ቃል ኪዳኑ የያዘው ዝርዝር ሐሳብ በድጋሚ ተነገረ (10-28)

    • የሙሴ ፊት አንጸባረቀ (29-35)

  • 35

    • ሰንበትን አስመልክቶ የተሰጠ መመሪያ (1-3)

    • ለማደሪያ ድንኳኑ የሚሰጥ መዋጮ (4-29)

    • ባስልኤልና ኤልያብ በመንፈስ ተሞሉ (30-35)

  • 36

    • ከሚያስፈልገው በላይ ተዋጣ (1-7)

    • የማደሪያ ድንኳኑ አሠራር (8-38)

  • 37

    • የታቦቱ አሠራር (1-9)

    • ጠረጴዛው (10-16)

    • መቅረዙ (17-24)

    • የዕጣን መሠዊያው (25-29)

  • 38

    • የሚቃጠል መባ መሠዊያው (1-7)

    • የመዳብ ገንዳው (8)

    • የማደሪያ ድንኳኑ ግቢ (9-20)

    • የማደሪያ ድንኳኑ ዕቃዎች ተቆጥረው ተመዘገቡ (21-31)

  • 39

    • የካህናቱ አልባሳት አሠራር (1)

    • ኤፉዱ (2-7)

    • የደረት ኪሱ (8-21)

    • እጅጌ የሌለው ቀሚስ (22-26)

    • ሌሎቹ የካህናት አልባሳት (27-29)

    • ጥምጥሙ ላይ የሚደረገው ጠፍጣፋ ወርቅ (30, 31)

    • ሙሴ የማደሪያ ድንኳኑ በትክክል መሠራቱን ተመለከተ (32-43)

  • 40

    • የማደሪያ ድንኳኑ ተተከለ (1-33)

    • የይሖዋ ክብር የማደሪያ ድንኳኑን ሞላው (34-38)