ለጢሞቴዎስ የተጻፈ ሁለተኛው ደብዳቤ 1:1-18

  • ሰላምታ (1, 2)

  • ጳውሎስ በጢሞቴዎስ እምነት የተነሳ አምላክን አመሰገነ (3-5)

  • የአምላክን ስጦታ ቸል አትበል (6-11)

  • ትክክለኛውን ትምህርት አጥብቀህ ያዝ (12-14)

  • የጳውሎስ ጠላቶችና ወዳጆች (15-18)

1  በክርስቶስ ኢየሱስ አማካኝነት የሚገኘውን ሕይወት+ በተመለከተ ከተገባው ቃል ጋር በሚስማማ ሁኔታ በአምላክ ፈቃድ የክርስቶስ ኢየሱስ ሐዋርያ ከሆነው ከጳውሎስ፣  ለተወዳጁ ልጄ ለጢሞቴዎስ፦+ አባት ከሆነው አምላክና ከጌታችን ከክርስቶስ ኢየሱስ ጸጋ፣ ምሕረትና ሰላም ለአንተ ይሁን።  የቀድሞ አባቶቼ እንዳደረጉት ቅዱስ አገልግሎት የማቀርብለትንና በንጹሕ ሕሊና የማገለግለውን አምላክ አመሰግናለሁ፤ ደግሞም ሌት ተቀን አንተን ዘወትር በምልጃዬ አስታውሳለሁ።  እንባህን ሳስታውስ፣ በደስታ እሞላ ዘንድ ላይህ እናፍቃለሁ።  በአንተ ውስጥ ያለውን ግብዝነት የሌለበት እምነት+ አስታውሳለሁና፤ ይህ እምነት በመጀመሪያ በአያትህ በሎይድ እንዲሁም በእናትህ በኤውንቄ ዘንድ ነበር፤ ይሁንና በአንተም ውስጥ እንዳለ እርግጠኛ ነኝ።  ስለዚህ በአንተ ላይ እጄን በጫንኩበት+ ጊዜ የተቀበልከውን የአምላክ ስጦታ በቅንዓት እንድትጠቀምበት* አሳስብሃለሁ።  አምላክ የኃይል፣+ የፍቅርና የጤናማ አእምሮ መንፈስ እንጂ የፍርሃት መንፈስ አልሰጠንምና።+  ስለሆነም ስለ ጌታችን መመሥከር አያሳፍርህ፤+ ደግሞም ለእሱ ስል እስረኛ በሆንኩት በእኔ አትፈር፤ ከዚህ ይልቅ በአምላክ ኃይል በመታመን+ አንተም ለምሥራቹ የበኩልህን መከራ ተቀበል።+  እሱ በእኛ ሥራ ሳይሆን በራሱ ዓላማና ጸጋ የተነሳ አዳነን፤+ እንዲሁም ቅዱስ በሆነ ጥሪ ጠራን።+ ይህን ጸጋ ከረጅም ዘመናት በፊት በክርስቶስ ኢየሱስ አማካኝነት ሰጠን፤ 10  አሁን ግን ይህ ጸጋ አዳኛችን የሆነው ክርስቶስ ኢየሱስ በመገለጡ ግልጽ ሆኖ ታይቷል፤+ እሱ ሞትን አስወግዶ+ በምሥራቹ አማካኝነት+ ሕይወትንና አለመበስበስን+ በተመለከተ ብርሃን ፈንጥቋል፤+ 11  እኔም ለዚህ ምሥራች ሰባኪ፣ ሐዋርያና አስተማሪ ሆኜ ተሹሜአለሁ።+ 12  አሁን መከራ እየተቀበልኩ ያለሁትም ለዚሁ ነው፤+ ሆኖም አላፍርበትም።+ ያመንኩበትን እሱን አውቀዋለሁና፤ በአደራ የሰጠሁትንም እስከ ፍርድ ቀን ድረስ ጠብቆ ማቆየት እንደሚችል እተማመናለሁ።+ 13  ከእኔ የሰማኸውን የትክክለኛ* ትምህርት+ መሥፈርት* ከክርስቶስ ኢየሱስ ጋር ባለህ አንድነት ካገኘኸው እምነትና ፍቅር ጋር አጥብቀህ ያዝ። 14  ይህን መልካም አደራ በእኛ ውስጥ በሚኖረው መንፈስ ቅዱስ አማካኝነት ጠብቅ።+ 15  ፊጌሎስንና ሄርሞጌኔስን ጨምሮ በእስያ አውራጃ+ ያሉት ሁሉ ትተውኝ እንደሄዱ ታውቃለህ። 16  ጌታ ለኦኔሲፎሮስ+ ቤተሰብ ምሕረትን ይስጥ፤ እሱ ብዙ ጊዜ መንፈሴን አድሶልኛልና፤ በታሰርኩበት ሰንሰለትም አላፈረም። 17  እንዲያውም ሮም በነበረ ጊዜ አፈላልጎ አገኘኝ። 18  ጌታ ይሖዋ* በዚያ ቀን ምሕረቱን ይስጠው። ደግሞም በኤፌሶን ያከናወነውን አገልግሎት ሁሉ በሚገባ ታውቃለህ።

የግርጌ ማስታወሻ

ወይም “እንደ እሳት እንድታቀጣጥል።”
ወይም “የጤናማ፤ ጠቃሚ የሆነ።”
ወይም “ንድፍ።”
ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።