ለጢሞቴዎስ የተጻፈ የመጀመሪያው ደብዳቤ 2:1-15

  • ለሁሉም ዓይነት ሰዎች ጸልዩ (1-7)

    • አንድ አምላክ፣ አንድ መካከለኛ (5)

    • ለሁሉም የሚሆን ተመጣጣኝ ቤዛ (6)

  • ለወንዶችና ለሴቶች የተሰጠ መመሪያ (8-15)

    • ልከኛ አለባበስ (9, 10)

2  እንግዲህ ከሁሉ አስቀድሞ ሁሉንም ዓይነት ሰዎች በተመለከተ ምልጃ፣ ጸሎት፣ ልመናና ምስጋና እንዲቀርብ አሳስባለሁ፤  በተጨማሪም ነገሥታትንና በሥልጣን ላይ ያሉትን ሁሉ በተመለከተ እንዲሁ እንዲደረግ አሳስባለሁ፤+ ይህም ሙሉ በሙሉ ለአምላክ በማደርና ሁሉንም ነገር በትጋት በማከናወን* በጸጥታና በተረጋጋ ሁኔታ መኖራችንን እንቀጥል ዘንድ ነው።+  ይህም አዳኛችን በሆነው አምላክ+ ፊት መልካምና ተቀባይነት ያለው ነው፤  የእሱ ፈቃድ ሁሉም ዓይነት ሰዎች እንዲድኑና+ የእውነትን ትክክለኛ እውቀት እንዲያገኙ ነው።  አንድ አምላክ አለና፤+ በአምላክና በሰው መካከል+ ደግሞ አንድ መካከለኛ አለ፤+ እሱም ሰው የሆነው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤+  ራሱን ለሁሉ* ተመጣጣኝ ቤዛ አድርጎ ሰጠ፤+ በተወሰነለት ጊዜም የምሥክርነት ቃል የሚነገርለት ነገር ይህ ነው።  ሰባኪና ሐዋርያ+ ይኸውም እምነትንና እውነትን በተመለከተ የአሕዛብ አስተማሪ+ ሆኜ የተሾምኩት ለዚህ ምሥክርነት ሲባል ነው፤+ ይህን ስል እውነቱን እየተናገርኩ ነው እንጂ እየዋሸሁ አይደለም።  ስለዚህ በሁሉም ቦታ ወንዶች ቁጣንና+ ክርክርን+ አስወግደው ታማኝ እጆችን ወደ ላይ በማንሳት+ አዘውትረው እንዲጸልዩ እፈልጋለሁ።  በተመሳሳይም ሴቶች ፀጉር በመሸረብና በወርቅ ወይም በዕንቁ ወይም ደግሞ በጣም ውድ በሆነ ልብስ ሳይሆን በልከኝነትና በማስተዋል፣* ተገቢ በሆነ* ልብስ ራሳቸውን ያስውቡ፤+ 10  ለአምላክ ያደርን ነን የሚሉ ሴቶች ሊያደርጉት እንደሚገባ በመልካም ሥራ ይዋቡ።+ 11  ሴት ሙሉ በሙሉ በመገዛት+ በጸጥታ* ትማር። 12  ሴት ዝም እንድትል እንጂ እንድታስተምር ወይም በወንድ ላይ ሥልጣን እንዲኖራት አልፈቅድም።+ 13  በመጀመሪያ የተፈጠረው አዳም ነውና፤ ከዚያም ሔዋን ተፈጠረች።+ 14  በተጨማሪም አዳም አልተታለለም፤ ከዚህ ይልቅ ፈጽሞ የተታለለችውና+ ሕግ የተላለፈችው ሴቷ ናት። 15  ይሁን እንጂ ሴት ጤናማ አስተሳሰብ በመያዝ* በእምነት፣ በፍቅርና በቅድስና ብትጸና ልጅ በመውለድ+ ደህንነቷ ተጠብቆ* ትኖራለች።+

የግርጌ ማስታወሻ

ወይም “ቁም ነገረኛ በመሆን።”
ወይም “ለሁሉም ዓይነት ሰዎች።”
ወይም “በጥሩ የማመዛዘን ችሎታ።”
ወይም “በሚያስከብር።”
ወይም “በዝምታ፤ በእርጋታ።”
ወይም “በጥሩ የማመዛዘን ችሎታ።”
መንፈሳዊነቷ ተጠብቆ ትኖራለች ማለት ነው።