በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ጥያቄ 5

የመጽሐፍ ቅዱስ መልእክት ምንድን ነው?

 “በአንተና በሴቲቱ መካከል እንዲሁም በዘርህና በዘሯ መካከል ጠላትነት እንዲኖር አደርጋለሁ፤ እሱ ራስህን ይጨፈልቃል፤ አንተም ተረከዙን ታቆስላለህ።”

ዘፍጥረት 3:15

 “ቃሌን ስለሰማህ የምድር ብሔራት ሁሉ በዘርህ አማካኝነት ለራሳቸው በረከት ያገኛሉ።”

ዘፍጥረት 22:18

 “መንግሥትህ ይምጣ። ፈቃድህ በሰማይ እየተፈጸመ እንዳለ ሁሉ በምድርም ላይ ይፈጸም።”

ማቴዎስ 6:10

 “ሰላም የሚሰጠው አምላክ በቅርቡ ሰይጣንን ከእግራችሁ በታች ይጨፈልቀዋል።”

ሮም 16:20

 “ሁሉም ነገር ከተገዛለት በኋላ ወልድ ራሱ ሁሉን ነገር ላስገዛለት ራሱን ያስገዛል፤ ይህም አምላክ ለሁሉም ሁሉንም ነገር እንዲሆን ነው።”

1 ቆሮንቶስ 15:28

 “የተስፋው ቃል የተነገረው ለአብርሃምና ለዘሩ ነው። . . . እሱም ክርስቶስ ነው። በተጨማሪም የክርስቶስ ከሆናችሁ በእርግጥም የአብርሃም ዘር ናችሁ።”

ገላትያ 3:16, 29

 “የዓለም መንግሥት የጌታችንና የእሱ መሲሕ መንግሥት ሆነ፤ እሱም ለዘላለም ይነግሣል።”

ራእይ 11:15

 “ስለሆነም ታላቁ ዘንዶ ይኸውም መላውን ዓለም እያሳሳተ ያለው ዲያብሎስና ሰይጣን ተብሎ የሚጠራው የጥንቱ እባብ ወደ ታች ተወረወረ፤ ወደ ምድር ተጣለ፤ መላእክቱም ከእሱ ጋር ተወረወሩ።”

ራእይ 12:9

 “እሱም ዘንዶውን ያዘውና ለ1,000 ዓመት አሰረው፤ ይህም ዘንዶ ዲያብሎስና ሰይጣን የሆነው የጥንቱ እባብ ነው።”

ራእይ 20:2