አንደኛ ዜና መዋዕል 16:1-43
16 የእውነተኛውን አምላክ ታቦት አምጥተው ዳዊት በተከለለት ድንኳን ውስጥ አስቀመጡት፤+ ከዚያም የሚቃጠሉ መባዎችንና የኅብረት መሥዋዕቶችን በእውነተኛው አምላክ ፊት አቀረቡ።+
2 ዳዊት የሚቃጠሉትን መባዎችና+ የኅብረት መሥዋዕቶቹን+ አቅርቦ ሲጨርስ ሕዝቡን በይሖዋ ስም ባረከ።
3 በተጨማሪም ለእስራኤላውያን ሁሉ፣ ለእያንዳንዱ ወንድና ሴት አንድ ዳቦ፣ አንድ የቴምር ጥፍጥፍና አንድ የዘቢብ ጥፍጥፍ አከፋፈለ።
4 ከዚያም የእስራኤልን አምላክ ይሖዋን ያከብሩ፣* ያመሰግኑና ያወድሱ ዘንድ የተወሰኑ ሌዋውያንን በይሖዋ ታቦት ፊት እንዲያገለግሉ ሾመ።+
5 መሪው አሳፍ+ ነበር፤ ከእሱ ቀጥሎ ዘካርያስ ሁለተኛ ሆኖ ተሾመ፤ የኢዔል፣ ሸሚራሞት፣ የሂኤል፣ ማቲትያህ፣ ኤልያብ፣ በናያህ፣ ኦቤድዔዶም እና የኢዔል+ ባለ አውታር መሣሪያዎችና በገና ይጫወቱ ነበር፤+ አሳፍ ደግሞ ሲምባል ይጫወት ነበር፤+
6 ካህናቱ በናያህ እና ያሃዚኤል በእውነተኛው አምላክ የቃል ኪዳን ታቦት ፊት ዘወትር መለከት ይነፉ ነበር።
7 በዚያ ቀን ዳዊት ለመጀመሪያ ጊዜ ለይሖዋ የምስጋና መዝሙር በማቀናበር አሳፍና+ ወንድሞቹ እንዲዘምሩት ሰጣቸው፦
8 “ይሖዋን አመስግኑ፤+ ስሙን ጥሩ፤ሥራውን በሕዝቦች መካከል አስታውቁ!+
9 ለእሱ ዘምሩ፤ የውዳሴም መዝሙር ዘምሩለት፤+አስደናቂ በሆኑት ሥራዎቹ ሁሉ ላይ አሰላስሉ።*+
10 በቅዱስ ስሙ ተኩራሩ።+
ይሖዋን የሚፈልጉ ሰዎች፣ ልባቸው ሐሴት ያድርግ።+
11 ይሖዋንና ብርታቱን ፈልጉ።+
ፊቱን ሁልጊዜ እሹ።+
12 ያከናወናቸውን አስደናቂ ሥራዎች፣ተአምራቱንና የተናገረውን ፍርድ አስታውሱ፤+
13 እናንተ የአገልጋዩ የእስራኤል ዘሮች፣+እሱ የመረጣችሁ የያዕቆብ ልጆች፣+ ይህን አስታውሱ።
14 እሱ ይሖዋ አምላካችን ነው።+
ፍርዱ በመላው ምድር ላይ ነው።+
15 ቃል ኪዳኑን ለዘላለም አስቡ፤የገባውን ቃል* እስከ ሺህ ትውልድ አስታውሱ፤+
16 ከአብርሃም ጋር የገባውን ቃል ኪዳን፣+ለይስሐቅም በመሐላ የገባውን ቃል አስቡ።+
17 ቃሉን ለያዕቆብ ድንጋጌ፣ለእስራኤልም ዘላቂ ቃል ኪዳን አድርጎ አቋቋመ፤+
18 ‘የከነአንን ምድርርስትህ አድርጌ እሰጥሃለሁ’ አለ።+
19 ይህን የተናገረው በቁጥር ጥቂት፣አዎ፣ በጣም ጥቂት በነበራችሁ ጊዜ ነው፤ በምድሪቱም ላይ የባዕድ አገር ሰዎች ነበራችሁ።+
20 እነሱም ከአንዱ ብሔር ወደ ሌላው ብሔር፣ከአንዱም መንግሥት ወደ ሌላው ሕዝብ ተንከራተቱ።+
21 ማንም እንዲጨቁናቸው አልፈቀደም፤+ይልቁንም ለእነሱ ሲል ነገሥታትን ገሠጸ፤+
22 ‘የቀባኋቸውን አገልጋዮቼን አትንኩ፤በነቢያቴም ላይ አንዳች ክፉ ነገር አታድርጉ’ አላቸው።+
23 መላዋ ምድር ለይሖዋ ትዘምር!
ማዳኑን በየቀኑ አሳውቁ!+
24 ክብሩን በብሔራት፣አስደናቂ ሥራዎቹንም በሕዝቦች ሁሉ መካከል አስታውቁ።
25 ይሖዋ ታላቅ ነውና፤ ደግሞም እጅግ ሊወደስ ይገባዋል።
ከሌሎች አማልክት ሁሉ በላይ እጅግ የሚፈራ ነው።+
26 የሌሎች ሕዝቦች አማልክት ሁሉ ከንቱ ናቸው፤+ይሖዋ ግን ሰማያትን የሠራ አምላክ ነው።+
27 ሞገስና* ግርማ በፊቱ ናቸው፤+ብርታትና ደስታ እሱ በሚኖርበት ስፍራ ይገኛሉ።+
28 እናንተ የሕዝብ ነገዶች፣ ለይሖዋ የሚገባውን ስጡ፤ከክብሩና ከብርታቱ የተነሳ ለይሖዋ የሚገባውን ስጡ።+
29 ለስሙ የሚገባውን ክብር ለይሖዋ ስጡ፤+ስጦታ ይዛችሁ በፊቱ ቅረቡ።+
ያጌጠ የቅድስና ልብስ ለብሳችሁ* ለይሖዋ ስገዱ።*+
30 ምድር ሁሉ በፊቱ ተንቀጥቀጪ!
ምድር* በጽኑ ተመሥርታለች፤ ከቦታዋ ልትንቀሳቀስ* አትችልም።+
31 ሰማያት ሐሴት ያድርጉ፤ ምድርም ደስ ይበላት፤+በብሔራት መካከል ‘ይሖዋ ነገሠ!’ ብላችሁ አስታውቁ።+
32 ባሕሩና በውስጡ ያለው ነገር ሁሉ የነጎድጓድ ድምፅ ያሰማ፤መስኩና በላዩ ላይ ያለው ሁሉ ሐሴት ያድርግ።
33 የዱር ዛፎችም በይሖዋ ፊት እልል ይበሉ፤እሱ በምድር ላይ ለመፍረድ እየመጣ ነውና።*
34 ይሖዋ ጥሩ+ ስለሆነ ምስጋና አቅርቡለት፤ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።+
35 እንዲህም በሉ፦ ‘አዳኝ አምላካችን ሆይ፣ አድነን፤+ለቅዱስ ስምህ ምስጋና እንድናቀርብ፣+አንተንም በማወደስ ሐሴት እንድናደርግ፣*+ከብሔራት ሰብስበን፤ ከእነሱም ታደገን።
36 የእስራኤል አምላክ ይሖዋከዘላለም እስከ ዘላለም ይወደስ።’”
ሕዝቡም ሁሉ “አሜን!”* አሉ፤ ይሖዋንም አወደሱ።
37 ከዚያም ዳዊት በዕለታዊው ልማድ መሠረት+ በታቦቱ ፊት ዘወትር እንዲያገለግሉ+ አሳፍንና+ ወንድሞቹን በዚያ በይሖዋ የቃል ኪዳን ታቦት ፊት ተዋቸው።
38 ኦቤድዔዶምና 68 ወንድሞቹ እንዲሁም የየዱቱን ልጅ ኦቤድዔዶምና ሆሳ በር ጠባቂዎች ነበሩ፤
39 ካህኑ ሳዶቅና+ አብረውት የሚያገለግሉት ካህናት ደግሞ በገባኦን በሚገኘው ከፍ ያለ ቦታ፣+ በይሖዋ የማደሪያ ድንኳን ፊት ነበሩ፤
40 ይህም የሆነው የሚቃጠል መባ በሚቀርብበት መሠዊያ ላይ ዘወትር ጠዋትና ማታ ለይሖዋ የሚቃጠል መባ እንዲያቀርቡና ይሖዋ ለእስራኤል በሰጠው ትእዛዝ መሠረት በሕጉ ላይ የሰፈረውን ሁሉ እንዲፈጽሙ ነው።+
41 ይሖዋን ያመሰግኑ ዘንድ ሄማን እና የዱቱን+ እንዲሁም በስም ተጠቅሰው የተመረጡት የቀሩት ሰዎች ከእነሱ ጋር ነበሩ፤+ ምክንያቱም “ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል”፤+
42 ደግሞም መለከት፣ ሲምባልና እውነተኛውን አምላክ ለማወደስ የሚያገለግሉ የሙዚቃ መሣሪያዎችን* ይጫወቱ ዘንድ ሄማን+ እና የዱቱን ከእነሱ ጋር ነበሩ፤ የየዱቱን+ ወንዶች ልጆች ደግሞ በር ላይ ተመድበው ነበር።
43 ከዚያም ሕዝቡ ሁሉ ወደ ቤቱ ተመለሰ፤ ዳዊትም ቤተሰቡን ለመባረክ ወደ ቤቱ ሄደ።