አቀረበኝ

አቀረበኝ

 

  1. 1. ተመስገን ልበል አምላኬን፤

    ደርሶ ቀየረው ታሪኬን።

    እንክትክት ያለው ቅስሜ፣

    በሱ ታከመ ሕመሜ።

    እያጽናናኝ ቆሞ ጎኔ፤

    ሰው ሆንኩኝ፣ ዛሬ ድኜ!

    (አዝማች)

    “ና፣ የኔ ሁን” አለኝ፣ “ና” አለኝ፤

    እጆቹን ዘርግቶ።

    አቀረበኝ፣ ቀረበኝ፤

    እሱን መሻቴን አይቶ።

    አቀረበኝ ወዶ!

  2. 2. ኮናኙ ልቤ በርትቶ፣

    ነፍሴን ሲያስጨንቃት ደቁሶ፤

    አልችለው በምን አቅሜ?

    ካልደረሰልኝ ደክሜ።

    ሳይንቅ የምስኪኑን ለቅሶ፣

    አነሳኝ አጎንብሶ።

    (አዝማች)

    “ና፣ የኔ ሁን” አለኝ፣ “ና” አለኝ፤

    እጆቹን ዘርግቶ።

    አቀረበኝ፣ ቀረበኝ፤

    እሱን መሻቴን አይቶ።

    አቀረበኝ ወዶ!

    (መሸጋገሪያ)

    ወደደኝ ሳላውቀው ገና፤

    ምን አይቶብኝ እንጃ!

    ቃል ያጥረኛል ማመስገኛ፤

    ታላቅ፣ እሱ ብቻ!

    (አዝማች)

    “ና፣ የኔ ሁን” አለኝ፣ “ና” አለኝ፤

    እጆቹን ዘርግቶ።

    አቀረበኝ፣ ቀረበኝ፤

    እሱን መሻቴን አይቶ።

    አቀረበኝ ወዶ!