በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

የቤቴል ጉብኝት

ቤቴል በሚል ስያሜ የሚታወቁትን ቅርንጫፍ ቢሮዎቻችንን እንድትጎበኝ ሞቅ ያለ ግብዣ እናቀርብልሃለን። በአንዳንዶቹ ቅርንጫፍ ቢሮዎች ውስጥ ያለአስጎብኚ የሚታዩ አውደ ርዕዮችም ተዘጋጅተዋል።

ጉብኝት በድጋሚ ተጀምሯል፦ ከሰኔ 1, 2023 አንስቶ በብዙ አገሮች ውስጥ የሚገኙ ቅርንጫፍ ቢሮዎቻችን በድጋሚ ለጉብኝት ክፍት ሆነዋል። ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት መጎብኘት የምትፈልገውን ቅርንጫፍ ቢሮ አነጋግር። በኮቪድ-19 መያዝህ በምርመራ ከተረጋገጠ፣ የጉንፋን ምልክት ከታየብህ ወይም በቅርቡ በኮቪድ-19 ከተያዘ ሰው ጋር ተገናኝተህ ከነበረ እባክህ ቅርንጫፍ ቢሮዎቻችንን አትጎብኝ።

ማዳጋስካር

Vavolombelon’i Jehovah

Lot 1207 MC

Mandrosoa

105 IVATO

MADAGASCAR

+261 2022-44837

+261 3302-44837 (ሞባይል)

የጉብኝት ፕሮግራም

ከሰኞ እስከ ዓርብ

ጠዋት ከ1:30 እስከ 5:00 እና ከሰዓት ከ7:00 እስከ 10:00

የሚወስደው ጊዜ 1 ሰዓት

ዋና ዋና እንቅስቃሴዎች

መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፎች በማላጋሲ፣ በታንካራና፣ በታንዶሪና በቬዞ ቋንቋዎች የሚተረጎሙ ከመሆኑም ሌላ በድምፅ የተቀረጹ ነገሮች በማላጋሲ ይዘጋጃሉ። ወደ 600 ገደማ የሚሆኑ ጉባኤዎች የሚያደርጉትን መንፈሳዊ እንቅስቃሴ በበላይነት ይከታተላል። በየወሩ ከ270,000 በላይ መጻሕፍትና ብሮሹሮች እንዲሁም 600,000 መጽሔቶች ይላካሉ።

የጉብኝት ብሮሹር አውርድ።