‘አይዘገይ ከቶ!’ (የ2023 የክልል ስብሰባ መዝሙር)

‘አይዘገይ ከቶ!’ (የ2023 የክልል ስብሰባ መዝሙር)

(ዕንባቆም 2:3)

 

  1. 1. ተሠርታ ባንተ፣ ድንቅ እጹብ ሆና፤

    ምድርን የሚገልጽ ምን ቃል ይገኝና!

    ቢያበላሻት ሰው የ’ጅህን ሥራ፣

    ታስውባታለህ ልክ እንደ ሙሽራ።

    (አዝማች)

    አባት ሆይ ናፈቀን፣ መኖር እፎይ ብለን፤

    ት’ግሥቱን ’ባክህ ስጠን።

    የጓጓንለት ቀን እናያለን መጥቶ፤

    ምን ቢቆይ፣ ምን ቢረዝም፣

    ‘አይዘገይ ከቶ!’

  2. 2. ሞት የረታቸው ካፈር ሲወጡ፣

    መች ይሆን ደርሶ ’ምናየው ሲመጡ?

    ሁንልን ጉልበት ሌቱ ’ስኪነጋ፤

    እንድንታገሥ ይሖዋ ካንተ ጋ።

    (አዝማች)

    አባት ሆይ ናፈቀን፣ መኖር እፎይ ብለን፤

    ት’ግሥቱን ’ባክህ ስጠን።

    የጓጓንለት ቀን እናያለን መጥቶ፤

    ምን ቢቆይ፣ ምን ቢረዝም፣

    ‘አይዘገይ ከቶ!’

  3. 3. ስተው ከመንገድ የተጨነቁ፣

    በመታገሥህ ስምህን አወቁ።

    ብርሃን ለዓለም፣ አንተ ነህ ተስፋ፤

    ብንደክምልህ፣ ክብር ነው ብንለፋ።

    (አዝማች)

    አባት ሆይ ናፈቀን፣ መኖር እፎይ ብለን፤

    ት’ግሥቱን ’ባክህ ስጠን።

    የጓጓንለት ቀን እናያለን መጥቶ፤

    ምን ቢቆይ፣ ምን ቢረዝም፣

    ‘አይዘገይ ከቶ!’

    ስጠን ታጋሽ ልብ ’ባክህ!

(በተጨማሪም ቆላ. 1:11⁠ን ተመልከት።)