ለቆሮንቶስ ሰዎች የተጻፈ የመጀመሪያው ደብዳቤ 5:1-13

  • በጉባኤው ውስጥ የፆታ ብልግና ተፈጸመ (1-5)

  • ጥቂት እርሾ ሊጡን ሁሉ ያቦካዋል (6-8)

  • “ክፉውን ሰው ከመካከላችሁ አስወግዱት” (9-13)

5  በመካከላችሁ የፆታ ብልግና*+ እንደተፈጸመ ይወራል፤ እንዲህ ዓይነቱ ብልግና* ደግሞ በአሕዛብ መካከል እንኳ ታይቶ አይታወቅም፤ ከአባቱ ሚስት ጋር የሚኖር ሰው አለ ተብሏል።+  ታዲያ በዚህ ትኩራራላችሁ? ይልቁንም በዚህ ማዘንና+ ድርጊቱን የፈጸመውን ሰው ከመካከላችሁ ማስወጣት አይገባችሁም?+  ምንም እንኳ እኔ በአካል ከእናንተ ጋር ባልሆንም በመንፈስ ከእናንተ ጋር ነኝ፤ ደግሞም እንዲህ ያለ ድርጊት በፈጸመው ሰው ላይ አብሬያችሁ ያለሁ ያህል ሆኜ ፈርጄበታለሁ።  በጌታችን በኢየሱስ ስም አንድ ላይ በምትሰበሰቡበት ጊዜ እኔም በጌታችን በኢየሱስ ኃይል በመንፈስ ከእናንተ ጋር እንደምሆን በመገንዘብ  እንዲህ ያለውን ሰው ለሰይጣን አሳልፋችሁ ልትሰጡት ይገባል፤+ ይህም እሱ በጉባኤው ላይ ያሳደረው መጥፎ ተጽዕኖ እንዲወገድና* የጉባኤው መንፈስ በጌታ ቀን ባለበት ሁኔታ እንዲቀጥል ነው።+  መመካታችሁ መልካም አይደለም። ጥቂት እርሾ ሊጡን ሁሉ እንደሚያቦካው አታውቁም?+  አዲስ ሊጥ እንድትሆኑ አሮጌውን እርሾ አስወግዱ፤ ምክንያቱም የፋሲካችን በግ+ የሆነው ክርስቶስ ስለተሠዋ+ ከእርሾ ነፃ ናችሁ።  ስለዚህ በዓሉን+ በአሮጌ እርሾ እንዲሁም በክፋትና በኃጢአት እርሾ ሳይሆን እርሾ በሌለበት በቅንነትና በእውነት ቂጣ እናክብር።  ከሴሰኞች* ጋር መግጠማችሁን እንድትተዉ* በደብዳቤዬ ላይ ጽፌላችሁ ነበር፤ 10  እንዲህ ስል ግን በአጠቃላይ ከዚህ ዓለም+ ሴሰኞች፣* ስግብግብ ሰዎች፣ ቀማኞች ወይም ጣዖት አምላኪዎች ጋር አትገናኙ ማለቴ አይደለም። እንዲህ ቢሆንማ ኖሮ ጨርሶ ከዓለም መውጣት ያስፈልጋችሁ ነበር።+ 11  አሁን ግን የጻፍኩላችሁ፣ ወንድም ተብሎ እየተጠራ ሴሰኛ* ወይም ስግብግብ+ ወይም ጣዖት አምላኪ ወይም ተሳዳቢ ወይም ሰካራም+ ወይም ቀማኛ+ ከሆነ ማንኛውም ሰው ጋር መግጠማችሁን እንድትተዉ*+ አልፎ ተርፎም እንዲህ ካለው ሰው ጋር ምግብ እንኳ እንዳትበሉ ነው። 12  በውጭ ባሉ* ሰዎች ላይ የምፈርደው እኔ ምን አግብቶኝ ነው? በውስጥ ባሉት ሰዎች ላይ እናንተ አትፈርዱም? 13  በውጭ ባሉት ላይ አምላክ ይፈርዳል።+ “ክፉውን ሰው ከመካከላችሁ አስወግዱት።”+

የግርጌ ማስታወሻ

ግሪክኛ፣ ፖርኒያ። የቃላት መፍቻው ላይ “የፆታ ብልግና” የሚለውን ተመልከት።
ግሪክኛ፣ ፖርኒያ። የቃላት መፍቻው ላይ “የፆታ ብልግና” የሚለውን ተመልከት።
ቃል በቃል “ሥጋው እንዲጠፋና።”
የቃላት መፍቻው ላይ “የፆታ ብልግና” የሚለውን ተመልከት።
ወይም “እንዳትቀራረቡ።”
የቃላት መፍቻው ላይ “የፆታ ብልግና” የሚለውን ተመልከት።
የቃላት መፍቻው ላይ “የፆታ ብልግና” የሚለውን ተመልከት።
ወይም “እንዳትቀራረቡ።”
ወይም “የክርስቲያን ጉባኤ አባል ባልሆኑ።”