አንደኛ ዜና መዋዕል 8:1-40

  • የቢንያም ዘሮች (1-40)

    • የሳኦል የዘር ሐረግ (33-40)

8  ቢንያም+ የበኩር ልጁን ቤላን፣+ ሁለተኛ ልጁን አሽቤልን፣+ ሦስተኛ ልጁን አሃራሕን፣  አራተኛ ልጁን ኖሃንና አምስተኛ ልጁን ራፋን ወለደ።  የቤላ ወንዶች ልጆች እነዚህ ናቸው፦ አዳር፣ ጌራ፣+ አቢሁድ፣  አቢሹዓ፣ ንዕማን፣ አሆዓሕ፣  ጌራ፣ ሼፉፋን እና ሁራም።  እነዚህ የኤሁድ ወንዶች ልጆች ይኸውም ወደ ማናሃት በግዞት የተወሰዱ በጌባ+ ይኖሩ የነበሩ ቤተሰቦች መሪዎች ናቸው፦  ንዕማን፣ አኪያህ እና ጌራ፤ ሰዎቹን በዋነኝነት እየመራ ወደ ግዞት የወሰዳቸው ጌራ ነበር፤ እሱም ዑዛን እና አሂሑድን ወለደ።  ሻሃራይም ሰዎቹን ከሰደዳቸው በኋላ በሞዓብ ምድር* ልጆች ወለደ። ሁሺም እና ባዓራ ሚስቶቹ ነበሩ።*  ከሚስቱ ከሆዴሽ ዮባብን፣ ጺብያን፣ ሜሻን፣ ማልካምን፣ 10  የኡጽን፣ ሳክያህን እና ሚርማን ወለደ። እነዚህ ወንዶች ልጆቹ ሲሆኑ የየአባቶቻቸው ቤቶች መሪዎች ነበሩ። 11  ከሁሺም አቢጡብን እና ኤልጳዓልን ወለደ። 12  የኤልጳዓል ወንዶች ልጆች ኤቤር፣ ሚሻም፣ ኦኖን+ እንዲሁም ሎድንና+ በሥሯ* ያሉትን ከተሞች የቆረቆረው ሻሜድ፣ 13  በሪአ እና ሼማ ነበሩ። እነዚህ በአይሎን+ ይኖሩ የነበሩ የየአባቶቻቸው ቤቶች መሪዎች ናቸው። የጌትን ነዋሪዎች ያሳደዱት እነሱ ነበሩ። 14  ደግሞም አሂዮ፣ ሻሻቅ፣ የሬሞት፣ 15  ዘባድያህ፣ አራድ፣ ኤዴር፣ 16  ሚካኤል፣ ይሽጳ እና ዮሃ የበሪአ ወንዶች ልጆች ነበሩ፤ 17  ዘባድያህ፣ መሹላም፣ ሂዝቂ፣ ሄቤር፣ 18  ይሽመራይ፣ ይዝሊያ እና ዮባብ የኤልጳዓል ወንዶች ልጆች ነበሩ፤ 19  ያቂም፣ ዚክሪ፣ ዛብዲ፣ 20  ኤሊዔናይ፣ ጺለታይ፣ ኤሊዔል፣ 21  አዳያህ፣ ቤራያህ እና ሺምራት የሺምአይ ወንዶች ልጆች ነበሩ፤ 22  ይሽጳን፣ ኤቤር፣ ኤሊዔል፣ 23  አብዶን፣ ዚክሪ፣ ሃናን፣ 24  ሃናንያህ፣ ኤላም፣ አንቶቲያህ፣ 25  ይፍደያህ እና ጰኑኤል የሻሻቅ ወንዶች ልጆች ነበሩ፤ 26  ሻምሸራይ፣ ሸሃሪያህ፣ ጎቶልያ፣ 27  ያአሬሽያህ፣ ኤልያስ እና ዚክሪ የየሮሃም ወንዶች ልጆች ነበሩ። 28  እነዚህ በትውልድ ሐረግ መዝገቡ ላይ ተጽፎ በሚገኘው መሠረት የየአባቶቻቸው ቤቶች መሪዎች ነበሩ። የሚኖሩትም በኢየሩሳሌም ነበር። 29  የገባኦን አባት የኢዔል በገባኦን+ ይኖር ነበር። የሚስቱ ስም ማአካ ይባል ነበር።+ 30  የበኩር ልጁ አብዶን ሲሆን ሌሎቹ ልጆቹ ደግሞ ጹር፣ ቂስ፣ ባአል፣ ናዳብ፣ 31  ጌዶር፣ አሂዮ እና ዛከር ነበሩ። 32  ሚቅሎት ሺምአህን ወለደ። እነዚህ ሁሉ ከሌሎች ወንድሞቻቸው ጋር ሆነው በወንድሞቻቸው አቅራቢያ በኢየሩሳሌም ይኖሩ ነበር። 33  ኔር+ ቂስን ወለደ፤ ቂስ ሳኦልን+ ወለደ፤ ሳኦል ዮናታንን፣+ ሜልኪሳን፣+ አቢናዳብን+ እና ኤሽባዓልን*+ ወለደ። 34  የዮናታን ልጅ መሪበኣል*+ ነበር። መሪበኣል ሚክያስን ወለደ።+ 35  የሚክያስ ወንዶች ልጆች ፒቶን፣ ሜሌክ፣ ታሬአ እና አካዝ ነበሩ። 36  አካዝ የሆአዳን ወለደ፤ የሆአዳ አለሜትን፣ አዝማዌትን እና ዚምሪን ወለደ፤ ዚምሪ ሞጻን ወለደ። 37  ሞጻ ቢንአን ወለደ፤ ቢንአ ራፋህን ወለደ፤ ራፋህ ኤልዓሳን ወለደ፤ ኤልዓሳ አዜልን ወለደ። 38  አዜል ስድስት ወንዶች ልጆች የነበሩት ሲሆን ስማቸውም አዝሪቃም፣ ቦከሩ፣ እስማኤል፣ ሸአርያህ፣ አብድዩ እና ሃናን ነበር። እነዚህ ሁሉ የአዜል ወንዶች ልጆች ነበሩ። 39  የወንድሙ የኤሼቅ ወንዶች ልጆች የበኩር ልጁ ዑላም፣ ሁለተኛው ልጁ የኡሽ፣ ሦስተኛው ልጁ ኤሊፌሌት ነበሩ። 40  የዑላም ወንዶች ልጆች ቀስተኞችና* ኃያላን ተዋጊዎች የነበሩ ሲሆን 150 ልጆችና የልጅ ልጆች ነበሯቸው። እነዚህ ሁሉ የቢንያም ዘሮች ነበሩ።

የግርጌ ማስታወሻ

ቃል በቃል “ሜዳ።”
“ሚስቶቹን ይኸውም ሁሺምን እና ባዓራን ከሰደደ በኋላ በሞዓብ ምድር ልጆች ወለደ” ማለትም ሊሆን ይችላል።
ወይም “በዙሪያዋ።”
ኢሽቦሼት ተብሎም ተጠርቷል።
ሜፊቦስቴ ተብሎም ተጠርቷል።
ቃል በቃል “ደጋን የሚረግጡና።”