አንድ ላይ እንጽና አጫውት አንድ ላይ እንጽና ይቅርታ፣ ማጫወቻው መሥራት አልቻለም። ይህን ቪዲዮ አውርድ ጽሑፉን አሳይ ጽሑፉን ደብቅ (መግቢያ) ጥሪያችን ይድረስ ለሁሉ! ይድረስ ለምንወዳችሁ! 1. ድንበር አያውቅ ፍቅራችን፤ አምላካችን አንድ፣ እምነታችን። የ’ውነት ልሳን ያግባባን፣ ባንድ ድምፅ የምናወድስ ጌታን። (ቅድመ አዝማች) የችግር ናዳ ምን ቢበረታ፣ አብረን ነን ምንም ቢመጣ! (አዝማች) አብረን ነን፤ አንድ ነን፤ ማን ይለያየናል? አብረን ነን፤ አንድ ነን፤ ምን ይበግረናል? አብረን ነን፤ አንድ ነን፤ አይዞን እንበርታ! ተባብረን፣ ተደጋግፈን፣ አንድ ላይ፣ አንድ ላይ እንጽና! 2. ያለነው ባለም ሁሉ፣ በዘር በብሔር ልዩ ልዩ። ድል ያረግን ጥላቻን፣ አንድ ሕዝብ ነን ልዩነት ያልረታን። (ቅድመ አዝማች) የትም ብንሄድ ቤተሰብ አለን፣ ገና ሳያውቀን ’ሚወደን። (አዝማች) አብረን ነን፤ አንድ ነን፤ ማን ይለያየናል? አብረን ነን፤ አንድ ነን፤ ምን ይበግረናል? አብረን ነን፤ አንድ ነን፤ አይዞን እንበርታ! ተባብረን፣ ተደጋግፈን፣ አንድ ላይ፣ አንድ ላይ እንጽና! አንድ ላይ፣ ተባብረን፣ አንድ ላይ! (አዝማች) አብረን ነን፤ አንድ ነን፤ ማን ይለያየናል? አብረን ነን፤ አንድ ነን፤ ምን ይበግረናል? አብረን ነን፤ አንድ ነን፤ አይዞን እንበርታ! ተባብረን፣ ተደጋግፈን፣ አንድ ላይ፣ አንድ ላይ እንጽና! አንድ ላይ እንጽና! አንድ ላይ እንጽና! ተመለስ ቀጥል አትም አጋራ አጋራ አንድ ላይ እንጽና ኦሪጅናል መዝሙሮች አንድ ላይ እንጽና የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ አንድ ላይ እንጽና https://cms-imgp.jw-cdn.org/img/p/1014363/univ/art/1014363_univ_sqr_xl.jpg