ያውቃል

ያውቃል

 

  1. 1. ዓለም ሳያየኝ በስውር ስፈጠር፣

    በምድር ላይ ዕድሜዬ ሳይቆጠር፣

    ይሖዋ ’የ ማንነቴን፤

    ያልታየውን እኔነቴን።

    ዳር የለው ታላቅ ፍቅሩ!

    (አዝማች)

    ያውቀኛል ጠንቅቆ፤

    ጠልቆ፣ ልቤ ዘልቆ።

    ቅን ሐሳቤን ከጥንስሱ፣

    ያውቃል ውስጤን፣ ፍቅሬን ለሱ።

    ያውቅሃል ጠንቅቆ፤

    ሚስጥርህን ጠልቆ።

    ስትቃትት ጭንቀትህ በዝቶ፣ ሳይወጣህ ቃል

    ያውቃል።

  2. 2. አባት እንደሚሳሳ ለልጁ፣

    እንዲሳካልኝ ነው ምኞቱ።

    ፈልጎ አገኘ ቅንነት፤

    ከልቤ ጓዳ መልካምነት።

    ዳር የለው ታላቅ ፍቅሩ!

    (አዝማች)

    ያውቀኛል ጠንቅቆ፤

    ጠልቆ፣ ልቤ ዘልቆ።

    ቅን ሐሳቤን ከጥንስሱ፣

    ያውቃል ውስጤን፣ ፍቅሬን ለሱ።

    ያውቅሃል ጠንቅቆ፤

    ሚስጥርህን ጠልቆ።

    ስትቃትት ጭንቀትህ በዝቶ፣ ሳይወጣህ ቃል

    ያውቃል።

    (መሸጋገሪያ)

    አይጠራጠርም ልቤ፤ በመከራዬ ሁሉ አለ ቅርቤ፣ ቅርቤ።

    ስጋት ልቤን ሲያስረው፣ እሱን ነው ድረስ የምለው።

    ይሰማል አውቃለሁ፤ ጉዳዬ ጉዳዩ ነው።

    (አዝማች)

    ያውቀኛል ጠንቅቆ፤

    ጠልቆ፣ ልቤ ዘልቆ።

    ቅን ሐሳቤን ከጥንስሱ፣

    ያውቃል ውስጤን፣ ፍቅሬን ለሱ።

    ያውቅሃል ጠንቅቆ፤

    ሚስጥርህን ጠልቆ።

    ስትቃትት ጭንቀትህ በዝቶ፣ ሳይወጣህ ቃል

    (አዝማች)

    ያውቀኛል ጠንቅቆ፤

    ጠልቆ፣ ልቤ ዘልቆ።

    ቅን ሐሳቤን ከጥንስሱ፣

    ያውቃል ውስጤን፣ ፍቅሬን ለሱ።

    ያውቅሃል ጠንቅቆ፤

    ሚስጥርህን ጠልቆ።

    ስትቃትት ጭንቀትህ በዝቶ፣ ሳይወጣህ ቃል

    ያውቃል።