ለቆሮንቶስ ሰዎች የተጻፈ የመጀመሪያው ደብዳቤ 4:1-21

  • “መጋቢዎች ታማኝ ሆነው መገኘት ይጠበቅባቸዋል” (1-5)

  • ክርስቲያን አገልጋዮች የሚያሳዩት ትሕትና (6-13)

    • “ከተጻፈው አትለፍ” (6)

    • ክርስቲያኖች እንደ ትርዒት ይታያሉ (9)

  • ጳውሎስ ለመንፈሳዊ ልጆቹ ያስባል (14-21)

4  እንግዲህ ሰው እኛን የክርስቶስ አገልጋዮችና* የአምላክ ቅዱስ ሚስጥር በአደራ የተሰጠን መጋቢዎች እንደሆን አድርጎ ሊቆጥረን ይገባል።+  በዚህ ረገድ መጋቢዎች ታማኝ ሆነው መገኘት ይጠበቅባቸዋል።  በእናንተም ሆነ በሰዎች ሸንጎ* ብመረመር ለእኔ ምንም ትርጉም የለውም። እኔም እንኳ ራሴን አልመረምርም።  ምክንያቱም ሕሊናዬ በሁሉም ነገር ንጹሕ ነው። ሆኖም ይህ ጻድቅ መሆኔን ያረጋግጣል ማለት አይደለም፤ እኔን የሚመረምረኝ ይሖዋ* ነው።+  ስለዚህ ጊዜው ከመድረሱ በፊት በምንም ነገር ላይ አትፍረዱ፤+ ጌታ እስኪመጣ ድረስ ጠብቁ። እሱ በጨለማ ውስጥ የተሰወረውን ነገር ወደ ብርሃን ያወጣዋል፤ እንዲሁም በልብ ውስጥ ያለውን ሐሳብ ይገልጣል፤ በዚያን ጊዜ እያንዳንዱ ሰው ከአምላክ ምስጋናውን ይቀበላል።+  እንግዲህ ወንድሞች፣ አንዱን ከሌላው በማስበለጥ እንዳትታበዩ፣+ ለእናንተው ጥቅም ራሴንና አጵሎስን+ ምሳሌ አድርጌ በማቅረብ እነዚህን ነገሮች የተናገርኩት “ከተጻፈው አትለፍ” የሚለውን ደንብ እንድትማሩ ነው።  ለመሆኑ አንተን ከሌላው የተለየህ እንድትሆን ያደረገህ ማን ነው? ደግሞስ ያልተቀበልከው ምን ነገር አለ?+ ከተቀበልክ ደግሞ እንዳልተቀበልክ ሆነህ የምትኩራራው ለምንድን ነው?  እንግዲህ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ አግኝታችኋል ማለት ነዋ! ባለጠጎች ሆናችኋላ! ያለእኛ ነግሣችኋል+ ማለት ነዋ! እኛም ከእናንተ ጋር መንገሥ እንድንችል ነገሥታት ሆናችሁ መግዛት ጀምራችሁ ቢሆን ምንኛ ደስ ባለኝ ነበር!+  አምላክ እኛን ሐዋርያቱን ሞት እንደተፈረደባቸው+ ሰዎች መጨረሻ ላይ ወደ መድረክ እንድንወጣ ያደረገን ይመስለኛል፤ ምክንያቱም ለዓለም፣ ለመላእክትና ለሰዎች ትርዒት ሆነናል።+ 10  እኛ በክርስቶስ የተነሳ ሞኞች ነን፤+ እናንተ ግን በክርስቶስ የተነሳ ልባሞች ናችሁ፤ እኛ ደካሞች ነን፤ እናንተ ግን ጠንካሮች ናችሁ፤ እናንተ የተከበራችሁ ናችሁ፤ እኛ ግን ተዋርደናል። 11  እስከዚህ ሰዓት ድረስ እየተራብንና+ እየተጠማን፣+ እየተራቆትን፣ እየተደበደብንና*+ ቤት አጥተን እየተንከራተትን እንገኛለን፤ 12  እንዲሁም በገዛ እጃችን እየሠራን እንለፋለን።+ ሲሰድቡን እንባርካለን፤+ ስደት ሲያደርሱብን በትዕግሥት እናሳልፋለን፤+ 13  ስማችንን ሲያጠፉ በለዘበ አንደበት እንመልሳለን፤*+ እስካሁን ድረስ የዓለም ጉድፍና* የሁሉ ነገር ጥራጊ እንደሆንን ተደርገን እንታያለን። 14  እነዚህን ነገሮች የምጽፍላችሁ ላሳፍራችሁ ብዬ ሳይሆን እንደተወደዳችሁ ልጆቼ አድርጌ ልመክራችሁ ነው። 15  ምንም እንኳ በክርስቶስ 10,000 ሞግዚቶች* ሊኖሯችሁ ቢችልም ብዙ አባቶች እንደሌሏችሁ ግን የተረጋገጠ ነው፤ በምሥራቹ አማካኝነት በክርስቶስ ኢየሱስ እኔ አባታችሁ ሆኛለሁና።+ 16  ስለዚህ እኔን እንድትመስሉ እለምናችኋለሁ።+ 17  በጌታ ልጄ የሆነውን የምወደውንና ታማኝ የሆነውን ጢሞቴዎስን የምልክላችሁ ለዚህ ነው። እሱም በየስፍራው በሚገኙ ጉባኤዎች ሁሉ ሳስተምር የምጠቀምባቸውን ይኸውም ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር በተያያዘ አገልግሎቴን የማከናውንባቸውን ዘዴዎች* ያሳስባችኋል።+ 18  አንዳንዶች እኔ ወደ እናንተ የማልመጣ መስሏቸው በኩራት ተወጥረዋል። 19  ይሁንና ይሖዋ* ከፈቀደ በቅርቡ ወደ እናንተ እመጣለሁ፤ በዚያን ጊዜም እነዚህ በኩራት የተወጠሩ ሰዎች የሚናገሩትን ነገር ሳይሆን የአምላክ ኃይል ይኖራቸው እንደሆነ ማወቅ እፈልጋለሁ። 20  የአምላክ መንግሥት የወሬ ጉዳይ ሳይሆን የኃይል ጉዳይ ነውና። 21  ለመሆኑ የትኛው ይሻላችኋል? ዱላ+ ይዤ ልምጣ ወይስ በፍቅርና በገርነት መንፈስ ልምጣ?

የግርጌ ማስታወሻ

ወይም “የበታቾችና።”
ወይም “ፍርድ ቤት።”
ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።
ወይም “በቡጢ እየተመታንና።”
ቃል በቃል “እንለማመጣለን።”
ወይም “ቆሻሻና፤ ትርኪ ምርኪና።”
ወይም “አስተማሪዎች።”
ቃል በቃል “መንገዶች።”
ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።