ውዴ፣ የኔ አጫውት ውዴ፣ የኔ ይቅርታ፣ ማጫወቻው መሥራት አልቻለም። ይህን ቪዲዮ አውርድ ጽሑፉን አሳይ ጽሑፉን ደብቅ 1. ፍቅሬ ሆይ፣ የኔ፣ የብቻዬ፤ አንቺ ነሽ ውዴ፣ አቻዬ። ፍቅርሽ፣ ደግነትሽ ገዝቶታል መንፈሴን፤ ስጦታዬ፣ ልዩ ነሽ መልካም ሴት። ደስ ይለኛል ሳስብ እንዳለሽ ከጎኔ፤ በጥልቅ አክብሮትሽ ማርከሽዋል ልቤን። (አዝማች) ፍቅራችን ይሁን ጽኑ፤ እንዲህ ተዋደን እንኑር። ይሖዋ ይጨመር በትዳራችን ውዴ፣ የኔ። 2. አንተ ነህ ፍቅሬ፣ የሕይወት አጋሬ፤ ጓደኛዬ፣ የምነግርህ ውስጤን። ደስታዬ ነው ክብሬ ማገልገል አብሬህ፤ ኩራቴ ነህ ሁሌም፤ አይታጠፍም ቃሌ። (አዝማች) ፍቅራችን ይሁን ጽኑ፤ እንዲህ ተዋደን እንኑር። ይሖዋ ይጨመር በትዳራችን ውዴ፣ የኔ። ፍቅራችን ይሁን ጽኑ፤ እንዲህ ተዋደን እንኑር። ይሖዋ ይጨመር በትዳራችን ውዴ፣ የኔ። ውዴ፣ የኔ። ፍቅሬ። ተመለስ ቀጥል አትም አጋራ አጋራ ውዴ፣ የኔ ኦሪጅናል መዝሙሮች ውዴ፣ የኔ የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ውዴ፣ የኔ https://cms-imgp.jw-cdn.org/img/p/1014333/univ/art/1014333_univ_sqr_xl.jpg