የይሖዋ ምሥክሮች መስቀልን ለአምልኮ የማይጠቀሙበት ለምንድን ነው? አጫውት የይሖዋ ምሥክሮች መስቀልን ለአምልኮ የማይጠቀሙበት ለምንድን ነው? ይቅርታ፣ ማጫወቻው መሥራት አልቻለም። ይህን ቪዲዮ አውርድ ጽሑፉን አሳይ ጽሑፉን ደብቅ ብዙ ሰዎች መስቀል በየትኛውም የዓለም ክፍል የሚኖሩ ክርስቲያኖች መለያ እንደሆነ ይሰማቸዋል። እኛ የይሖዋ ምሥክሮች ክርስቲያኖች ብንሆንም መስቀልን ለአምልኮ አንጠቀምበትም። ለምን? አንደኛው ምክንያት መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ የሞተው የመስቀል ቅርጽ ባለው እንጨት ላይ ሳይሆን በአንድ ወጥ እንጨት ላይ እንደሆነ ስለሚናገር ነው። በተጨማሪም መጽሐፍ ቅዱስ ለክርስቲያኖች “ከጣዖት አምልኮ ሽሹ” የሚል ጠንካራ ማሳሰቢያ ይሰጣል። ይህ ደግሞ መስቀልን ለአምልኮ መጠቀምን ይጨምራል።—1 ቆሮንቶስ 10:14፤ 1 ዮሐንስ 5:21 ኢየሱስ “በመካከላችሁ ፍቅር ካለ ሰዎች ሁሉ ደቀ መዛሙርቴ እንደሆናችሁ በዚህ ያውቃሉ” ማለቱ ትኩረት የሚስብ ነው። (ዮሐንስ 13:34, 35) ኢየሱስ ይህን በማለት፣ እውነተኛ ተከታዮቹ ተለይተው የሚታወቁት የራስን ጥቅም መሥዋዕት የሚያደርግ ፍቅር በማሳየት እንጂ በመስቀል ወይም በሌላ በማንኛውም ዓይነት ምስል እንዳልሆነ ግልጽ አድርጓል። ተዛማጅ ርዕሶች ብዙ ጊዜ የሚነሱ ጥያቄዎች እነዚህንስ አይተሃቸዋል? የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ትምህርቶች አምላክ ምስሎችን ተጠቅመን የምናቀርበውን አምልኮ ይቀበላል? ምስሎችን ተጠቅመን ማምለካችን ወደማይታየው አምላክ ለመቅረብ ይረዳናል? የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች የመጽሐፍ ቅዱስ ኮርሳችንን ለምን አትሞክረውም? አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ ኮርስ ከአስተማሪ ጋር። አትም አጋራ አጋራ የይሖዋ ምሥክሮች መስቀልን ለአምልኮ የማይጠቀሙበት ለምንድን ነው? ብዙ ጊዜ የሚነሱ ጥያቄዎች የይሖዋ ምሥክሮች መስቀልን ለአምልኮ የማይጠቀሙበት ለምንድን ነው? የኢትዮጵያ ምልክት ቋንቋ የይሖዋ ምሥክሮች መስቀልን ለአምልኮ የማይጠቀሙበት ለምንድን ነው? https://cms-imgp.jw-cdn.org/img/p/502013309/univ/art/502013309_univ_sqr_xl.jpg ijwfq 30