መጽሐፍ ቅዱስ ሳይጋቡ አብሮ መኖርን በተመለከተ ምን ይላል? አጫውት መጽሐፍ ቅዱስ ሳይጋቡ አብሮ መኖርን በተመለከተ ምን ይላል? ይቅርታ፣ ማጫወቻው መሥራት አልቻለም። ይህን ቪዲዮ አውርድ ጽሑፉን አሳይ ጽሑፉን ደብቅ መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል? አምላክ የሰው ልጆች ‘ከፆታ ብልግና እንዲርቁ’ እንደሚፈልግ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። (1 ተሰሎንቄ 4:3) በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘው “የፆታ ብልግና” የሚለው ቃል ምንዝርን፣ ግብረ ሰዶምንና ባልተጋቡ ሰዎች መካከል የሚፈጸምን የፆታ ግንኙነት ይጨምራል። አምላክ ሰዎች ጋብቻ የመመሥረታቸው ጉዳይ የሚያሳስበው ለምንድን ነው? በደንብ እንደሚጣጣሙ ለማረጋገጥ ከጋብቻ በፊት አብሮ መኖር ምን ችግር አለው? ባለትዳሮች ትዳራቸውን ማጠናከር የሚችሉት እንዴት ነው? አምላክ ሰዎች ጋብቻ የመመሥረታቸው ጉዳይ የሚያሳስበው ለምንድን ነው? የጋብቻ ዝግጅትን የመሠረተው አምላክ ነው። አምላክ አዳምንና ሔዋንን በትዳር በማጣመር የጋብቻ ዝግጅትን አቋቁሟል። (ዘፍጥረት 2:22-24) የአምላክ ዓላማ አንድ ወንድና አንዲት ሴት የጋብቻ መሐላ ሳይፈጽሙ አብረው እንዲኖሩ አልነበረም። ለሰው ልጆች የሚጠቅመውን የሚያውቀው አምላክ ነው። አምላክ ጋብቻን ያቋቋመው በአንድ ወንድና በአንዲት ሴት መካከል የሚመሠረት ዘላቂ ጥምረት እንዲሆን አድርጎ ሲሆን ጋብቻ ለሁሉም የቤተሰብ አባላት ደስታና ጥበቃ የሚያስገኝ እንዲሆን ይፈልጋል። አንድ ቀላል ምሳሌ እንመልከት። የቤት ዕቃ የሚያመርት ድርጅት የሚሰጠው መመሪያ ዕቃውን በትክክል ለመገጣጠም እንደሚረዳ ሁሉ አምላክ የሚሰጠው መመሪያም አስደሳች የቤተሰብ ሕይወት ለመመሥረት ይረዳል። የአምላክን መሥፈርቶች የሚከተሉ ሰዎች ምንጊዜም ጥቅም ያገኛሉ።—ኢሳይያስ 48:17, 18 የቤት ዕቃ የሚያመርት ድርጅት የሚሰጠው መመሪያ ዕቃውን በትክክል ለመገጣጠም ይረዳል። አምላክ የሚሰጠው መመሪያም አስደሳች የቤተሰብ ሕይወት ለመመሥረት ይረዳል ከጋብቻ ውጭ የሚፈጸም የፆታ ግንኙነት ከባድ መዘዝ ሊያስከትል ይችላል። ለምሳሌ ላልተፈለገ እርግዝና፣ ለአባላዘር በሽታዎችና ለስሜት ቀውስ ሊዳርግ ይችላል። ሰዎች በፆታ ግንኙነት አማካኝነት ልጅ የመውለድ ችሎታ እንዲኖራቸው ያደረገው አምላክ ነው። አምላክ ሕይወትን ቅዱስ አድርጎ ይመለከተዋል፤ ዘር የመተካት ችሎታም ልዩ ስጦታ ነው። ለዚህ ስጦታ አክብሮት እንዳለን ማሳየት የምንችለው አምላክ ያቋቋመውን የጋብቻ ዝግጅት በማክበር ነው፤ አምላክም እንዲህ እንድናደርግ ይፈልጋል።—ዕብራውያን 13:4 በደንብ እንደሚጣጣሙ ለማረጋገጥ ከጋብቻ በፊት አብሮ መኖር ምን ችግር አለው? ስኬታማ ትዳር መመሥረት የሚቻለው ከጋብቻ በፊት ያለምንም ቃል ኪዳን “ለሙከራ ያህል” አብሮ በመኖር አይደለም። ከዚህ ይልቅ ጥሩ ትዳር መመሥረት የሚቻለው ሁለቱም ምንም ነገር ቢያጋጥም አብረው ለመኖር ቁርጠኛ ከሆኑና ችግሮችን ለመፍታት ተባብረው የሚሠሩ ከሆነ ነው። a በጋብቻ መተሳሰራቸው አብረው ለመኖር ያላቸውን ቁርጠኝነት ያጠናክረዋል።—ማቴዎስ 19:6 ባለትዳሮች ትዳራቸውን ማጠናከር የሚችሉት እንዴት ነው? ፍጹም የሆነ ትዳር የለም። ሆኖም ባለትዳሮች የመጽሐፍ ቅዱስን ምክር በተግባር የሚያውሉ ከሆነ አስደሳች የትዳር ሕይወት ሊኖራቸው ይችላል። ለምሳሌ መጽሐፍ ቅዱስ የሚከተሉትን ምክሮች ይሰጣል፦ ከራሳችሁ ፍላጎት ይልቅ የትዳር ጓደኛችሁን ፍላጎት አስቀድሙ።—1 ቆሮንቶስ 7:3-5፤ ፊልጵስዩስ 2:3, 4 እርስ በርስ ተዋደዱ እንዲሁም ተከባበሩ።—ኤፌሶን 5:25, 33 ንግግራችሁን ተቆጣጠሩ።—ምሳሌ 12:18 ትዕግሥተኛና ይቅር ባይ ሁኑ።—ቆላስይስ 3:13, 14 a “ስኬታማ ቤተሰቦች—ቃል ኪዳንን ማክበር” የሚለውን ርዕስ ተመልከት። ተዛማጅ ርዕሶች ጋብቻ አኗኗር እና ሥነ ምግባር የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው እነዚህንስ አይተሃቸዋል? ስለ እኛ አንድ የይሖዋ ምሥክር መጥቶ እንዲያነጋግርህ ጠይቅ ከይሖዋ ምሥክሮች ጋር ስለምትፈልገው የመጽሐፍ ቅዱስ ርዕሰ ጉዳይ መወያየት ወይም መጽሐፍ ቅዱስን በነፃ ከምናስተምርበት ዝግጅት መጠቀም ትችላለህ። አትም አጋራ አጋራ መጽሐፍ ቅዱስ ሳይጋቡ አብሮ መኖርን በተመለከተ ምን ይላል? የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው መጽሐፍ ቅዱስ ሳይጋቡ አብሮ መኖርን በተመለከተ ምን ይላል? የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ መጽሐፍ ቅዱስ ሳይጋቡ አብሮ መኖርን በተመለከተ ምን ይላል? https://cms-imgp.jw-cdn.org/img/p/500100100/univ/art/500100100_univ_sqr_xl.jpg ijwbq 168