የቤቴል ጉብኝት
ቤቴል በሚል ስያሜ የሚታወቁትን ቅርንጫፍ ቢሮዎቻችንን እንድትጎበኝ ሞቅ ያለ ግብዣ እናቀርብልሃለን። በአንዳንዶቹ ቅርንጫፍ ቢሮዎች ውስጥ ያለአስጎብኚ የሚታዩ አውደ ርዕዮችም ተዘጋጅተዋል።
ጉብኝት በድጋሚ ተጀምሯል፦ ከሰኔ 1, 2023 አንስቶ በብዙ አገሮች ውስጥ የሚገኙ ቅርንጫፍ ቢሮዎቻችን በድጋሚ ለጉብኝት ክፍት ሆነዋል። ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት መጎብኘት የምትፈልገውን ቅርንጫፍ ቢሮ አነጋግር። በኮቪድ-19 መያዝህ በምርመራ ከተረጋገጠ፣ የጉንፋን ምልክት ከታየብህ ወይም በቅርቡ በኮቪድ-19 ከተያዘ ሰው ጋር ተገናኝተህ ከነበረ እባክህ ቅርንጫፍ ቢሮዎቻችንን አትጎብኝ።
ፊጂ
19 St. Fort Street
SUVA
FIJI
+679 330-4766
የጉብኝት ፕሮግራም
ከሰኞ እስከ ዓርብ
ጠዋት ከ2:00 እስከ 5:00 እና ከሰዓት ከ7:00 እስከ 10:00
የሚወስደው ጊዜ 1 ሰዓት
ዋና ዋና እንቅስቃሴዎች
የይሖዋ ምሥክሮች በቱቫሉ፣ በናኡሩ፣ በኪሪባቲ፣ በፊጂና በቫኑአቱ የሚያደርጉትን መንፈሳዊ እንቅስቃሴ በበላይነት ይከታተላል። መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፎች በሮቱማን፣ በቢስላማ፣ በቱቫሉ፣ በናውሩዋን፣ በኪሪባቲና በፊጂኛ ቋንቋዎች ይተረጎማሉ።