ሰላም ሲያዜም ፍጥረት

ሰላም ሲያዜም ፍጥረት

 

  1. 1. ኧረ፣ መላው ታጣ፤

    ሰላም የውኃ ሽታ!

    በዚህ ቢሉ፣ ቢሉ በዚያ፣

    ባሰ፣ ጦርነት በዛ።

    የሰው ጥረት መና፣

    መች ተሳክቶ ያውቅና!

    ከላይ ነው ከሱ፣ መፍትሔው መልሱ፤

    ያሳየናል በቅርቡ፦

    (አዝማች)

    አንድ ውዳሴ፣

    አንድ እምነት፤

    ለሱ ብቻ

    ሲንበረከክ ጉልበት፤

    ሰላም ሲያዜም ፍጥረት።

  2. 2. እያለው ደስ ደስ፣

    ልቤ ወዷል ሊታገሥ።

    እስኪያልፍ ቢያስከፋም፣ እስኪያልፍ ቢያለፋም

    እጸናለሁ በተስፋ።

    ይሖዋ ሰላሜ፣

    አለ ካጠገቤ።

    ያሳርፈኛል፣ ያድነኛል፤

    አንድ ቀን፣ በቅርቡ፦

    (አዝማች)

    አንድ ውዳሴ፣

    አንድ እምነት፤

    ለሱ ብቻ

    ሲንበረከክ ጉልበት፤

    ሰላም ሲያዜም ፍጥረት።

    (መሸጋገሪያ)

    የሰላሙ መስፍን

    ሺህ ዓመት ሲደፍን፣

    ሥልጣንን ሁሉ፣ ኃይልን በሙሉ

    ያስገዛል ላባቱ፤

    ይነግሣል ልዑሉ!

    (አዝማች)

    አንድ ውዳሴ፣

    አንድ እምነት፤

    ለሱ ብቻ

    ሲንበረከክ ጉልበት፤

    አንድ ውዳሴ፣

    አንድ እምነት፤

    ለሱ ብቻ

    ሲንበረከክ ጉልበት፤

    ሰላም ሲያዜም ፍጥረት።

    አሜን፣ ቶሎ ድረስ!