በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

የመጽሐፍ ቅዱስ መጻሕፍት ማስተዋወቂያዎች

እነዚህ አጫጭር ቪዲዮዎች የአንድን የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ ይዘትና ከመጽሐፉ ጋር የተያያዙ ጠቃሚ መረጃዎችን ይዘዋል። እነዚህ ቪዲዮዎች ከመጽሐፍ ቅዱስ ንባብህና ጥናትህ ይበልጥ ጥቅም እንድታገኝ ይረዱሃል።

የዘዳግም መጽሐፍ ማስተዋወቂያ

ይሖዋ ለእስራኤላውያን የሰጣቸው ሕግ ለሕዝቦቹ ያለውን ፍቅር የሚያሳየው እንዴት እንደሆነ ተመልከት።

የኢያሱ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ

እስራኤላውያን አምላክ የሰጣቸውን ምድር የተቆጣጠሩትና የተከፋፈሉት እንዴት እንደሆነ ተመልከት።

የመሳፍንት መጽሐፍ ማስተዋወቂያ

በተለያዩ ክንውኖች የተሞላው ይህ መጽሐፍ ስያሜውን ያገኘው አምላክ እስራኤላውያንን ከጠላቶቻቸው ለመታደግ ከተቀመባቸው ደፋር መሳፍንት ነው።

የሩት መጽሐፍ ማስተዋወቂያ

የሩት መጽሐፍ የሚተርከው አንዲት ወጣት መበለት ለአማቷ ስላሳየችው ጥልቅ ፍቅርና ይሖዋ ስለሰጣቸው በረከት ነው።

የ1 ሳሙኤል ማስተዋወቂያ

እስራኤላውያን ከመሳፍንት ዘመን ወደ ነገሥታት ዘመን የተሸጋገሩት እንዴት እንደሆነ ተመልከት።

የ2 ሳሙኤል መጽሐፍ ማስተዋወቂያ

ዳዊት ትሑትና ጠንካራ እምነት ያለው ሰው ነበር። እነዚህ ባሕርያት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከተጠቀሱት ሰዎች መካከል በጣም ተወዳጅና በስፋት የሚታወቅ እንዲሆን ያደረጉት እንዴት እንደሆነ ተመልከት።

የ1 ነገሥት መጽሐፍ ማስተዋወቂያ

እስራኤል በሰሎሞን አገዛዝ ሥር ታላቅ ክብርና ብልጽግና ነበራት፤ ከዚያ በኋላ ብሔሩ ለሁለት ሲከፈል የተቋቋሙት የእስራኤልና የይሁዳ መንግሥታት ታሪክ ግን ሁከት የነገሠበት ነው።

የ2 ነገሥት መጽሐፍ ማስተዋወቂያ

ክህደት ለሰሜናዊው የእስራኤል መንግሥት እንደ መቅሰፍት ሆኖበታል፤ ያም ቢሆን ይሖዋ እሱን በሙሉ ልብ ያገለገሉትን ጥቂት ሰዎች ባርኳቸዋል።

የ1 ዜና መዋዕል መጽሐፍ ማስተዋወቂያ

ይህ መጽሐፍ፣ ፈሪሃ አምላክ የነበረውን የንጉሥ ዳዊትን የትውልድ ሐረግ መስመር እንዲሁም የእስራኤል ንጉሥ ሆኖ ከተሾመበት እስከሞተበት ጊዜ ድረስ ያለውን አስገራሚ ታሪክ ይዟል።

የ2 ዜና መዋዕል መጽሐፍ ማስተዋወቂያ

የይሁዳ ነገሥታት ታሪክ ለአምላክ ታማኝ የመሆንን አስፈላጊነት ጎላ አድርጎ የሚያሳየው እንዴት እንደሆነ ተመልከት።

የዕዝራ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ

ይሖዋ በባቢሎን ምርኮ የነበሩትን ሕዝቦቹ ነፃ ለማውጣትና በኢየሩሳሌም ንጹሑን አምልኮ ለማቋቋም የገባውን ቃል ፈጽሟል።

የነህምያ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ

የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የሆነው የነህምያ መጽሐፍ በዛሬው ጊዜ ላሉ እውነተኛ የአምላክ አገልጋዮች በሙሉ የሚሆን ጠቃሚ ትምህርት ይዟል።

የአስቴር መጽሐፍ ማስተዋወቂያ

በአስቴር ዘመን የተፈጸሙ አስገራሚ ክንውኖች አምላክ ሕዝቦቹን ከአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የማውጣት ችሎታ እንዳለው ጠንካራ እምነት እንዲያድርብህ ያደርጋል።

የኢዮብ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ

ይሖዋን የሚወዱ ሁሉ መፈተናቸው አይቀርም። የኢዮብ መጽሐፍ፣ ንጹሕ አቋማችንን መጠበቅና የይሖዋን ሉዓላዊነት መደገፍ እንደምንችል እርግጠኞች እንድንሆን ያደርገናል።

የመዝሙር መጽሐፍ ማስተዋወቂያ

የመዝሙር መጽሐፍ የይሖዋን ሉዓላዊነት ይደግፋል፤ ይሖዋ የሚወዱትን ሰዎች እንዴት እንደሚረዳና እንደሚያጽናና ይናገራል፤ እንዲሁም በአምላክ መንግሥት አማካኝነት ምድር ገነት እንደምትሆን ይናገራል።