ሁለት ሳንቲም

ሁለት ሳንቲም

  1. 1. ሁለት ሳንቲም፣

    ያለቻትም እሷ፤

    ደጁ ነች፣

    መባዋን ልትከት ደርሶ ተራዋ።

    ዓይን አትገባ፣

    ባ’ብታሞቹ ደብዝዛ፤

    ልብ የሚላት ማን ነው?

    ሁለቷን ሳንቲም ይዛ በጇ!

    (አዝማች)

    ያያል ይሖዋ፣

    ያደንቃል አይቶ፤

    መባዋን አይንቅም ከቶ።

    ሚዛን ባትደፋ፣

    ኮሽም ባታሰማ፤

    አታንስም፣ አትቀልም ላይኑ

    ሳንቲሟ።

  2. 2. እንደ ዛሬው፣

    ኑሮ ሳይከብዳት ያኔ፤

    አ’ርጋለች ብዙ

    ትዝ አላት ይሆን ያ ደጉ ጊዜ?

    ሁለት ሳንቲሞች

    ሰጠች ኮሽም ሳይሰማ፤

    በይሖዋ ፊት ግን

    ከበረች ካጀብ ተነጥላ።

    (አዝማች)

    ያያል ይሖዋ፣

    ያደንቃል አይቶ፤

    መባዋን አይንቅም ከቶ።

    ሚዛን ባትደፋ፣

    ኮሽም ባታሰማ፤

    አታንስም፣ አትቀልም ላይኑ

    ሳንቲሟ።

    (መሸጋገሪያ)

    ሰው ያቀለለው፣ ለሱ ክቡር ነው፤

    የስጦታ ብዛት አያስደምመው፤

    የሚያየው ልብን ነው።

    (አዝማች)

    ያያል ይሖዋ፣

    ያደንቃል አይቶ፤

    መባዋን አይንቅም ከቶ።

    ሚዛን ባትደፋ፣

    ኮሽም ባታሰማ፤

    አታንስም፣ አትቀልም ላይኑ

    ሳንቲሟ።

    ክቡር ናት በይሖዋ ዓይን!