አንደኛ ዜና መዋዕል 7:1-40

  • የይሳኮር ዘሮች (1-5)፣ የቢንያም ዘሮች (6-12)፣ የንፍታሌም ዘሮች (13)፣ የምናሴ ዘሮች (14-19)፣ የኤፍሬም ዘሮች (20-29)፣ እና የአሴር ዘሮች (30-40)

7  የይሳኮር ወንዶች ልጆች ቶላ፣ ፑሃ፣ ያሹብና ሺምሮን+ ሲሆኑ በአጠቃላይ አራት ነበሩ።  የቶላም ወንዶች ልጆች ዑዚ፣ ረፋያህ፣ የሪኤል፣ ያህማይ፣ ይብሳም እና ሸሙኤል ሲሆኑ የአባቶቻቸው ቤት መሪዎች ነበሩ። የቶላ ዘሮች ኃያላን ተዋጊዎች ነበሩ፤ በዳዊት ዘመን ቁጥራቸው 22,600 ነበር።  የዑዚ ዘሮች* ይዝራህያህ እና የይዝራህያህ ወንዶች ልጆች ይኸውም ሚካኤል፣ አብድዩ፣ ኢዩኤልና ይሽሺያህ ናቸው፤ አምስቱም አለቆች* ነበሩ።  እነሱም ብዙ ሚስቶችና ወንዶች ልጆች ስለነበሯቸው በየትውልድ ሐረጋቸው ከየአባቶቻቸው ቤት ለመዋጋት ዝግጁ የሆኑ 36,000 ወታደሮችን ያቀፈ ሠራዊት ነበራቸው።  ከይሳኮር ቤተሰቦች በሙሉ በትውልድ ሐረግ መዝገቡ ላይ የሰፈሩት ኃያላን ተዋጊዎች የሆኑት ወንድሞቻቸው በአጠቃላይ 87,000 ነበሩ።+  የቢንያም+ ወንዶች ልጆች ቤላ፣+ ቤኬር+ እና የዲአዔል+ ሲሆኑ በአጠቃላይ ሦስት ነበሩ።  የቤላ ወንዶች ልጆች ኤጽቦን፣ ዑዚ፣ ዑዚኤል፣ የሪሞት እና ኢሪ ሲሆኑ በአጠቃላይ አምስት ነበሩ፤ እነሱም የአባቶቻቸው ቤት መሪዎች እንዲሁም ኃያላን ተዋጊዎች ነበሩ፤ በትውልድ ሐረግ መዝገቡም ላይ የሰፈሩት 22,034 ነበሩ።+  የቤኬር ወንዶች ልጆች ዘሚራ፣ ኢዮአስ፣ ኤሊዔዘር፣ ኤሊዮዔናይ፣ ኦምሪ፣ የሬሞት፣ አቢያህ፣ አናቶት እና አለሜት ነበሩ፤ እነዚህ ሁሉ የቤኬር ወንዶች ልጆች ናቸው።  በየትውልድ ሐረጋቸውና በየዘሮቻቸው የተመዘገቡት በየአባቶቻቸው ቤት ያሉት መሪዎች 20,200 ኃያላን ተዋጊዎች ነበሩ። 10  የየዲአዔል+ ወንዶች ልጆች ቢልሃን እና የቢልሃን ወንዶች ልጆች ይኸውም የኡሽ፣ ቢንያም፣ ኤሁድ፣ ኬናአና፣ ዜታን፣ ተርሴስ እና አሂሻሐር ነበሩ። 11  እነዚህ ሁሉ የየዲአዔል ወንዶች ልጆች ሲሆኑ የየአባቶቻቸው ቤቶች መሪዎች እንዲሁም ሠራዊቱን ተቀላቅለው ለመዋጋት ዝግጁ የሆኑ 17,200 ኃያላን ተዋጊዎች ነበሩ። 12  የሹፒምና የሁፒም ቤተሰቦች* የኢር+ ልጆች ነበሩ፤ የሁሺም ልጆች ደግሞ የአሄር ዘሮች ነበሩ። 13  የንፍታሌም ወንዶች ልጆች+ ያህጺኤል፣ ጉኒ፣ የጼር እና ሻሉም ነበሩ፤ እነዚህ ሰዎች የባላ+ ዘሮች* ነበሩ። 14  የምናሴ ልጆች፦+ ሶርያዊት ቁባቱ የወለደችለት አስሪዔል። (እሷ የጊልያድን አባት ማኪርን+ ወለደች። 15  ማኪር፣ ሁፒምንና ሹፒምን ሚስት አጋባቸው፤ የእህቱም ስም ማአካ ይባላል።) ሁለተኛው ሰለጰአድ+ ተብሎ ይጠራል፤ ሆኖም ሰለጰአድ የወለደው ሴት ልጆችን ብቻ ነበር።+ 16  የማኪር ሚስት ማአካ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም ፔሬሽ አለችው፤ የወንድሙም ስም ሼሬሽ ይባል ነበር፤ ወንዶች ልጆቹም ዑላም እና ራቄም ነበሩ። 17  የዑላም ልጅ* ቤዳን ነበር። እነዚህ የምናሴ ልጅ፣ የማኪር ልጅ የጊልያድ ዘሮች ነበሩ። 18  እህቱም ሞሌኬት ትባል ነበር። እሷም ኢሽሆድን፣ አቢዔዜርንና ማህላን ወለደች። 19  የሸሚዳ ወንዶች ልጆችም አሂያን፣ ሴኬም፣ ሊቅሂ እና አኒዓም ነበሩ። 20  ሹተላ የኤፍሬም+ ልጅ ነበር፤ የሹተላ+ ልጅ ቤሬድ፣ የቤሬድ ልጅ ታሃት፣ የታሃት ልጅ ኤልዓዳ፣ የኤልዓዳ ልጅ ታሃት፣ 21  የታሃት ልጅ ዛባድ፣ የዛባድ ልጅ ሹተላ ነበር፤ ኤጼር እና ኤልዓድም የኤፍሬም ልጆች ነበሩ። እነሱም መንጎች ለመዝረፍ በወረዱ ጊዜ የምድሪቱ ተወላጆች የሆኑት የጌት+ ሰዎች ገደሏቸው። 22  አባታቸው ኤፍሬም ለብዙ ቀናት አለቀሰ፤ ወንድሞቹም እሱን ለማጽናናት ይመጡ ነበር። 23  ከዚያም ከሚስቱ ጋር ግንኙነት ፈጸመ፤ እሷም ፀንሳ ወንድ ልጅ ወለደች። ሆኖም እሷ በወለደች ጊዜ በቤተሰቡ ላይ መከራ ደርሶ ስለነበር ስሙን በሪአ* አለው። 24  የሴት ልጁም ስም ሼኢራ ሲሆን እሷም የታችኛውንና+ የላይኛውን ቤትሆሮንን+ እንዲሁም ዑዜንሼራን የገነባች ነች። 25  ሬፋህ እና ሬሼፍ ወንዶች ልጆቹ ነበሩ፤ ሬሼፍ ቴላህን ወለደ፤ ቴላህ ታሃንን ወለደ፤ 26  ታሃን ላዳንን ወለደ፤ ላዳን አሚሁድን ወለደ፤ አሚሁድ ኤሊሻማን ወለደ፤ 27  ኤሊሻማ ነዌን ወለደ፤ ነዌ ኢያሱን*+ ወለደ። 28  ርስታቸውና ሰፈራቸው ቤቴልንና+ በሥሯ* ያሉትን ከተሞች፣ በስተ ምሥራቅ ናአራንን፣ በስተ ምዕራብ ደግሞ ጌዜርንና በሥሯ ያሉትን ከተሞች እንዲሁም ሴኬምንና በሥሯ ያሉትን ከተሞች ጨምሮ እስከ አያህና* በሥሯ እስካሉት ከተሞች ይደርሳል፤ 29  በምናሴም ዘሮች ወሰን በኩል ቤትሼንና+ በሥሯ ያሉት ከተሞች፣ ታአናክና+ በሥሯ ያሉት ከተሞች፣ መጊዶና+ በሥሯ ያሉት ከተሞች እንዲሁም ዶርና+ በሥሯ ያሉት ከተሞች ነበሩ። በእነዚህ ስፍራዎች የእስራኤል ልጅ የዮሴፍ ዘሮች ይኖሩ ነበር። 30  የአሴር ወንዶች ልጆች ይምናህ፣ ይሽዋ፣ ይሽዊ እና በሪአ+ ሲሆኑ እህታቸውም ሴራህ ትባላለች።+ 31  የበሪአ ወንዶች ልጆች ሄቤር እና የቢርዛይት አባት የሆነው ማልኪኤል ነበሩ። 32  ሄቤር ያፍሌጥን፣ ሾሜርን፣ ሆታምንና እህታቸውን ሹአን ወለደ። 33  የያፍሌጥ ወንዶች ልጆች ፓሳክ፣ ቢምሃል እና አሽዋት ነበሩ። እነዚህ የያፍሌጥ ልጆች ነበሩ። 34  የሼሜር* ወንዶች ልጆች አሂ፣ ሮህጋ፣ የሁባ እና አራም ነበሩ። 35  የወንድሙ የሄሌም* ወንዶች ልጆች ጾፋ፣ ይምና፣ ሼሌሽ እና አማል ነበሩ። 36  የጾፋ ወንዶች ልጆች ሱአ፣ ሃርኔፌር፣ ሹአል፣ ቤሪ፣ ይምራ፣ 37  ቤጼር፣ ሆድ፣ ሻማ፣ ሺልሻ፣ ይትራን እና ቤኤራ ነበሩ። 38  የየቴር ወንዶች ልጆች የፎኒ፣ ፒስጳ እና አራ ነበሩ። 39  የዑላ ወንዶች ልጆች ኤራ፣ ሃኒኤል እና ሪጽያ ነበሩ። 40  እነዚህ ሁሉ የአሴር ወንዶች ልጆችና የአባቶቻቸው ቤት መሪዎች ናቸው፤ እንዲሁም የተመረጡ ኃያላን ተዋጊዎች ሲሆኑ የሠራዊቱ አለቆች መሪዎች ነበሩ፤ ደግሞም በቤተሰባቸው መዝገብ ላይ እንደተጻፈው+ ለውጊያ ዝግጁ የሆኑ 26,000 ሰዎች+ በሠራዊቱ ውስጥ ይገኙ ነበር።

የግርጌ ማስታወሻ

ቃል በቃል “ራሶች።”
ቃል በቃል “ወንዶች ልጆች።”
ወይም “ሹፒምና ሁፒም።”
ቃል በቃል “ወንዶች ልጆች።”
ቃል በቃል “ወንዶች ልጆች።”
“ከመከራ ጋር” የሚል ትርጉም አለው።
ወይም “የሆሹዋን።” “ይሖዋ አዳኝ ነው” የሚል ትርጉም አለው።
ወይም “በዙሪያዋ።”
“ጋዛ” ማለትም ሊሆን ይችላል። ይሁንና በፍልስጤም የምትገኘውን ጋዛን አያመለክትም።
በ1ዜና 7:32 ላይ ሾሜር ተብሎም ተጠርቷል።
በ1ዜና 7:32 ላይ ከተጠቀሰው “ሆታም” ጋር አንድ ሳይሆን አይቀርም።