እንጸናለን

እንጸናለን

 

  1. 1. አልረሳውም ያን ልዩ ደስታ፣

    ያን ልዩ ስሜት እውነትን ስሰማ።

    አልጠፋም አለ የቀድሞው ፍቅሬ፤

    ዓለም ግን ሊያርቀኝ ይጥራል ዛሬም።

    (ቅድመ አዝማች)

    አልዘናጋም፤

    ቆርጫለሁ በቃ!

    (አዝማች)

    በ’ምነቴ ጠንካራ፣ ብርቱ ’ሆናለሁ፤

    ፍንክች አልልም፣ ’ጸናለሁ።

    ቃሉ ’ሚለኝን እታዘዛለሁ፤

    ሳልታክት እጸልያለሁ።

    የመጣው ቢመጣ እጸናለሁ።

  2. 2. አይናወጥም እምነታችን

    ዓለት ላይ ቢሆን መሠረታችን።

    ያለም መልክ ብልጭልጭ፣ አማላይ ነው፤

    የሚፈርስ አይመስልም እንዲሁ ላየው።

    (ቅድመ አዝማች)

    ውሸት ነው ያልፋል፤

    እውነቱን አውቀናል።

    (አዝማች)

    በ’ምነታችን ጽኑ፣ ብርቱ ’ንሆናለን፤

    ፍንክች ሳንል እንጸናለን።

    ቃሉ ’ሚለንን እንጠብቃለን፤

    ሳንታክት እንጸልያለን።

    የመጣው ቢመጣ እንጸናለን።

    (አዝማች)

    በ’ምነታችን ጽኑ፣ ብርቱ ’ንሆናለን፤

    ፍንክች ሳንል እንጸናለን።

    ቃሉ ’ሚለንን እንጠብቃለን፤

    ሳንታክት እንጸልያለን።

    የመጣው ቢመጣ እንጸናለን።

    እንጸናለን።

    እንጸናለን።