ለቆሮንቶስ ሰዎች የተጻፈ ሁለተኛው ደብዳቤ 3:1-18

  • “የምሥክር ወረቀት” (1-3)

  • “የአዲስ ቃል ኪዳን አገልጋዮች” (4-6)

  • አዲሱ ቃል ኪዳን ያለው የላቀ ክብር (7-18)

3  ብቁ መሆናችንን ለማሳየት ራሳችንን ለእናንተ እንደ አዲስ ማስተዋወቅ ያስፈልገናል? ወይስ እንደ አንዳንድ ሰዎች ለእናንተ ወይም ከእናንተ የምሥክር ወረቀት ያስፈልገን ይሆን?  ሰዎች ሁሉ የሚያውቁትና የሚያነብቡት በልባችን ላይ የተጻፈ ማስረጃችን እናንተ ራሳችሁ ናችሁ።+  ምክንያቱም እናንተ በቀለም ሳይሆን በሕያው አምላክ መንፈስ፣ በድንጋይ ጽላቶች+ ላይ ሳይሆን በሥጋ ጽላቶች ይኸውም በልብ ላይ፣+ አገልጋዮች+ በሆንነው በእኛ አማካኝነት የተጻፋችሁ የክርስቶስ ደብዳቤ እንደሆናችሁ በግልጽ ታይቷል።  በክርስቶስ በኩል በአምላክ ፊት እንዲህ ያለ እምነት አለን።  ብቃታችንን በገዛ ራሳችን ያገኘነው እንደሆነ አድርገን አናስብም፤ ከዚህ ይልቅ አስፈላጊውን ብቃት ያገኘነው ከአምላክ ነው፤+  እሱም የአዲስ ቃል ኪዳን+ አገልጋዮች ይኸውም የተጻፈ ሕግ+ ሳይሆን የመንፈስ አገልጋዮች እንድንሆን ብቁዎች አድርጎናል፤ የተጻፈው ሕግ ለሞት ፍርድ ይዳርጋልና፤+ መንፈስ ግን ሕያው ያደርጋል።+  የእስራኤል ልጆች፣ ከፊቱ ክብር የተነሳ የሙሴን ፊት ትኩር ብለው ማየት እስኪሳናቸው ድረስ+ የሞት ፍርድ የሚያስከትለውና በድንጋይ ላይ በፊደል የተቀረጸው ሕግ+ በክብር ይኸውም በሚጠፋ ክብር ከመጣ  የመንፈስ አገልግሎት+ እንዴት የላቀ ክብር አይኖረውም?+  ኩነኔ የሚያስከትለው የሕግ አገልግሎት+ ክብራማ+ ከሆነ ጽድቅ የሚያስገኘው አገልግሎትማ እንዴት እጅግ የላቀ ክብር አይኖረውም!+ 10  እንዲያውም በአንድ ወቅት ክብራማ የነበረው፣ ከእሱ የላቀ ክብር ያለው በመምጣቱ ምክንያት ክብሩ ተገፏል።+ 11  የሚጠፋው በክብር ከመጣ+ ጸንቶ የሚኖረውማ እንዴት የላቀ ክብር አይኖረውም!+ 12  እንዲህ ዓይነት ተስፋ ስላለን+ ታላቅ የመናገር ነፃነት አለን፤ 13  ደግሞም የእስራኤል ልጆች የዚያን የሚሻረውን ነገር መጨረሻ እንዳይመለከቱ ሙሴ ፊቱን በመሸፈኛ ይሸፍን+ በነበረበት ጊዜ ያደርግ እንደነበረው አናደርግም። 14  ሆኖም እነሱ አእምሯቸው ደንዝዟል።+ እስከ ዛሬ ድረስ፣ አሮጌው ቃል ኪዳን ሲነበብ ያው መሸፈኛ እንደጋረዳቸው ነውና፤+ ምክንያቱም መሸፈኛው የሚወገደው በክርስቶስ አማካኝነት ብቻ ነው።+ 15  እንዲያውም እስከ ዛሬ ድረስ የሙሴ መጻሕፍት በተነበቡ ቁጥር+ ልባቸው በመሸፈኛ እንደተሸፈነ ነው።+ 16  ሆኖም አንድ ሰው ወደ ይሖዋ* ሲመለስ መሸፈኛው ይወገዳል።+ 17  ይሖዋ* መንፈስ ነው፤+ የይሖዋ* መንፈስ ባለበት ደግሞ ነፃነት አለ።+ 18  እኛ ሁላችንም ባልተሸፈነ ፊት የይሖዋን* ክብር እንደ መስተዋት ስናንጸባርቅ ያንኑ መልክ ለመምሰል ከክብር ወደ ክብር* እንለወጣለን፤ በዚህ መንገድ መንፈስ የሆነው ይሖዋ* ራሱ* እንደሚያደርገን እንሆናለን።+

የግርጌ ማስታወሻ

ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።
ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።
ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።
ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።
ወይም “ከክብር ወደላቀ ክብር።”
ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።
“የይሖዋ መንፈስ” ማለትም ሊሆን ይችላል።