አንደኛ ዜና መዋዕል 2:1-55

  • የእስራኤል 12 ወንዶች ልጆች (1, 2)

  • የይሁዳ ዘሮች (3-55)

2  የእስራኤል+ ወንዶች ልጆች እነዚህ ነበሩ፦ ሮቤል፣+ ስምዖን፣+ ሌዊ፣+ ይሁዳ፣+ ይሳኮር፣+ ዛብሎን፣+  ዳን፣+ ዮሴፍ፣+ ቢንያም፣+ ንፍታሌም፣+ ጋድ+ እና አሴር።+  የይሁዳ ወንዶች ልጆች ኤር፣ ኦናን እና ሴሎም ነበሩ። እነዚህ ሦስቱ ከከነአናዊቷ ከሹአ ሴት ልጅ የተወለዱለት ናቸው።+ የይሁዳ የበኩር ልጅ የሆነው ኤር ግን ይሖዋን አሳዘነ፤ እሱም ቀሰፈው።+  የይሁዳ ምራት ትዕማር+ ፋሬስን+ እና ዛራን ወለደችለት። የይሁዳ ወንዶች ልጆች በአጠቃላይ አምስት ነበሩ።  የፋሬስ ወንዶች ልጆች ኤስሮን እና ሃሙል+ ነበሩ።  የዛራ ወንዶች ልጆች ዚምሪ፣ ኤታን፣ ሄማን፣ ካልኮል እና ዳራ ነበሩ። በአጠቃላይ አምስት ነበሩ።  የካርሚ ልጅ* አካር* ነበር፤ እሱም ለጥፋት ከተለየው ነገር ጋር በተያያዘ እምነት በማጉደሉ በእስራኤል ላይ መዓት* አምጥቷል።+  የኤታን ልጅ* አዛርያስ ነበር።  ለኤስሮን የተወለዱለት ወንዶች ልጆች የራህምኤል፣+ ራም+ እና ከሉባይ* ነበሩ። 10  ራም አሚናዳብን+ ወለደ፤ አሚናዳብ የይሁዳ ዘሮች አለቃ የሆነውን ነአሶንን+ ወለደ። 11  ነአሶን ሳልማን+ ወለደ። ሳልማ ቦዔዝን+ ወለደ። 12  ቦዔዝ ኢዮቤድን ወለደ። ኢዮቤድ እሴይን+ ወለደ። 13  እሴይ የበኩር ልጁን ኤልያብን፣ ሁለተኛውን ልጁን አቢናዳብን፣+ ሦስተኛውን ልጁን ሺምአን፣+ 14  አራተኛውን ልጁን ናትናኤልን፣ አምስተኛውን ልጁን ራዳይን፣ 15  ስድስተኛውን ልጁን ኦጼምን እና ሰባተኛውን ልጁን ዳዊትን+ ወለደ። 16  እህቶቻቸው ጽሩያ እና አቢጋኤል+ ነበሩ። የጽሩያ ወንዶች ልጆች ሦስት ሲሆኑ እነሱም አቢሳ፣+ ኢዮዓብ+ እና አሳሄል+ ነበሩ። 17  አቢጋኤልም አሜሳይን+ ወለደች፤ የአሜሳይ አባት እስማኤላዊው የቴር ነበር። 18  የኤስሮን ልጅ ካሌብ* ከሚስቱ ከአዙባ እና ከይሪዖት ወንዶች ልጆች ወለደ፤ የእሷም ወንዶች ልጆች የሼር፣ ሾባብ እና አርዶን ነበሩ። 19  አዙባ ስትሞት ካሌብ ኤፍራታን+ አገባ፤ እሷም ሁርን+ ወለደችለት። 20  ሁር ዖሪን ወለደ። ዖሪ ባስልኤልን+ ወለደ። 21  ከዚያም ኤስሮን የጊልያድ+ አባት ከሆነው ከማኪር+ ሴት ልጅ ጋር ግንኙነት ፈጸመ። እሷን ያገባት በ60 ዓመቱ ነበር፤ እሷም ሰጉብን ወለደችለት። 22  ሰጉብ ያኢርን+ ወለደ፤ እሱም በጊልያድ+ ምድር 23 ከተሞች ነበሩት። 23  በኋላም ገሹር+ እና ሶርያ+ ቄናትንና+ በሥሯ* ያሉትን ከተሞች ጨምሮ ሃዎትያኢርን+ ይኸውም 60 ከተሞችን ወሰዱባቸው። እነዚህ ሁሉ የጊልያድ አባት የሆነው የማኪር ዘሮች ነበሩ። 24  ኤስሮን+ በካሌብ ኤፍራታ ከሞተ በኋላ የኤስሮን ሚስት የሆነችው አቢያህ፣ የተቆአ+ አባት የሆነውን አሽሁርን+ ወለደችለት። 25  የኤስሮን የበኩር ልጅ የራህምኤል የወለዳቸው ወንዶች ልጆች የበኩር ልጁ ራም፣ ቡናህ፣ ኦሬን፣ ኦጼም እና አኪያህ ነበሩ። 26  የራህምኤል፣ አታራ የተባለች ሌላ ሚስት አገባ። እሷም የኦናም እናት ነበረች። 27  የየራህምኤል የበኩር ልጅ የራም ወንዶች ልጆች ማአጽ፣ ያሚን እና ኤቄር ነበሩ። 28  የኦናም ወንዶች ልጆች ሻማይ እና ያዳ ነበሩ። የሻማይ ወንዶች ልጆች ናዳብ እና አቢሹር ነበሩ። 29  የአቢሹር ሚስት አቢሃይል ትባል ነበር፤ እሷም አህባንን እና ሞሊድን ወለደችለት። 30  የናዳብ ወንዶች ልጆች ሰሌድ እና አፋይም ነበሩ። ሆኖም ሰሌድ ወንዶች ልጆች ሳይወልድ ሞተ። 31  የአፋይም ልጅ* ይሽኢ ነበር። የይሽኢ ልጅ* ሸሻን ነበር፤ የሸሻን ልጅ* አህላይ ነበር። 32  የሻማይ ወንድም የያዳ ወንዶች ልጆች የቴር እና ዮናታን ነበሩ። የቴር ግን ወንዶች ልጆች ሳይወልድ ሞተ። 33  የዮናታን ወንዶች ልጆች ፐሌት እና ዛዛ ነበሩ። እነዚህ የየራህምኤል ዘሮች ነበሩ። 34  ሸሻን ሴቶች ብቻ እንጂ ወንዶች ልጆች አልነበሩትም። ሸሻን፣ ያርሃ የተባለ ግብፃዊ አገልጋይ ነበረው። 35  ሸሻን ለአገልጋዩ ለያርሃ ሴት ልጁን ዳረለት፤ እሷም አታይን ወለደችለት። 36  አታይ ናታንን ወለደ። ናታን ዛባድን ወለደ። 37  ዛባድ ኤፍላልን ወለደ። ኤፍላል ኢዮቤድን ወለደ። 38  ኢዮቤድ ኢዩን ወለደ። ኢዩ አዛርያስን ወለደ። 39  አዛርያስ ሄሌጽን ወለደ። ሄሌጽ ኤልዓሳን ወለደ። 40  ኤልዓሳ ሲስማይን ወለደ። ሲስማይ ሻሉምን ወለደ። 41  ሻሉም የቃምያህን ወለደ። የቃምያህ ኤሊሻማን ወለደ። 42  የየራህምኤል ወንድም የካሌብ*+ ወንዶች ልጆች፣ የዚፍ አባት የሆነው የበኩር ልጁ ሜሻ እንዲሁም የኬብሮን አባት የማሬሻህ ወንዶች ልጆች ነበሩ። 43  የኬብሮን ወንዶች ልጆች ቆሬ፣ ታጱአ፣ ራቄም እና ሼማ ነበሩ። 44  ሼማ የዮርቀአምን አባት ራሃምን ወለደ። ራቄም ሻማይን ወለደ። 45  የሻማይ ልጅ ማኦን ነበር። ማኦን ቤትጹርን+ ወለደ። 46  የካሌብ ቁባት ኤፋ ካራንን፣ ሞጻንና ጋዜዝን ወለደች። ካራን ጋዜዝን ወለደ። 47  የያህዳይ ወንዶች ልጆች ረጌም፣ ኢዮዓታም፣ ጌሻን፣ ጴሌጥ፣ ኤፋ እና ሻአፍ ነበሩ። 48  የካሌብ ቁባት ማአካ ሸበርን እና ቲርሃናን ወለደች። 49  ከጊዜ በኋላም የማድማናን+ አባት ሻአፍን እንዲሁም የማክበናን እና የጊባዓን+ አባት ሻዌን ወለደች። የካሌብ+ ሴት ልጅ አክሳ+ ትባል ነበር። 50  የካሌብ ዘሮች እነዚህ ነበሩ። የኤፍራታ+ የበኩር ልጅ የሆነው የሁር+ ወንዶች ልጆች እነዚህ ናቸው፦ የቂርያትየአሪም+ አባት ሾባል፣ 51  የቤተልሔም+ አባት ሳልማ እና የቤትጋዴር አባት ሃሬፍ። 52  የቂርያትየአሪም አባት የሾባል ልጆች ሃሮኤ እና የመኑሆት ሰዎች እኩሌታ ነበሩ። 53   የቂርያትየአሪም ወገኖች ይትራውያን፣+ ፑታውያን፣ ሹማታውያን እና ሚሽራውያን ነበሩ። ጾራውያን+ እና ኤሽታዖላውያን+ የተገኙት ከእነዚህ ወገኖች ነው። 54  የሳልማ ልጆች ቤተልሔም፣+ ነጦፋውያን፣ አትሮት ቤት ዮአብ፣ የማናሃታውያን ሰዎች እኩሌታና ጾራውያን ነበሩ። 55  በያቤጽ የሚኖሩት የጸሐፍት ወገኖች ቲራታውያን፣ ሺመአታውያን እና ሱካታውያን ነበሩ። እነዚህ የሬካብ+ ቤት አባት ከሆነው ከሃማት የተገኙት ቄናውያን+ ናቸው።

የግርጌ ማስታወሻ

ቃል በቃል “ወንዶች ልጆች።”
“መዓት አምጪ፤ ሞገስ የሚያሳጣ” የሚል ትርጉም አለው። ኢያሱ 7:1 ላይ አካን ተብሎም ተጠርቷል።
ወይም “ችግር፤ መጠላት።”
ቃል በቃል “ወንዶች ልጆች።”
በ1ዜና 2:18, 1942 ላይ ካሌብ ተብሎም ተጠርቷል።
በ1ዜና 2:9 ላይ ከሉባይ ተብሎም ተጠርቷል።
ወይም “በዙሪያዋ።”
ቃል በቃል “ወንዶች ልጆች።”
ቃል በቃል “ወንዶች ልጆች።”
ቃል በቃል “ወንዶች ልጆች።”
በ1ዜና 2:9 ላይ ከሉባይ ተብሎም ተጠርቷል።