ለተሰሎንቄ ሰዎች የተጻፈ የመጀመሪያው ደብዳቤ 1:1-10

  • ሰላምታ (1)

  • የተሰሎንቄ ክርስቲያኖች ላሳዩት እምነት የቀረበ ምስጋና (2-10)

1  ከጳውሎስ፣ ከስልዋኖስና*+ ከጢሞቴዎስ፤+ አባት ከሆነው አምላክና ከጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር አንድነት ላለው የተሰሎንቄ ሰዎች ጉባኤ፦ የአምላክ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።  ሁላችሁንም በጸሎታችን+ በጠቀስን ቁጥር ሁልጊዜ አምላክን እናመሰግናለን፤  የእምነት ሥራችሁን፣ ከፍቅር የመነጨ ድካማችሁንና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ተስፋ በማድረጋችሁ+ የተነሳ የምታሳዩትን ጽናት በአምላካችንና በአባታችን ፊት ዘወትር እናስባለን።  አምላክ የሚወዳችሁ ወንድሞች፣ እሱ እንደመረጣችሁ እናውቃለን፤  ምክንያቱም የሰበክንላችሁ ምሥራች ወደ እናንተ የመጣው በቃል ብቻ ሳይሆን በኃይልና በመንፈስ ቅዱስ እንዲሁም በጠንካራ እምነት ነው። ደግሞም ለእናንተ ስንል በመካከላችሁ ምን ዓይነት ሰዎች ሆነን እንደኖርን ታውቃላችሁ።  ብዙ መከራ ቢደርስባችሁም+ ቃሉን ከመንፈስ ቅዱስ በሚገኝ ደስታ ስለተቀበላችሁ የእኛንም+ ሆነ የጌታን+ አርዓያ ተከትላችኋል፤  በመሆኑም በመቄዶንያና በአካይያ ለሚገኙ አማኞች ሁሉ ምሳሌ ሆናችኋል።  የይሖዋ* ቃል ከእናንተ ወጥቶ የተሰማው በመቄዶንያና በአካይያ ብቻ አይደለም፤ ከዚህ ይልቅ በአምላክ ላይ ያላችሁ እምነት በሌሎች ቦታዎችም ሁሉ ተሰራጭቷል፤+ ስለዚህ እኛ ምንም መናገር አያስፈልገንም።  ምክንያቱም መጀመሪያ ከእናንተ ጋር እንዴት እንደተገናኘን እንዲሁም ሕያው የሆነውንና እውነተኛውን አምላክ ለማገልገል ጣዖቶቻችሁን በመተው+ እንዴት ወደ አምላክ እንደተመለሳችሁ እነሱ ራሳቸው ሁልጊዜ ይናገራሉ፤ 10  በተጨማሪም ወደ አምላክ የተመለሳችሁት ከሞት ያስነሳውንና ከሚመጣው ቁጣ+ የሚታደገንን የልጁን ይኸውም የኢየሱስን ከሰማይ መምጣት ለመጠባበቅ ነው።+

የግርጌ ማስታወሻ

ሲላስ ተብሎም ይጠራል።
ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።