ወደ ማን እሄዳለሁ?

ወደ ማን እሄዳለሁ?

 

  1. 1. በጨለማ ስዳክር፣

    ሕይወት ውሏን ላገኝ፤

    ደርሶ አበራልኝ

    መንገዱ ’ንዲታየኝ።

    ኢየሱስ አይደል ወይ

    መልካሙ ’ረኛዬ?

    አልደናቀፍ፣

    አለ ጠባቂዬ።

    (ቅድመ አዝማች)

    ለማን ብዬ ነው፣ ለምን?

    እንግዳ ድምፅ የምሰማው?

    ጠቅሞ ለማይጠቅመኝ

    ጆሮዬን የምሰጠው?

    (አዝማች)

    ወደ ማን እሄዳለሁ?

    ሲጨንቀኝ ወዴት ዞር እላለሁ?

    ወደ ማን እሄዳለሁ?

    እንግዳ ድምፅ ሰምቶ፣

    ያውቃል ወይ ተሳክቶ?

    ለኔስ ኢየሱስ ነው ’ረኛዬ።

  2. 2. እተኛለሁ በሰላም፣

    ያለስጋት ውዬ፤

    ግራ ቀኜን ባይ፣

    ፍቅር ነው ዙሪያዬ።

    ይታየኛል ተስፋው፣

    ደምቆ በርቶ ላይኔ፤

    የሕይወት ቃል አለው፣

    ደጉ አዳኜ።

    (ቅድመ አዝማች)

    አተርፍ ባይ አጉዳይ፣

    ሆኜ እንዳይቆጨኝ ኋላ።

    ዘጋሁ፣ ደፈንኩ ጆሮዬን፤

    አበጀሁለት ከለላ።

    (አዝማች)

    ወደ ማን እሄዳለሁ?

    ሲጨንቀኝ ወዴት ዞር እላለሁ?

    ወደ ማን እሄዳለሁ?

    እንግዳ ድምፅ ሰምቶ፣

    ያውቃል ወይ ተሳክቶ?

    ለኔስ ኢየሱስ ነው ’ረኛዬ።

    (አዝማች)

    ወደ ማን እሄዳለሁ?

    ሲጨንቀኝ ወዴት ዞር እላለሁ?

    ወደ ማን እሄዳለሁ?

    እንግዳ ድምፅ ሰምቶ፣

    ያውቃል ወይ ተሳክቶ?

    ለኔስ ኢየሱስ ነው ’ረኛዬ።

    ወደ ማን እሄዳለሁ?

    መቼም አልርቅም ከረኛዬ! መቼም!