ወደ ቅዱሳን መጸለይ ይገባኛል? አጫውት ወደ ቅዱሳን መጸለይ ይገባኛል? ይቅርታ፣ ማጫወቻው መሥራት አልቻለም። ይህን ቪዲዮ አውርድ ጽሑፉን አሳይ ጽሑፉን ደብቅ መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል? እንዲህ ማድረግ ተገቢ አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ፣ በኢየሱስ ስም ለአምላክ ብቻ መጸለይ እንዳለብን ይገልጽልናል። ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ ብሏቸዋል፦ “እናንተ ግን እንዲህ ብላችሁ ጸልዩ፤ ‘በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ፣ ስምህ ይቀደስ።’” (ማቴዎስ 6:9 አዲሱ መደበኛ ትርጉም) ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱ ወደ ቅዱሳን፣ ወደ መላእክት ወይም ከአምላክ ውጪ ወደ ሌላ አካል እንዲጸልዩ አላዘዛቸውም። በተጨማሪም ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን እንዲህ ብሏቸዋል፦ “መንገዱ እኔ ነኝ፤ እውነትና ሕይወትም እኔው ነኝ፤ በእኔ በኩል ካልሆነ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።” (ዮሐንስ 14:6 አ.መ.ት) አምላክ አማላጅ እንዲሆን አድርጎ የሾመው ኢየሱስን ብቻ ነው።—ዕብራውያን 7:25 ወደ አምላክ መጸለዬ እንዳለ ሆኖ ወደ ቅዱሳንም ጭምር ብጸልይስ? አምላክ አሥርቱን ትእዛዛት ሲሰጥ “እኔ እግዚአብሔር አምላክህ . . . ቀናተኛ አምላክ ነኝ” ብሏል። (ዘፀአት 20:5 አ.መ.ት) ይሁንና አምላክ “ቀናተኛ” የሆነው እንዴት ነው? የማጥኛ ጽሑፍ ያለው አዲሱ መደበኛ ትርጉም በግርጌ ማስታወሻው ላይ እንደሚናገረው “ቀናተኛ” ሲባል “እርሱን ብቻ ማምለክን ይጠይቃል።” በመሆኑም አምላክ ጸሎትን ጨምሮ ከአምልኮ ጋር የተያያዙ ማንኛውንም ነገሮች ለእሱ ብቻ እንድናቀርብ ይፈልጋል።—ኢሳይያስ 48:11 ከእሱ ውጪ ሌላው ቀርቶ ለቅዱሳንና ለመላእክትም ብንጸልይ አምላክ ያዝንብናል። ሐዋርያው ዮሐንስ ለአንድ መልአክ የአምልኮ ስግደት ሊያቀርብለት ሲል መልአኩ እንደሚከተለው በማለት አስቁሞታል፦ “ተው! ይህን አታድርግ! እኔም ከአንተና የኢየሱስን ምስክር ከያዙት ወንድሞችህ ጋር አገልጋይ ነኝ፤ ለእግዚአብሔር ስገድ።”—ራእይ 19:10 አ.መ.ት ተዛማጅ ርዕሶች ጸሎት እምነት እና አምልኮ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው እነዚህንስ አይተሃቸዋል? የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች የመጽሐፍ ቅዱስ ኮርሳችንን ለምን አትሞክረውም? አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ ኮርስ ከአስተማሪ ጋር። አትም አጋራ አጋራ ወደ ቅዱሳን መጸለይ ይገባኛል? የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው ወደ ቅዱሳን መጸለይ ይገባኛል? የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ ወደ ቅዱሳን መጸለይ ይገባኛል? https://cms-imgp.jw-cdn.org/img/p/502012527/univ/art/502012527_univ_sqr_xl.jpg ijwbq 29