በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የአንደኛ ነገሥት መጽሐፍ

ምዕራፎች

የመጽሐፉ ይዘት

  • 1

    • አቢሻግ የዳዊት ሞግዚት ሆነች (1-4)

    • አዶንያስ መንገሥ ፈለገ (5-10)

    • ናታንና ቤርሳቤህ እርምጃ ወሰዱ (11-27)

    • ዳዊት ሰለሞንን እንዲቀቡት አዘዘ (28-40)

    • አዶንያስ የመሠዊያውን ቀንዶች ያዘ (41-53)

  • 2

    • ዳዊት ለሰለሞን መመሪያ ሰጠው (1-9)

    • ዳዊት ሞተ፤ ሰለሞን ነገሠ (10-12)

    • አዶንያስ የጠነሰሰው ሴራ ሕይወቱን አሳጣው (13-25)

    • አብያታር ተባረረ፤ ኢዮዓብ ተገደለ (26-35)

    • ሺምአይ ተገደለ (36-46)

  • 3

    • ሰለሞን የፈርዖንን ሴት ልጅ አገባ (1-3)

    • ይሖዋ ለሰለሞን በሕልም ተገለጠለት (4-15)

      • ሰለሞን ጥበብ ለማግኘት ጠየቀ (7-9)

    • ሰለሞን ሁለት እናቶችን ዳኘ (16-28)

  • 4

    • የሰለሞን አስተዳደር (1-19)

    • በሰለሞን ግዛት የነበረው ብልጽግና (20-28)

      • እያንዳንዱ ሰው ከወይኑና ከበለስ ዛፉ ሥር ያለስጋት ይኖር ነበር (25)

    • የሰለሞን ጥበብና የተናገራቸው ምሳሌዎች (29-34)

  • 5

    • ንጉሥ ኪራም የግንባታ ቁሳቁሶችን ለሰለሞን ላከ (1-12)

    • ሰለሞን የግዳጅ ሥራ የሚሠሩ ሰዎችን መለመለ (13-18)

  • 6

    • ሰለሞን ቤተ መቅደሱን ሠራ (1-38)

      • የውስጠኛው ክፍል (19-22)

      • ኪሩቦች (23-28)

      • ግድግዳው ላይ የተቀረጹት ምስሎች፣ በሮቹና የውስጠኛው ግቢ (29-36)

      • ቤተ መቅደሱን ገንብቶ ለመጨረስ ሰባት ዓመት ገደማ ፈጀ (37, 38)

  • 7

    • የሰለሞን ቤተ መንግሥት (1-12)

    • ከፍተኛ ችሎታና ልምድ የነበረው ኪራም ሰለሞንን ረዳው (13-47)

      • ሁለቱ የመዳብ ዓምዶች (15-22)

      • ከቀለጠ ብረት የተሠራው ባሕር (23-26)

      • አሥሩ የዕቃ ማጓጓዣ ጋሪዎችና የመዳብ ገንዳዎቹ (27-39)

    • ከወርቅ የተሠሩት ዕቃዎች (48-51)

  • 8

    • ታቦቱን ቤተ መቅደሱ ውስጥ አስቀመጡት (1-13)

    • ሰለሞን ለሕዝቡ ንግግር አቀረበ (14-21)

    • ሰለሞን ቤተ መቅደሱ ሲወሰን ያቀረበው ጸሎት (22-53)

    • ሰለሞን ሕዝቡን ባረከ (54-61)

    • የቀረቡት መሥዋዕቶችና የውሰናው በዓል (62-66)

  • 9

    • ይሖዋ ዳግመኛ ለሰለሞን ተገለጠለት (1-9)

    • ሰለሞን ለንጉሥ ኪራም የሰጠው ስጦታ (10-14)

    • ሰለሞን ያከናወናቸው የተለያዩ ግንባታዎች (15-28)

  • 10

    • የሳባ ንግሥት ሰለሞንን ልትጠይቀው መጣች (1-13)

    • ሰለሞን የነበረው ብዙ ሀብት (14-29)

  • 11

    • የሰለሞን ሚስቶች ልቡ ወደ ሌላ እንዲያዘነብል አደረጉት (1-13)

    • ሰለሞን ተቃዋሚዎች ተነሱበት (14-25)

    • ኢዮርብዓም አሥር ነገዶች እንደሚሰጡት ቃል ተገባለት (26-40)

    • ሰለሞን ሞተ፤ ሮብዓም ነገሠ (41-43)

  • 12

    • ሮብዓም ለሕዝቡ የሰጠው መጥፎ ምላሽ (1-15)

    • አሥሩ ነገዶች ዓመፁ (16-19)

    • ኢዮርብዓም የእስራኤል ንጉሥ ሆነ (20)

    • ሮብዓም ከእስራኤላውያን ጋር እንዳይዋጋ ተነገረው (21-24)

    • ኢዮርብዓም ያቋቋመው የጥጃ አምልኮ (25-33)

  • 13

    • ቤቴል ስለሚገኘው መሠዊያ የተነገረ ትንቢት (1-10)

      • መሠዊያው ተሰነጠቀ (5)

    • የእውነተኛው አምላክ ሰው (11-34)

  • 14

    • አኪያህ ስለ ኢዮርብዓም የተናገረው ትንቢት (1-20)

    • ሮብዓም በይሁዳ ላይ የነገሠበት ጊዜ (21-31)

      • ሺሻቅ ያካሄደው ወረራ (25, 26)

  • 15

    • አብያም በይሁዳ ነገሠ (1-8)

    • አሳ በይሁዳ ላይ መግዛት ጀመረ (9-24)

    • ናዳብ የእስራኤል ንጉሥ ሆነ (25-32)

    • ባኦስ የእስራኤል ንጉሥ ሆነ (33, 34)

  • 16

    • በባኦስ ላይ የተነገረው የይሖዋ ቃል (1-7)

    • ኤላህ በእስራኤል ላይ ነገሠ (8-14)

    • ዚምሪ በእስራኤል ላይ ነገሠ (15-20)

    • ኦምሪ በእስራኤል ላይ ነገሠ (21-28)

    • አክዓብ በእስራኤል ላይ ነገሠ (29-33)

    • ሂኤል ኢያሪኮን መልሶ ገነባ (34)

  • 17

    • ኤልያስ ድርቅ እንደሚከሰት ትንቢት ተናገረ (1)

    • ኤልያስን ቁራዎች መገቡት (2-7)

    • ኤልያስ በሰራፕታ ወደምትገኘው መበለት ሄደ (8-16)

    • የመበለቷ ልጅ ሞተ፤ ከዚያም ከሞት ተነሳ (17-24)

  • 18

    • ኤልያስ ከአብድዩና ከአክዓብ ጋር ተገናኘ (1-18)

    • ኤልያስ በቀርሜሎስ ተራራ ላይ የባአል ነቢያትን ተገዳደረ (19-40)

      • “በሁለት ሐሳብ የምታነክሱት እስከ መቼ ነው?” (21)

    • የሦስት ዓመት ተኩሉ ድርቅ አበቃ (41-46)

  • 19

    • ኤልያስ ከኤልዛቤል ሸሸ (1-8)

    • ይሖዋ ለኤልያስ በኮሬብ ተገለጠለት (9-14)

    • ኤልያስ ሃዛኤልን፣ ኢዩንና ኤልሳዕን እንዲቀባቸው ተነገረው (15-18)

    • ኤልሳዕ የኤልያስ ተተኪ እንዲሆን ተሾመ (19-21)

  • 20

    • ሶርያውያን በአክዓብ ላይ ጦርነት አወጁ (1-12)

    • አክዓብ ሶርያውያንን ድል አደረገ (13-34)

    • ስለ አክዓብ የተነገረ ትንቢት (35-43)

  • 21

    • አክዓብ የናቡቴን የወይን እርሻ ለመውሰድ ፈለገ (1-4)

    • ኤልዛቤል ናቡቴን አስገደለችው (5-16)

    • ኤልያስ በአክዓብ ላይ የተናገረው የፍርድ መልእክት (17-26)

    • አክዓብ ራሱን አዋረደ (27-29)

  • 22

    • ኢዮሳፍጥ ከአክዓብ ጋር ግንባር ፈጠረ (1-12)

    • ሚካያህ ትንቢት ተናገረ (13-28)

      • አንድ መንፈስ አክዓብን እንደሚያሞኘው ተናገረ (21, 22)

    • አክዓብ ራሞትጊልያድ ላይ ተገደለ (29-40)

    • ኢዮሳፍጥ በይሁዳ ላይ የነገሠበት ጊዜ (41-50)

    • አካዝያስ በእስራኤል ላይ ነገሠ (51-53)