ጥያቄ 6
መጽሐፍ ቅዱስ ስለ መሲሑ ምን ትንቢት ተናግሯል?
ትንቢት
“ከይሁዳ አእላፋት መካከል በጣም ትንሽ የሆንሽው ቤተልሔም ኤፍራታ ሆይ፣ . . . በእስራኤል ገዢ የሚሆን ከአንቺ ይወጣልኛል።”
ፍጻሜ
“በንጉሥ ሄሮድስ ዘመን ኢየሱስ በይሁዳ በምትገኘው በቤተልሔም ከተወለደ በኋላ ኮከብ ቆጣሪዎች ከምሥራቅ ወደ ኢየሩሳሌም [መጡ]።”
ትንቢት
“መደረቢያዎቼን እርስ በርሳቸው ተከፋፈሉ፤ በልብሴም ላይ ዕጣ ተጣጣሉ።”
ፍጻሜ
“ወታደሮቹ ኢየሱስን በእንጨት ላይ ከቸነከሩት በኋላ መደረቢያዎቹን ወስደው . . . አራት ቦታ ቆራረጧቸው፤ ከውስጥ ለብሶት የነበረውንም ልብስ ወሰዱ። ሆኖም ልብሱ ከላይ እስከ ታች አንድ ወጥ ሆኖ ያለስፌት የተሠራ ነበር። ስለዚህ እርስ በርሳቸው ‘ከምንቀደው ዕጣ ተጣጥለን ለማን እንደሚደርስ እንወስን’ ተባባሉ።”
ትንቢት
“አጥንቶቹን ሁሉ ይጠብቃል፤ አንዳቸውም ቢሆኑ አልተሰበሩም።”
ፍጻሜ
“ወደ ኢየሱስ በመጡ ጊዜ ግን ቀደም ብሎ መሞቱን ስላዩ እግሮቹን አልሰበሩም።”
ትንቢት
“ስለ መተላለፋችን ተወጋ።”
ፍጻሜ
“ከወታደሮቹ አንዱ ጎኑን በጦር ወጋው፤ ወዲያውም ደምና ውኃ ፈሰሰ።”
ትንቢት
“እነሱም ደሞዜን፣ 30 የብር ሰቅል ከፈሉኝ።”
ፍጻሜ
“ከዚህ በኋላ፣ ከአሥራ ሁለቱ አንዱ የሆነው የአስቆሮቱ ይሁዳ ወደ ካህናት አለቆች ሄዶ ‘እሱን አሳልፌ ብሰጣችሁ ምን ትሰጡኛላችሁ?’ አላቸው። እነሱም 30 የብር ሳንቲሞች ሊሰጡት ተስማሙ።”