እንታረቅ

እንታረቅ

 

  1. 1. ይጨንቀኛል፣ ተሠቃየሁ፤

    ቂም በልቤ ስላቆየሁ።

    ነገር መብላት ውስጤን ጎዳው፤

    ማስተካከል ይገባኛል

    ስህተት ነው።

    (አዝማች)

    ለ’ርምጃ አሁን ነው ጊዜው፤

    እስከ መቼ ተሸክሜው?

    ሰላማችን እንዲመለስ

    እንታረቅ፣ እንዋደድ።

  2. 2. እኔ ይቅር ’ምለው ጥፋት፣

    እኔ የምረሳው በደል፣

    ከይሖዋ ይቅርታ ጋር

    አይወዳደር፤ ያምላክ ፍቅር

    የለው ወደር!

    (አዝማች)

    ለ’ርምጃ አሁን ነው ጊዜው፤

    እስከ መቼ ተሸክሜው?

    ሰላማችን እንዲመለስ

    እንታረቅ፣ እንዋደድ።

    (መሸጋገሪያ)

    ቅድሚያ ’ወስዳለሁ፤

    ዛሬውኑ፣ ቀን ሳይተካ።

    እንፍታው ግድ የለም፤

    ኩርፊያው ይብቃ፣ ይቅር በቃ።

  3. 3. ይሖዋ ’ምላክ ይወደናል፤

    ስንዋደድ ደስ ይለዋል።

    ምሕረት ሳደርግ ሰላም አለኝ፤

    ይቅር ማለት፣ ነፃ መተው

    ነው ’ሚያዋጣኝ።

    (አዝማች)

    ለ’ርምጃ አሁን ነው ጊዜው፤

    እስከ መቼ ተሸክሜው?

    ሰላማችን እንዲመለስ

    እንታረቅ፣ እንዋደድ።

    እንታረቅ፣ እንዋደድ።

    ቅድሚያ ’ወስዳለሁ።